2 ULB እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን ህዝቡን አልጣላቸውም። ኤልያስ እስራኤልን በመቃወም ከእግዚአብሔር ጋር እንዴት እንደተከራከረ መጽሀፍ የሚለውን አታውቁምን? BSB BSB: God did not reject His people, whom He foreknew. Do you not know what the Scripture says about Elijah, how he appealed to God against Israel:
3 ULB «ጌታ ሆይ ነቢያትህን ገድለዋል፣ መሰዊያዎችህንም አፍርሰዋል፣ እኔም ብቻዬን ቀርቻለሁ ሊገድሉኝም እየፈለጉኝ ነው።» BSB BSB: “Lord, they have killed Your prophets and torn down Your altars. I am the only one left, and they are seeking my life as well”?
4 ULB ነገር ግን እግዚአብሔር ምን ብሎ መለሰለት? «ለበዓል ያልሰገዱ ሰባት ሺ ሰዎችን ለራሴ ጠብቄ አቆይቻለሁ።» BSB BSB: And what was the divine reply to him? “I have reserved for Myself seven thousand men who have not bowed the knee to Baal.”
5 ULB በዚህም በአሁኑ ዘመንም ከጸጋ ምርጫ የተነሳ ትሩፋን አሉ። BSB BSB: In the same way, at the present time there is a remnant chosen by grace.
6 ULB ነገር ግን በጸጋ ከሆነ ከእንግዲህ በሥራ አይደለም።አለዚያ ጸጋ ከእንግዲህ ጸጋ መሆኑ ቀርቷል። BSB BSB: And if it is by grace, then it is no longer by works. Otherwise, grace would no longer be grace.
7 ULB እንግዲህ ምን ይሁን፣ እስራኤል ይፈልገው የነበረውን ነገር አላገኘም፥ የተመረጡት ግን አግኝተውታል፥ የቀሩት ግን ደንዳኖች ሆነዋል። BSB BSB: What then? What Israel was seeking, it failed to obtain, but the elect did. The others were hardened,
8 ULB ይህም ልክ «እያዩ እንዳያዩ እየሰሙ እንዳይሰሙ እስከ አሁን እግዚአብሔር ያለማስተዋልን መንፈስ ሰጣቸው» ተብሎ እንደተጻፈው ነው። BSB BSB: as it is written: “God gave them a spirit of stupor, eyes that could not see, and ears that could not hear, to this very day.”
9 ULB ዳዊትም «ገበታቸው መረብ፥ወጥመድ፥የእንቅፋት ድንጋይና የበቀል ይሁንባቸው» ይላል። BSB BSB: And David says: “May their table become a snare and a trap, a stumbling block and a retribution to them.
10 ULB እንዳያዩ አይናቸው ይጨልም፥ ሁልጊዜ ጀርባቸው እንደጎበጠ ይቅር።» ይላል። BSB BSB: May their eyes be darkened so they cannot see, and their backs be bent forever.”
11 ULB «እስኪወድቁ ድረስ ተሰናከሉ» እላለሁን? ፈጽሞ አይሁን። በቅናት ሊያነሳሳቸው በእነርሱ ውድቀት ለአህዛብ ድነት ሆነ። BSB BSB: I ask then, did they stumble so as to fall beyond recovery? Certainly not! However, because of their trespass, salvation has come to the Gentiles to make Israel jealous.
12 ULB እንግዲህ ውድቀታቸው ለዓለም ሙላት ከሆነ ጉድለታችው ለአህዛብም ሙላት ከሆነ ሙላታቸው እንዴት ታላቅ ይሆን? BSB BSB: But if their trespass means riches for the world, and their failure means riches for the Gentiles, how much greater riches will their fullness bring!
13 ULB አሁን ለእናንተ ለአህዛብ እናገራለሁ። የአህዛብ ሀዋሪያ እንደመሆኔ በአገልግሎቴ እመካለሁ። BSB BSB: I am speaking to you Gentiles. Inasmuch as I am the apostle to the Gentiles, I magnify my ministry
14 ULB ምናልባት የገዛ ሥጋዬ የሆኑትን አስቀናና አንዳንዶቹን እናድን ይሆናል። BSB BSB: in the hope that I may provoke my own people to jealousy and save some of them.
15 ULB የእነኚያ መጣል ለዓለም የመታረቅ ምክንያት ከሆነ ተቀባይነት ማግኘታቸው ከሞት ወደ ህይወት ማምለጥ ካልሆን ምን ሊሆን ይችላል? BSB BSB: For if their rejection is the reconciliation of the world, what will their acceptance be but life from the dead?
16 ULB በኩሩ ቅዱስ ከሆነ ሊጡም ቅዱስ ነው። ሥሩ ቅዱስ ከሆነ ቅርንጫፉ ቅዱስ ነው። BSB BSB: If the first part of the dough is holy, so is the whole batch; if the root is holy, so are the branches.
