1 ULB ከእነዚህ ነገሮች በኋላ እነሆ የተከፈተ በር በሰማይ አየሁ። እንደ መለከት ድምፅ ሆኖ ሲናገረኝ የነበረው የመጀመሪያው ድምፅ፥«ወደዚህ ና! ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ በኋላ የሚሆነውን አሳይሃለሁ።» አለ። BSB BSB: After this I looked and saw a door standing open in heaven. And the voice I had previously heard speak to me like a trumpet was saying, “Come up here, and I will show you what must happen after these things.”
2 ULB ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤በሰማይ ዙፋን ተዘርግቶ አየሁ፤በዙፋኑም ላይ አንድ የተቀመጠ አካል ነበር። BSB BSB: At once I was in the Spirit, and I saw a throne standing in heaven, with someone seated on it.
3 ULB በዙፋኑም ላይ ተቀምጦ የነበረው መልኩ የኢያስጲድንና የሰርዲኖን ዕንቁ ይመስል ነበር። በዙፋኑም ዙሪያ የመረግድ ዕንቁ የመሰለ ቀስተ ደመና ነበር። BSB BSB: The One seated there looked like jasper and carnelian, and a rainbow that gleamed like an emerald encircled the throne.
4 ULB በዙፋኑም ዙሪያ ሃያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፤በእነዚህም ዙፋኖች ላይ ነጭ ልብስ የለበሱና በራሳቸውም ላይ የወርቅ አክሊል የደፉ ሃያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር። BSB BSB: Surrounding the throne were twenty-four other thrones, and on these thrones sat twenty-four elders dressed in white, with golden crowns on their heads.
5 ULB ከዙፋኑም የመብረቅ ብልጭታና የነጎድጓድ ድምፅ ወጣ። በዙፋኑም ፊት ሰባት መብራቶች ይበሩ ነበር፤እነዚህም ሰባቱ የእግዚአብሔር መንፈሶች ናቸው። BSB BSB: From the throne came flashes of lightning, rumblings, and peals of thunder. Before the throne burned seven torches of fire. These are the seven spirits of God.
6 ULB እንደዚሁም በዙፋኑ ፊት እንደ መስተዋት እጅግ የጠራ ባሕር ነበር። በዙፋኑም ዙሪያ ሁሉ ከፊትና ከኋላ በዐይን የተሞሉ አራት ሕያዋን ፍጡራን ነበሩ። BSB BSB: And before the throne was something like a sea of glass, as clear as crystal. In the center, around the throne, were four living creatures, covered with eyes in front and back.
7 ULB የመጀመሪያው ሕያው ፍጡር አንበሳ ሲመስል፥ሁለተኛው ሕያው ፍጡር ጥጃ ይመስል ነበር፤ሦስተኛው ሕያው ፍጡር የሰውን ፊት የሚመስል ፊት ነበረው፤አራተኛው ሕያው ፍጡር ደግሞ የሚበር ንስር ይመስል ነበር። BSB BSB: The first living creature was like a lion, the second like a calf, the third had a face like a man, and the fourth was like an eagle in flight.
8 ULB አራቱም ሕያዋን ፍጡራን እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፍ ነበራቸው፤ከላይና ከሥርም በዐይኖች የተሞሉ ነበሩ። እነርሱም ቀንና ሌሊት፥ «ቅዱስ፥ቅዱስ፥ቅዱስ፥ በሁሉም ላይ የሚገዛ፥የነበረና ያለ፥ወደፊትም የሚመጣው ጌታ አምላክ» ማለትን አያቋርጡም ነበር። BSB BSB: And each of the four living creatures had six wings and was covered with eyes all around and within. Day and night they never stop saying: “Holy, Holy, Holy, is the Lord God Almighty, who was and is and is to come!”
9 ULB ሕያዋን ፍጡራኑም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠውና ከዘላለም እስከ ዘላለም ለሚኖረው ክብር፥ ሞገስና ምስጋና በሚሰጡበት ጊዜ፥ BSB BSB: And whenever the living creatures give glory, honor, and thanks to the One seated on the throne, who lives forever and ever,
10 ULB ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው ፊት በግምባራቸው ተደፍተው ከዘላለም እስከ ዘላለም ለሚኖረው ሰገዱ፤አክሊላቸውንም በዙፋኑ ፊት አስቀምጠው፥ BSB BSB: the twenty-four elders fall down before the One seated on the throne, and they worship Him who lives forever and ever. They cast their crowns before the throne, saying:
11 ULB «ጌታችንና አምላካችን ሆይ፤አንተ ሁሉንም ነገር ስለፈጠርህ፥በፈቃድህ ስለፈጠርሃቸውና እንደዚያም ሆነው ስለተገኙ ክብር፥ሞገስ፥ኅይልም ልትቀበል ይገባሃል።» ይሉ ነበር። BSB BSB: “Worthy are You, our Lord and God, to receive glory and honor and power, for You created all things; by Your will they exist and were created.”
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.