1 ULB ከዚያም ዘወር ብዬ ዐይኖቼን ወደ ላይ ሳነሣ አራት ሰረገሎች ከሁለት ተራሮች መካከል ሲመጡ አየሁ፤ ሁለቱ ተራሮች የናስ ተራሮች ነበር። BSB BSB: And again I lifted up my eyes and saw four chariots coming out from between two mountains—mountains of bronze.
2 ULB የመጀመሪያው ሰረገላ ቀይ ፈረሶች ነበሩት፤ ሁለተኛው ሰረገላ ጥቁር ፈረሶች ነበሩት። BSB BSB: The first chariot had red horses, the second black horses,
3 ULB ሦስተኛው ሰረገላ ነጭ ፈረሶች ነበሩት፤ አራተኛው ሰረገላ ዝንጉርጉር ፈረሶች ነበሩት። BSB BSB: the third white horses, and the fourth dappled horses—all of them strong.
4 ULB እኔም ከእኔ ጋር እየተነጋገረ የነበረውን መልአክ፣ “ጌታዬ ሆይ፣ እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልሁት። BSB BSB: So I inquired of the angel who was speaking with me, “What are these, my lord?”
5 ULB መልአኩም እንዲህ አለኝ’ “እነዚህ በምድር ሁሉ ጌታ ፊት ቆመው ከነበሩበት ቦታ የወጡ አራቱ የሰማይ ነፋሶች ናቸው!” አለኝ። BSB BSB: And the angel told me, “These are the four spirits of heaven, going forth from their station before the Lord of all the earth.
6 ULB ጥቁር ፈረሶች ያሉት ወደ ሰሜን፣ ነጭ ፈረሶች ያሉት ወደ ምዕራብ፣ ዝንጉርጉር ፈረሶች ያሉት ወደ ደቡብ ይሄዳሉ። BSB BSB: The one with the black horses is going toward the land of the north, the one with the white horses toward the west, and the one with the dappled horses toward the south.”
7 ULB ጠንካሮች ፈረሶች ሲወጡ፣ በምድር ሁሉ ፊት ለመመላለስ አቆብቁበው ነበር፤ ስለዚህም መልአኩ፣ “ወደ ምድር ሁሉ ሂዱ!” አላቸው። እነርሱም ወጥተው ወደ ምድር ሁሉ ሄዱ። BSB BSB: As the strong horses went out, they were eager to go and patrol the earth; and the LORD said, “Go and patrol the earth.” So they patrolled the earth.
8 ULB ከዚያም ወደ እኔ ጮኾ እንዲህ አለኝ፤ “ወደ ሰሜን እየሄዱ ያሉትን ተመልከት፣ መንፈሴን በሰሜን ምድር አሳርፈውታል።” BSB BSB: Then the LORD summoned me and said, “Behold, those going to the land of the north have given rest to My Spirit in the land of the north.”
9 ULB የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ BSB BSB: The word of the LORD also came to me, saying,
10 ULB ከምርኮኞቹ ከሔልዳይና፥ ከጦቢያ፣ ከዮዳኤም ወርቅና ብር ወስደህ በዚያው ቀን ከምርኮ ወደ መጣው ወደ ሶፎንያስ ልጅ ወደ ኢዮስያስ ቤት ሂድ። BSB BSB: “Take an offering from the exiles—from Heldai, Tobijah, and Jedaiah, who have arrived from Babylon—and go that same day to the house of Josiah son of Zephaniah.
11 ULB ወርቁንና ብሩን ወስደህ አክሊል ሥራ በኢዮሴዴቅ ልጅ በሊቀ ካህኑ ኢያሱ ራስ ላይ አድርገው። BSB BSB: Take silver and gold, make an ornate crown, and set it on the head of the high priest, Joshua son of Jehozadak.
12 ULB እንዲህም በለው፤ የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ እነሆ፣ ስሙ ቁጥቋጥ የተባለው ሰው ይህ ነው! እርሱም በቦታው ይንሰራፋል፤ የያህዌንም ቤተ መቅደስ ይሠራል! BSB BSB: And you are to tell him that this is what the LORD of Hosts says: ‘Here is a man whose name is the Branch, and He will branch out from His place and build the temple of the LORD.
13 ULB የያህዌን ቤተ መቅደስ የሚሠራው እርሱ ነው፤ ክብሩን ይጎናጸፋል፤ ከዚያም በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ይገዛል። በዙፋኑ ላይ ካህን ይሆናል፤ በሁለቱም መካከል ስምምነት ይኖራል። BSB BSB: Yes, He will build the temple of the LORD; He will be clothed in splendor and will sit on His throne and rule. And He will be a priest on His throne, and there will be peaceful counsel between the two.’
14 ULB ለሔልዳይና፣ ለጦቢያና ለዮዳኤ ክብር አክሊል ቤተ መቅደሱ ውስጥ ይቀመጣል፤ ለሶፎንያስ ልጅ ቸርነት መታሰቢያ ይሆናል። BSB BSB: The crown will reside in the temple of the LORD as a memorial to Helem, Tobijah, Jedaiah, and the gracious son of Zephaniah.
15 ULB ያኔ በሩቅ ያሉት መጥተው የያህዌን ቤተ መቅደስ ይሠራሉ፤ ወደ እናንተ የላከኝ ያህዌ እንደ ሆነም ታውቃላችሁ፤ የአምላካችሁን የያህዌን ድምፅ ከልባችሁ ብትሰሙ ይህ ይሆናል!” BSB BSB: Even those far away will come and build the temple of the LORD, and you will know that the LORD of Hosts has sent Me to you. This will happen if you diligently obey the voice of the LORD your God.”