1 ULB እነሆ፣ ብዝበዛሽን በውስጥሽ የሚከፋፈሉበት ቀን ይመጣል። BSB BSB: Behold, a day of the LORD is coming when your plunder will be divided in your presence.
2 ULB ሕዝብን ሁሉ ለጦርነት ኢየሩሳሌም ላይ አስነሣለሁ፤ ከተማዋም ትያዛለች። ቤቶች ይበዘበዛሉ፣ ሴቶች ይነወራሉ። የከተማው ግማሽ ሕዝብ በምርኮ ይወሰዳል፤ የተቀረው ሕዝብ ግን ከከተማው አይጠፋም። BSB BSB: For I will gather all the nations for battle against Jerusalem, and the city will be captured, the houses looted, and the women ravished. Half of the city will go into exile, but the rest of the people will not be removed from the city.
3 ULB ነገር ግን በጦርነት ጊዜ እንደሚዋጋ ያህዌ እነዚያን ሕዝቦች ይዋጋል። BSB BSB: Then the LORD will go out to fight against those nations, as He fights in the day of battle.
4 ULB በዚያ ጊዜ እግሮቹ ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ባለው ደብረ ዘይት ተራራ ይቆማሉ። የደብረ ዘይት ተራራ በመካከሉ ባለው ታላቅ ሸለቆ ወደ ምሥራቅና ምዕራብ ለሁለት ይከፈልና እኩሌታው ወደ ሰሜን፣ እኩሌታው ወደ ደቡብ ይሄዳሉ። BSB BSB: On that day His feet will stand on the Mount of Olives, east of Jerusalem, and the Mount of Olives will be split in two from east to west, forming a great valley, with half the mountain moving to the north and half to the south.
6 ULB በዚያ ቀን ብርሃን አይኖርም፣ ብርድና ውርጭም አይኖርም። BSB BSB: On that day there will be no light, no cold or frost.
7 ULB በዚያ በእግዚአብሔር ብቻ በሚታወቅ ቀን ቀንም ሆነ ማታ ከኢየሩሳሌም ይፈስሳል። BSB BSB: It will be a unique day known only to the LORD, without day or night; but when evening comes, there will be light.
8 ULB ክረምትም ሆነ በጋ እኩሌታው ወደ ምሥራቅ ባሕር፣ እኩሌታው ወደ ምዕራብ ባሕር ይፈስሳል። BSB BSB: And on that day living water will flow out from Jerusalem, half of it toward the Eastern Sea and the other half toward the Western Sea, in summer and winter alike.
9 ULB ያህዌ በመላው ምድር ይነግሣል። በዚያ ቀን አንድ አምላክ ያህዌ ብቻ ይሆናል፤ ስሙም አንድ ይሆናል። BSB BSB: On that day the LORD will become King over all the earth—the LORD alone, and His name alone.
10 ULB ከጌባ አንሥቶ በኢየሩሳሌም ደቡብ እስካለችው ሬሞን ድረስ ምድር ሁሉ እንደ አረባ ትሆናለች። ኢየሩሳሌም ከፍ እንዳለች ትዘልቃለች። ከብንያም በር አንሥቶ የመጀመሪያው በር እስከ ነበረበት እስከ ማእዘኑ በር ድረስ፣ ከሐናንኤል ግንብ እስከ ንጉሡ ወይን መርገጫ ድረስ በቦታዋ ትኖራለች። BSB BSB: All the land from Geba to Rimmon south of Jerusalem will be turned into a plain, but Jerusalem will be raised up and will remain in her place, from the Benjamin Gate to the site of the First Gate to the Corner Gate, and from the Tower of Hananel to the royal winepresses.
11 ULB ሕዝቡም በኢየሩሳሌም ይኖራል፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከባድ ጥፋት አይመጣባቸውም፤ ኢየሩሳሌም በሰላም ትኖራለች። BSB BSB: People will live there, and never again will there be an utter destruction. So Jerusalem will dwell securely.
12 ULB ኢየሩሳሌምን በወጉ ሕዝቦች ሁሉ ላይ ያህዌ የሚያመጣባቸው መቅሠፍቶች እነዚህ ናቸው፤ በእግራቸው ቆመው እያለ ሥጋቸው ይበሰብሳል። ዐይኖቻቸው ጉድጓዶቻቸው ውስጥ እያሉ ይበሰብሳሉ፤ ምላሳቸው አፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል። BSB BSB: And this will be the plague with which the LORD strikes all the peoples who have warred against Jerusalem: Their flesh will rot while they stand on their feet, their eyes will rot in their sockets, and their tongues will rot in their mouths.
