2 ULB እኛም ደግሞ በእርሱ በኩል አሁን ወደቆምንበት ወደዚህ ጸጋ በእምነት መቅረብ አለን። በእግዚአብሔር ክብር ውስጥ ተካፋዮች እንሆን ዘንድ እግዚአብሔር ስለወደፊቱ በሰጠን ተስፋ በመተማመን ደስ ይለናል። BSB BSB: through whom we have gained access by faith into this grace in which we stand. And we rejoice in the hope of the glory of God.
3 ULB ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን በመከራዎቻችን ደግሞ ደስ ይለናል። መከራ መጽናትን እንደሚያደርግ እናውቃለን። BSB BSB: Not only that, but we also rejoice in our sufferings, because we know that suffering produces perseverance;
4 ULB መጽናት ተቀባይነትን፥ ተቀባይነትም ስለ ወደፊቱ መተማመኛን ያስገኛል። BSB BSB: perseverance, character; and character, hope.
5 ULB በተሰጠን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የእግዚአብሔር ፍቅር ወደ ልባችን ውስጥ ስለፈሰሰ ይህ ተስፋ ሐዘን የለበትም። BSB BSB: And hope does not disappoint us, because God has poured out His love into our hearts through the Holy Spirit, whom He has given us.
7 ULB ስለ ጻድቅ ሰው የሚሞት ከስንት አንዱ ነው። ይህም ማለት ስለ ደግ ሰው ለመሞት የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል። BSB BSB: Very rarely will anyone die for a righteous man, though for a good man someone might possibly dare to die.
8 ULB ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች እያለን ክርስቶስ ስለ እኛ መሞቱ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያረጋግጣል። BSB BSB: But God proves His love for us in this: While we were still sinners, Christ died for us.
9 ULB እንግዲህ አሁን በደሙ ስለ ጸደቅን ይበልጡኑ በእርሱ ከእግዚአብሔር ቁጣ እንድናለን። BSB BSB: Therefore, since we have now been justified by His blood, how much more shall we be saved from wrath through Him!
10 ULB ጠላቶች እያለን በልጁ ሞት ከእግዚአብሔር ጋር ከታረቅን ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን። BSB BSB: For if, when we were enemies of God, we were reconciled to Him through the death of His Son, how much more, having been reconciled, shall we be saved through His life!
11 ULB ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን አሁን ይህንን ዕርቅ ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እኛ ደግሞ በእግዚአብሔር ደስ ይለናል። BSB BSB: Not only that, but we also rejoice in God through our Lord Jesus Christ, through whom we have now received reconciliation.
13 ULB ሕግ እስኪመጣ ድረስ ኃጢአት በዓለም ነበረ፥ነገር ግን ሕግ በሌለበት ኃጢአት አይቆጠርም። BSB BSB: For sin was in the world before the law was given; but sin is not taken into account when there is no law.
14 ULB ይሁንና ሊመጣ ላለው ምሳሌ የሆነው የአዳምን አይነት ያለመታዘዝ ኃጢአት ባላደረጉት ላይ እንኳን ሳይቀር ከአዳም እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ። BSB BSB: Nevertheless, death reigned from Adam until Moses, even over those who did not sin in the way that Adam transgressed. He is a pattern of the One to come.
15 ULB ነጻ ስጦታው ግን እንደ መተላለፉ አይደለም። በአንዱ መተላለፍ ብዙዎች ከሞቱ የእግዚአብሔር ጸጋና በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ በኩል የሆነው ስጦታ ከዚያ ይልቅ ለብዙዎች በዛ። BSB BSB: But the gift is not like the trespass. For if the many died by the trespass of the one man, how much more did God’s grace and the gift that came by the grace of the one man, Jesus Christ, abound to the many!
16 ULB ስጦታው እንደተሰራው ኃጢአት ውጤት አይደለም። በአንድ ወገን በአንዱ ሰው መተላለፍ ምክንያት የኩነኔ ፍርድ መጣ። በሌላ ወገን ግን ጽድቅን የሚያስገኘው ነጻ ስጦታው ከብዙ መተላለፍ በኋላ መጣ። BSB BSB: Again, the gift is not like the result of the one man’s sin: The judgment that followed one sin brought condemnation, but the gift that followed many trespasses brought justification.
17 ULB በአንዱ ሰው መተላለፍ ሞት በእርሱ በኩል ከነገሠ የጸጋን ብዛትና በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት በኩል የጽድቅን ስጦታ የተቀበሉት አብልጠው ይነግሳሉ። BSB BSB: For if, by the trespass of the one man, death reigned through that one man, how much more will those who receive the abundance of grace and of the gift of righteousness reign in life through the one man, Jesus Christ!
19 ULB በአንድ ሰው አለመታዘዝ በኩል ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደሆኑ እንዲሁ በአንዱ መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ። BSB BSB: For just as through the disobedience of the one man the many were made sinners, so also through the obedience of the one man the many will be made righteous.
21 ULB ኃጢአት በሞት እንደ ነገሠ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለዘላለም ሕይወት ጸጋው በጽድቅ አብልጦ እንዲነግሥ ይህ ሆነ። BSB BSB: so that, just as sin reigned in death, so also grace might reign through righteousness to bring eternal life through Jesus Christ our Lord.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.