1 ULB ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክም ተመልሶ፣ ከእንቅልፉ እንደሚነቃ ሰው አንቃኝ። BSB BSB: Then the angel who was speaking with me returned and woke me, as a man is awakened from his sleep.
2 ULB እርሱም፣ “ምን ይታይሃል?” አለኝ። እኔም፣ “በዐናቱ ላይ፣ የዘይት ማሰሮ ያለበት ሁለመናው ወርቅ የሆነ መቅረዝ አየሁ። መቅረዙም ላይ በእያንዳንዱ ጫፍ ሰባት ክሮች ያሏቸው ሰባት መብራቶች ነበር። BSB BSB: “What do you see?” he asked. “I see a solid gold lampstand,” I replied, “with a bowl at the top and seven lamps on it, with seven spouts to the lamps.
3 ULB ደግሞም አንዱ ከዘይት ማሰሮው በስተ ቀኝ፣ ሌላውም በስተ ግራ ሁለት የወይራ ዛፎች አሉ።” BSB BSB: There are also two olive trees beside it, one on the right side of the bowl and the other on its left.”
4 ULB እኔም፣ ያነጋገረኝ የነበረውን መልአክ፣ “ጌታዬ እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልሁት። BSB BSB: “What are these, my lord?” I asked the angel who was speaking with me.
5 ULB ከእኔ ጋር እየተነጋገረ የነበረው መልአክም መልሶ፣ “እነዚህ ምን እንደ ሆኑ አታውቅም?” አለኝ። እኔም፣ “ጌታዬ ሆይ፣ አላውቅም” አልሁት። BSB BSB: “Do you not know what they are?” replied the angel. “No, my lord,” I answered.
6 ULB ከዚያም እንዲህ አለኝ፤ “ለዘሩባቤል የመጣው የያህዌ ቃል ይህ ነው፤ ‘በመንፈሴ እንጂ፣ በኀይልና በብርታት አይደለም፤ ይላል የሰራዊት ጌታ ያህዌ። BSB BSB: So he said to me, “This is the word of the LORD to Zerubbabel: Not by might nor by power, but by My Spirit, says the LORD of Hosts.
7 ULB አንተ ታላቅ ተራራ ምንድነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ፤ ሰዎች “ሞገስ! ሞገስ ይሁንለት!” ብለው እየጮኹ እርሱ መደምደሚያውን ድንጋይ ያወጣል። BSB BSB: What are you, O great mountain? Before Zerubbabel you will become a plain. Then he will bring forth the capstone accompanied by shouts of ‘Grace, grace to it!’”
8 ULB የያህዌ ቃል ወደ እኔ መጣ፤ BSB BSB: Then the word of the LORD came to me, saying,
9 ULB “የዘሩባቤል እጆች የዚህን ቤት መሠረት እንደ ጣሉ ሁሉ፣ የእርሱ እጆች ይፈጽሙታል። ያኔ፣ የሰራዊት ጌታ ያህዌ ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ። BSB BSB: “The hands of Zerubbabel have laid the foundation of this house, and his hands will complete it. Then you will know that the LORD of Hosts has sent me to you.
10 ULB የጥቂቱን ቀን ነገሮች የናቀ ግን ነው? እነዚህ ሰዎች በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን ሲያዩ በጣም ደስ ይላቸዋል። እነዚህ ሰባት መብራቶች በምድር ሁሉ የሚመላለሱ የያህዌ ዐይኖች ናቸው። BSB BSB: For who has despised the day of small things? But these seven eyes of the LORD, which scan the whole earth, will rejoice when they see the plumb line in the hand of Zerubbabel.”
11 ULB ከዚያም መልአኩን፣ “ከመቅረዙ ግራና ቀኝ የቆሙት እነዚህ ሁለት የወይራ ዛፎች ምንድን ናቸው?” በማለት ጠየቅሁት። BSB BSB: Then I asked the angel, “What are the two olive trees on the right and left of the lampstand?”
12 ULB እንደ ገናም፣ “በሁለት የወርቅ ቧንቧዎች አጠገብ የወርቅ ዘይት የሚያፈስሱት እነዚህ ሁለት የወይራ ቅንርንጫፎችስ ምንድን ናቸው?” አልሁት። BSB BSB: And I questioned him further, “What are the two olive branches beside the two gold pipes from which the golden oil pours?”
13 ULB እርሱም፣ “እነዚህ ምን እንደ ሆኑ አታውቅም?” አለኝ፤ እኔም፣ “ጌታዬ ሆይ፣ አላውቅም” አልሁት። BSB BSB: “Do you not know what these are?” he inquired. “No, my lord,” I replied.
14 ULB እርሱም፣ “እነዚህ የምድርን ሁሉ ጌታ ለማገለል የሚቆሙ ሁለቱ የወይራ ዛፎች ናቸው” አለኝ። BSB BSB: So he said, “These are the two anointed ones who are standing beside the Lord of all the earth.”