1 ULB አምስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ አንድን ኮከብ ከሰማይ ወደ ምድር ሲወድቅ አየሁ። ኮከቡም የጥልቁ ጕድጓድ መክፈቻ ተሰጠው፤ BSB BSB: Then the fifth angel sounded his trumpet, and I saw a star that had fallen from heaven to earth, and it was given the key to the pit of the Abyss.
2 ULB እርሱም ጥልቅ የሆነውን ጕድጓድ ከፈተው፤ ጢስም ከታላቅ ምድጃ እንደሚወጣ ጢስ ሆኖ ከጕድጓዱ ወጣ፤ ከጕድጓዱ በሚወጣው ጢስ ምክንያት ፀሐይና አየር ወደ ጨለማነት ተለወጡ፤ BSB BSB: The star opened the pit of the Abyss, and smoke rose out of it like the smoke of a great furnace, and the sun and the air were darkened by the smoke from the pit.
3 ULB ከጢሱም ውስጥ አንበጣዎች በምድር ላይ ወጡ፤የምድር ጊንጦችን ኅይል የመሰለ ኅይል ተሰጣቸው፤ BSB BSB: And out of the smoke, locusts descended on the earth, and they were given power like that of the scorpions of the earth.
4 ULB የምድርንም ሣር ሆነ ማናቸውንም የለመለመ ተክል ወይም ማናቸውንም ዛፍ እንዳይጎዱ ተነገራቸው። መጉዳት የነበረባቸው ግን በግንባራቸው ላይ የእግዚአብሔር ማህተም የሌለባቸውን ሰዎች ብቻ ነው። BSB BSB: They were told not to harm the grass of the earth or any plant or tree, but only those who did not have the seal of God on their foreheads.
5 ULB እነርሱንም ቢሆን ለአምስት ወር ለማሰቃየት ብቻ እንጂ የመግደል ሥልጣን አልተሰጣቸውም። የእነርሱም ስቃይ ጊንጥ ሰውን ነድፎ እንደሚሰማው ስቃይ ዐይነት ነበር። BSB BSB: The locusts were not given power to kill them, but only to torment them for five months, and their torment was like the stinging of a scorpion.
6 ULB በእነዚያ ቀናት ሰዎች ሞትን ይፈልጋሉ፤ነገር ግን አያገኙትም። ለመሞት በብርቱ ይሻሉ፤ ነገር ግን ሞት ከእነርሱ ይሸሻል። BSB BSB: In those days men will seek death and will not find it; they will long to die, but death will escape them.
7 ULB አንበጦቹ ለጦርነት እንደ ተዘጋጁ ፈረሶች ነበሩ። በራሳቸውም ላይ የወርቅ አክሊል የመሰለ ነገር ነበር፤ ፊታቸውም የሰው ፊት ይመስል ነበር። BSB BSB: And the locusts looked like horses prepared for battle, with something like crowns of gold on their heads; and their faces were like the faces of men.
8 ULB የሴቶች ጠጕር የሚመስል ጠጕር ነበራቸው። ጥርሳቸው የአንበሳ ጥርስ ይመስል ነበር። BSB BSB: They had hair like that of women, and teeth like those of lions.
9 ULB የብረት ጥሩር የሚመስልጥሩር ነበራቸው፤ የክንፎቻቸውም ድምፅ ወደ ጦርነት የሚጋልቡ ብዙ ፈረሶችና ሰረገሎች የሚያሰሙትን ድምፅ ይመስል ነበር። BSB BSB: They also had breastplates like breastplates of iron, and the sound of their wings was like the roar of many horses and chariots rushing into battle.
10 ULB እንደ ጊንጥ መንደፊያ ያለው ጅራት ነበራቸው። ሰዎችንም በጅራታቸው ባለ መንደፊያ ለአምስት ወር ለመጉዳት ስልጣን ነበራቸው። BSB BSB: They had tails with stingers like scorpions, which had the power to injure people for five months.
11 ULB በእነርሱም ላይ የጥልቁ ጕድጓድ መልአክ የሆነ ንጉሥ ነበራቸው። ስሙም በዕብራይስጥ አብዶን ሲሆን በግሪክ ደግሞ አጶሊዮን ይባላል፥ BSB BSB: They were ruled by a king, the angel of the Abyss. His name in Hebrew is Abaddon, and in Greek it is Apollyon.