17 ULB ነገር ግን አንዳንዶቹ ቅርንጫፎች በመሰበራቸው ምክንያት አንተ የበረሀ ወይራ ዛፍ ቅርንጫፍ ባልወደቁት ቅርንጫፎች መካከል ብትጣበቅና የወይራ ዛፉን ሥር ብልጽግና ተካፋይ ብትሆን BSB BSB: Now if some branches have been broken off, and you, a wild olive shoot, have been grafted in among the others to share in the nourishment of the olive root,
18 ULB በቅርንጫፎቹ ላይ አትኩራራ። ብትኩራራ ግን ሥሩ አንተን ተሸከምህ እንጂ አንተ ሥሩን አልተሸከመከውም። BSB BSB: do not boast over those branches. If you do, remember this: You do not support the root, but the root supports you.
19 ULB «ቅርንጫፎቹ ስለተሰበሩ እኔ ተተካሁ» ትላለህ። BSB BSB: You will say then, “Branches were broken off so that I could be grafted in.”
20 ULB እውነት ነው ባለማመናቸው ምክንያት እነርሱ ተቆርጠው ወድቀዋል አንተ ደግሞ በእምነት ቆመሀል። ፍራ እንጂ ራስህ ከፍ አድርገህ አታስብ። BSB BSB: That is correct: They were broken off because of unbelief, but you stand by faith. Do not be arrogant, but be afraid.
21 ULB እግዚአብሔር ለመጀመሪያዎቹ ቅርንጫፎች ካልራራ ለአንተም አይራራልህም። BSB BSB: For if God did not spare the natural branches, He will certainly not spare you either.
22 ULB እንግዲህ የእግዚአብሔርን የምህረት ሥራና ጭካኔ አስተውል። በአንድ በኩል ጭካኔው በወደቁት በአይሁድ ላይ መጣ፥በሌላ በኩል ደግሞ ጸንታችሁ ከቆያችሁ ምህረቱ ወደ እናንተ መጥቷል። አለበለዚያ ግን እናንተም ተቆርጣችሁ ትጣላላችሁ። BSB BSB: Take notice, therefore, of the kindness and severity of God: severity to those who fell, but kindness to you, if you continue in His kindness. Otherwise you also will be cut off.
23 ULB ደግሞም እነርሱ ባለማመናቸው ካልጸኑ እንደገና በዛፉ ላይ ሊተከሉ ይችላሉ። እግዚአብሔር እንደገና በዛፉ ላይ ሊተክላቸው ይችላልና። BSB BSB: And if they do not persist in unbelief, they will be grafted in, for God is able to graft them in again.
24 ULB እናንተ መነሻችሁ የበረሀ የወይራ ዛፍ የሆነና ተቆርጣችሁ የነበራችሁ ቅርንጫፎች ከተፈጥሮ ህግ ውጪ በመልካሙ የወይራ ዛፍ ላይ እንደገና ከተተከላችሁ የመጀመሪያዎቹ ቅርንጫፎች እነኝህ አይሁድ ወደገዛ ዛፋቸው እንዴት እንደግና አይጣበቁም? BSB BSB: For if you were cut from a wild olive tree, and contrary to nature were grafted into one that is cultivated, how much more readily will these, the natural branches, be grafted into their own olive tree!
26 ULB ስለዚህም እስራኤል በሙሉ እንደተጻፈው ይድናሉ። «ከጽዮን ነጻ አውጪ ይነሳል ከያዕቆብም የማይገባ አካሄድን ያስወግዳል። BSB BSB: And so all Israel will be saved, as it is written: “The Deliverer will come from Zion; He will remove godlessness from Jacob.
27 ULB ኃጢአታቸውን በማስወግድላቸው ጊዜ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው።» BSB BSB: And this is My covenant with them when I take away their sins.”
29 ULB ምክንያቱም የእግዚአብሔር ስጦታና ጥሪ አይለወጥም። BSB BSB: For God’s gifts and His call are irrevocable.
30 ULB እናንተ ቀድሞ ለእግዚአብሔር የማትታዘዙ የነበራችሁ አሁን ግን በእነርሱ አለመታዘዝ ምክንያት ምህረትን አግኝታችኋል። BSB BSB: Just as you who formerly disobeyed God have now received mercy through their disobedience,
31 ULB ልክ እንደዚያው ዘንድ እነዚህ አይሁድ አሁን የማይታዘዙ ሆነዋል። በውጤቱም ለእናንት በተሰጠው ምህረት እነርሱ ደግሞ እንዲቀበሉ ነበር። BSB BSB: so they too have now disobeyed, in order that they too may now receive mercy through the mercy shown to you.
32 ULB ምህረቱን ለሁሉ ያሳይ ዘንድ እግዚአብሔር ሁሉን ባለመታዘዝ ዘግቶታልና። BSB BSB: For God has consigned everyone to disobedience so that He may have mercy on everyone.
34 ULB «የጌታን ልብ የሚያውቅ ማነው? አማካሪውስ የሆነ ማነው? BSB BSB: “Who has known the mind of the Lord? Or who has been His counselor?”
35 ULB ወይስ መልሶ ይከፍለው ዘንድ ለእግዚአብሔር ያበደረ ማነው?» BSB BSB: “Who has first given to God, that God should repay him?”
36 ULB ሁሉም ነገር ከእርሱ በእርሱና ለእርሱ ነው። ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን። አሜን። BSB BSB: For from Him and through Him and to Him are all things. To Him be the glory forever! Amen.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.