1 ULB እንግዲህ ክፋትን፣ ማታለልን፣ ግብዝነትን፣ ቅናትንና ሐሜትን ሁሉ አስወግዱ። BSB BSB: Rid yourselves, therefore, of all malice, deceit, hypocrisy, envy, and slander.
2 ULB በድነታችሁ በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ንጹህ የሆነውን መንፈሳዊ ወተት ተመኙ፤ BSB BSB: Like newborn babies, crave pure spiritual milk, so that by it you may grow up in your salvation,
3 ULB ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ ከሆነ፣ BSB BSB: now that you have tasted that the Lord is good.
4 ULB በሰው ዘንድ ወደ ተናቀው፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ወደ ተመረጠውና ክቡር ወደ ሆነው ወደዚህ ሕያው ድንጋይ ቅረቡ። BSB BSB: As you come to Him, the living stone, rejected by men but chosen and precious in God’s sight,
5 ULB ደግሞም እንደ ሕያዋን ድንጋዮች፣ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕት የሚያቀርቡ ቅዱሳን ካህናት ትሆኑ ዘንድ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ትሠራላችሁ። BSB BSB: you also, like living stones, are being built into a spiritual house to be a holy priesthood, offering spiritual sacrifices acceptable to God through Jesus Christ.
6 ULB በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈው «እነሆ፤ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም»። BSB BSB: For it stands in Scripture: “See, I lay in Zion a stone, a chosen and precious cornerstone; and the one who believes in Him will never be put to shame.”
7 ULB እንግዲህ ለምታምኑት ለእናንተ እርሱ ክቡር ነው፤ ለማያምኑት ግን፣«ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣ እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ» BSB BSB: To you who believe, then, this stone is precious. But to those who do not believe, “The stone the builders rejected has become the cornerstone,”
8 ULB እንደዚሁም ደግሞ «ሰዎችን የሚያሰናክልና የሚጥላቸውም ዐለት ሆነ»። የሚሰናከሉት ቃሉን ባለመታዘዛቸው ነው፤ የተመደቡት ለዚህ ነውና። BSB BSB: and, “A stone of stumbling and a rock of offense.” They stumble because they disobey the word—and to this they were appointed.
9 ULB እናንተ ግን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ እንድታውጁ፣ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉሥ ካህናት፣ ቅዱስ ሕዝብ፣ እግዚአብሔር የራሱ ያደረጋችሁ ሕዝብ ናችሁ። BSB BSB: But you are a chosen people, a royal priesthood, a holy nation, a people for God’s own possession, to proclaim the virtues of Him who called you out of darkness into His marvelous light.
11 ULB ወዳጆች ሆይ፤ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ መጠን፣ ነፍሳችሁን ከሚዋጉ ከኅጢኣት ምኞቶች እንድትርቁ እለምናችኋለሁ። BSB BSB: Beloved, I urge you, as foreigners and exiles, to abstain from the desires of the flesh, which war against your soul.
12 ULB ክፉ እንደምትሠሩ አድርገው ቢያሟችሁም፣ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ መልካሙን ሥራችሁን አይተው እግዚአብሔርን እንዲያከብሩ፣ በአሕዛብ መካከል አኗኗራችሁ መልካም መሆን አለበት። BSB BSB: Conduct yourselves with such honor among the Gentiles that, though they slander you as evildoers, they may see your good deeds and glorify God on the day He visits us.
13 ULB ስለ ጌታ ብላችሁ ለምድራዊ ባለ ሥልጣን ሁሉ ታዘዙ፤ BSB BSB: Submit yourselves for the Lord’s sake to every human institution, whether to the king as the supreme authority,
14 ULB የበላይ ባለ ሥልጣን ስለ ሆነ ለንጉሥ ቢሆን፣ ወይም ክፉ አድራጊዎችን ለመቅጣት፣ በጎ አድራጊዎችን ለማመስገን እርሱ ለሾማቸው ገዦች ታዘዙ፤ BSB BSB: or to governors as those sent by him to punish those who do wrong and to praise those who do right.
15 ULB ምክንያቱም፣ መልካም በማድረግ የአላዋቂዎችን ከንቱ ንግግር ዝም እንድታሰኙ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። BSB BSB: For it is God’s will that by doing good you should silence the ignorance of foolish men.
16 ULB እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ሆናችሁ በነጻነት ኑሩ እንጂ ነጻነታችሁን የክፋት መሸፈኛ አታድርጉት። BSB BSB: Live in freedom, but do not use your freedom as a cover-up for evil; live as servants of God.
17 ULB ለሰው ሁሉ ተገቢውን አክብሮት ስጡ፤ ወንድሞችን ውደዱ፤ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ንጉሥን አክብሩ። BSB BSB: Treat everyone with high regard: Love the brotherhood of believers, fear God, honor the king.
18 ULB እናንተ አገልጋዮች፤ ለመልካሞችና ለገሮች ጌቶቻችሁ ብቻ ሳይሆን ለክፉዎችም በፍጹም አክብሮት ታዘዙ። BSB BSB: Servants, submit yourselves to your masters with all respect, not only to those who are good and gentle, but even to those who are unreasonable.
19 ULB ስለ እግዚአብሔር ሲል የግፍ መከራን የሚቀበል ሰው ምስጋናን ያገኛል። BSB BSB: For if anyone endures the pain of unjust suffering because he is conscious of God, this is to be commended.
20 ULB ክፉ ሥራ ሠርታችሁ ስትቀጡ ብትታገሡ ምን ያስመሰግናችኋል? ነገር ግን መልካም ሥራ ሠርታችሁ መከራ ስትቀበሉ ብትታገሡ ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ ያስመሰግናችኋል። BSB BSB: How is it to your credit if you are beaten for doing wrong and you endure it? But if you suffer for doing good and you endure it, this is commendable before God.
21 ULB የተጠራችሁት ለዚህ ነው፤ ክርስቶስ ስለ እናንተ መከራን የተቀበለው የእርሱን ፈለግ እንድትከተሉ ምሳሌ ሊተውላችሁ ነው። BSB BSB: For to this you were called, because Christ also suffered for you, leaving you an example, that you should follow in His footsteps:
23 ULB ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራንም ሲቀበል አልዛተም፤ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤ BSB BSB: When they heaped abuse on Him, He did not retaliate; when He suffered, He made no threats, but entrusted Himself to Him who judges justly.
24 ULB ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በመስቀል ላይ ተሸከመ፤ በእርሱ ቊስል እናንተ ተፈውሳችኋል። BSB BSB: He Himself bore our sins in His body on the tree, so that we might die to sin and live to righteousness. “By His stripes you are healed.”
25 ULB ቀድሞ ሁላችሁም እንደ ጠፉ በጎች ትቅበዘበዙ ነበር፤ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል። BSB BSB: For “you were like sheep going astray,” but now you have returned to the Shepherd and Overseer of your souls.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.