12 ULB የመጀመሪያው ወዮ አልፎአል፥ልብ በል! ከዚህ በኋላ ሌላ ሁለት ጥፋቶች ይመጣሉ። BSB BSB: The first woe has passed. Behold, two woes are still to follow.
13 ULB ስድስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፥ በእግዚአብሔር ፊት ካለው በወርቅ ከተሰራው መሰዊያ ከቀንዶቹ ድምጽ ሲወጣ ሰማሁ። BSB BSB: Then the sixth angel sounded his trumpet, and I heard a voice from the four horns of the golden altar before God
14 ULB ድምፁም መለከት የያዘውን ስድስተኛውን መልአክ፣ «በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ የታሰሩትን አራቱን መላእክት ፍታቸው» አለው። BSB BSB: saying to the sixth angel with the trumpet, “Release the four angels who are bound at the great river Euphrates.”
15 ULB ለዚያ ሰዓትና ለዚያ ቀን ለዚያ ወርና ለዚያ ዓመት ተዘጋጅተው የነበሩት አራት መላእክት የሰዎችን አንድ ሦስተኛ እንዲገድሉ ተፈቱ። BSB BSB: So the four angels who had been prepared for this hour and day and month and year were released to kill a third of mankind.
16 ULB የፈረሰኛው ሰራዊት ብዛት ሁለት መቶ ሚሊዮን ነበር።ቍጥራቸውንም ሰማሁ። BSB BSB: And the number of mounted troops was two hundred million; I heard their number.
17 ULB ፈረሶቹና በፈረሶቹ ላይ የሚጋልቡ በራእይ ያየኋቸው በዚህ ዐይነት ነበር፥ በደረታቸው ላይ የነበረው ጥሩር እንደ እሳት ቀይ፣ እንደ ያክንት (ጥቁር ሰማያዊ)፣ እንደ ዲንም ቢጫ ነበር፥ የፈረሶቹ ራስ የአንበሳ ራስ ይመስል ነበር። ከአፋቸው እሳትና ጢስ ዲንም ይወጣ ነበር። BSB BSB: Now the horses and riders in my vision looked like this: The riders had breastplates the colors of fire, sapphire, and sulfur. The heads of the horses were like the heads of lions, and out of their mouths proceeded fire, smoke, and sulfur.
18 ULB በእነዚህ ሦስት መቅሰፍቶች ማለትም ከአፋቸው በወጣው እሳት፤ ጢስና ዲን የሰዎች አንድ ሦስተኛ ተገደለ። BSB BSB: A third of mankind was killed by the three plagues of fire, smoke, and sulfur that proceeded from their mouths.
19 ULB የፈረሶቹ ኃይል በአፋቸውና በጅራታቸው ነበር፥ ምክንያቱም ጅራታቸው እባብ ይመስላል፥ ራስ አላቸው፥ ሰውን የሚጎዱትም በእርሱ ነበር። BSB BSB: For the power of the horses was in their mouths and in their tails; indeed, their tails were like snakes, having heads with which to inflict harm.
20 ULB በእነዚያ መቅሰፍቶች ከመሞት የተረፉት ሰዎች ከክፉ ሥራቸው ንስሓ አልገቡም፤ አጋንንትንና ከወር፣ ከብር፣ ከናስ፣ ከድንጋይና ከእንጨት የተሠሩ፣ ማየት ወይም መሄድ የማይችሉትን ጣዖታት ማምለክንም አልተዉም። BSB BSB: Now the rest of mankind who were not killed by these plagues still did not repent of the works of their hands. They did not stop worshiping demons and idols of gold, silver, bronze, stone, and wood, which cannot see or hear or walk.
21 ULB እንዲሁም ከነፍሰ ገዳይነት ወይም ከሟርት፥ ከሴስኛነትና፥ ከሌብነት ንስሓ አልገቡም። BSB BSB: Furthermore, they did not repent of their murder, sorcery, sexual immorality, and theft.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.