13 ULB በዚያ ቀን ከያህዌ ዘንድ ታላቅ ፍርሃት ይመጣባቸዋል። እያንዳንዱ ሰው የባልንጀራውን እጅ ይይዛል፤ አንዱ ሌላውን ይወጋል። BSB BSB: On that day a great panic from the LORD will come upon them, so that each will seize the hand of another, and the hand of one will rise against the other.
14 ULB ይሁዳም ኢየሩሳሌምን ይወጋል። የአካባቢውን ሕዝቦች ሁሉ ሀብት ይሰበስባሉ፤ ወርቅ፣ ብርና ልብስ በብዛት ይኖራል። BSB BSB: Judah will also fight at Jerusalem, and the wealth of all the surrounding nations will be collected—gold, silver, and apparel in great abundance.
15 ULB ፈረሶችና በቅሎዎች ላይ፣ ግመሎችና አይሆች ላይ መቅሠፍት ይወርዳል፤ ይኸው መቅሠፍት በየሰፈሩ ያሉ እንስሳትንም ሁሉ ይመታል። BSB BSB: And a similar plague will strike the horses and mules, camels and donkeys, and all the animals in those camps.
16 ULB ኢየሩሳሌምን ከወጓት ሕዝቦች ከሞት የተረፉት ለንጉሡ ለሰራዊት ጌታ ለያህዌ ለመስገድና የዳስን በዓል ለማክበር በየዓመቱ ይወጣሉ። BSB BSB: Then all the survivors from the nations that came against Jerusalem will go up year after year to worship the King, the LORD of Hosts, and to celebrate the Feast of Tabernacles.
17 ULB በምድር ካሉ ሕዝቦች ሁሉ ለንጉሡ፣ ለሰራዊት ጌታ ለያህዌ ለመስገድ ወደ ኢየሩሳሌም የማይወጣ ካለ፣ ያህዌ ደግሞ ዝናብ አያዘንብላቸውም። BSB BSB: And should any of the families of the earth not go up to Jerusalem to worship the King, the LORD of Hosts, then the rain will not fall on them.
18 ULB የግብፅ ሕዝብ የማይወጣ ከሆነ ዝናብ አያገኝም። የዳስ በዓልን ለማክበር በማይወጡ ሕዝቦች ላይ መቅሠፍት ከያህዌ ዘንድ ይመጣባቸዋል። BSB BSB: And if the people of Egypt will not go up and enter in, then the rain will not fall on them; this will be the plague with which the LORD strikes the nations who do not go up to celebrate the Feast of Tabernacles.
19 ULB የዳስ በዓልን ለማክበር በማይወጣው ግብፅና ማንኛውም ሕዝብ ላይ የሚመጣው ቅጣት ይህ ይሆናል። BSB BSB: This will be the punishment of Egypt and of all the nations that do not go up to celebrate the Feast of Tabernacles.
20 ULB በዚያ ቀን በፈረሶች ሻኩራ ላይ፣ “ለእግዚአብሔር የተቀደሰ” የሚል ጽሑፍ ይቀረጻል፤ በእግዚአብሔር ቤት ያሉት መታጠቢያዎች መሠዊያው ፊት እንዳሉት ሳህኖች የተቀደሱ ይሆናሉ፤ BSB BSB: On that day, HOLY TO THE LORD will be inscribed on the bells of the horses, and the cooking pots in the house of the LORD will be like the sprinkling bowls before the altar.
21 ULB በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉት ምንቸቶች ሁሉ ለሰራዊት ጌታ ለያህዌ ይቀደሳሉ፤ መሥዋዕት ለማቅረብ የሚመጡ ሁሉ በእነርሱ በማብሰል ይበሉባቸዋል። በዚያ ቀን በሰራዊት ጌታ በያህዌ ቤት ውስጥ ከእንግዲህ ነጋዴዎች አይኖሩም። BSB BSB: Indeed, every pot in Jerusalem and Judah will be holy to the LORD of Hosts, and all who sacrifice will come and take some pots and cook in them. And on that day there will no longer be a Canaanite in the house of the LORD of Hosts.