1 ULB ሚስቶች ሆይ፤ እናንተም እንደዚሁ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤ አንዳንድ ለቃሉ የማይታዘዙ ቢኖሩ እንኳ፣ ሚስቶቻቸው ቃል ሳይናገሩ በመልካም አኗኗራቸው ሊማርኳቸው ይችላሉ፤ BSB BSB: Wives, in the same way, submit yourselves to your husbands, so that even if they refuse to believe the word, they will be won over without words by the behavior of their wives
2 ULB ይህም የሚሆነው ለእነርሱ ያላችሁን አክብሮት በንጹሕ አኗኗራችሁ ሲመለከቱ ነው። BSB BSB: when they see your pure and reverent demeanor.
3 ULB ውበታችሁ በውጫዊ ነገሮች በመሽሞንሞን ይኸውም ሹሩባ በመሠራት፣ በወርቅ በመንቆጥቆጥ ወይም ጌጠኛ ልብስ በመልበስ አይሁን፤ BSB BSB: Your beauty should not come from outward adornment, such as braided hair or gold jewelry or fine clothes,
4 ULB ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት የከበረ፣ ገርና ጭምት መንፈስ ያለበት፣ ምንጊዜም የማይጠፋ የውስጥ ሰውነት ውበት ይሁን። BSB BSB: but from the inner disposition of your heart, the unfading beauty of a gentle and quiet spirit, which is precious in God’s sight.
5 ULB የቀድሞ ቅዱሳት ሴቶች የተዋቡት በዚህ ዐይነት ነበር፤ እነርሱ በእግዚአብሔር የሚደገፉና ለባሎቻቸ የሚታዘዙ ነበሩ። BSB BSB: For this is how the holy women of the past adorned themselves. They put their hope in God and were submissive to their husbands,
6 ULB ሣራም እንደዚሁ አብርሃምን «ጌታዬ» እያለች ትታዘዘው ነበር፣ እናንተም መከራን ሳትፈሩ መልካም ብታደርጉ፣ አሁን የእርሷ ልጆች ናችሁ። BSB BSB: just as Sarah obeyed Abraham and called him lord. And you are her children if you do what is right and refuse to give way to fear.
7 ULB እንዲሁም ባሎች ሆይ፤ ሚስቶቻችሁ ደካማ አጋር መሆናቸውን ዐውቃችሁ፣ የሕይወትን ጸጋ ከእናንተ ጋር አብረው የሚካፈሉ መሆናቸውንም ተገንዝባችሁ አብራችኋቸው ኑሩ። ጸሎታችሁ እንዳይከለከል ይህን አድርጉ። BSB BSB: Husbands, in the same way, treat your wives with consideration as a delicate vessel, and with honor as fellow heirs of the gracious gift of life, so that your prayers will not be hindered.
8 ULB በመጨረሻም፣ ሁላችሁ በአንድ ሐሳብ ተስማሙ፤ ተዛዘኑ፤ እንደ ወንድማማቾች ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ። BSB BSB: Finally, all of you, be like-minded and sympathetic, love as brothers, be tenderhearted and humble.
9 ULB ክፉን በክፉ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ፤ ምክንያቱም እናንተ የተጠራችሁት በረከትን ለመውረስ ነው። BSB BSB: Do not repay evil with evil or insult with insult, but with blessing, because to this you were called so that you may inherit a blessing.
10 ULB ስለዚህ «ሕይወትን የሚወድና መልካም ቀኖችን ሊያይ የሚፈልግ ምላሱን ከክፉ፣ ከንፈሮቹንም ተንኰል ከመናገር ይከልክል። BSB BSB: For, “Whoever would love life and see good days must keep his tongue from evil and his lips from deceitful speech.
11 ULB ከክፉ ይራቅ፤ መልካምንም ያድርግ፤ ሰላምን ይፈልግ፤ ይከተላትም። BSB BSB: He must turn from evil and do good; he must seek peace and pursue it.
12 ULB የጌታ ዐይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉና፤ ጆሮቹም ጸሎታቸውን ለመስማት የተከፈቱ ናቸው፤ የጌታ ፊት ግን በክፉ አድራጊዎች ላይ ነው።» BSB BSB: For the eyes of the Lord are on the righteous, and His ears are inclined to their prayer. But the face of the Lord is against those who do evil.”
13 ULB መልካም ነገር ለማድረግ ብትቀኑ የሚጐዳችሁ ማን ነው? BSB BSB: Who can harm you if you are zealous for what is good?
14 ULB ነገር ግን በጽድቅ ምክንያት መከራ ቢደርስባችሁ ቡሩካን ናችሁ፤ ዛቻቸውን አትፍሩ፤ አትታወኩም። BSB BSB: But even if you should suffer for what is right, you are blessed. “Do not fear what they fear; do not be shaken.”
16 ULB በክርስቶስ ያላችሁን መልካም አናናራችሁን የሚያክፋፉ ሰዎች በሐሜታቸው እንዲያፍሩ በጎ ኅሊና ይኑራችሁ። BSB BSB: keeping a clear conscience, so that those who slander you may be put to shame by your good behavior in Christ.
17 ULB እግዚአብሔር የሚፈልገው ይህን ከሆነ፣ ክፉ ሠርቶ መከራ ከመቀበል ይልቅ መልካም አድርጎ መከራ መቀበል ይሻላል፤ BSB BSB: For it is better, if it is God’s will, to suffer for doing good than for doing evil.
18 ULB እንዲሁም ክርስቶስ አንድ ጊዜ ስለ ኀጢአታችን ሞቷል። ወደ እግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ፣ ጻድቅ የሆነው እርሱ ስለ እኛ ስለ ዐመፀኞች ሞተ፤ እርሱ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፤ BSB BSB: For Christ also suffered for sins once for all, the righteous for the unrighteous, to bring you to God. He was put to death in the body but made alive in the Spirit,
21 ULB ይህም ውሃ አሁን እናንተን የሚያድነው የጥምቀት ምሳሌ ነው፤ ይህ ጥምቀት የሰውነትን ዕድፍ ማስወገድ ሳይሆን ንጹሕ ኅሊናን ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ልመና ነው፤ የሚያድናችሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ አማካይነት ነው፤ BSB BSB: And this water symbolizes the baptism that now saves you also—not the removal of dirt from the body, but the pledge of a clear conscience toward God—through the resurrection of Jesus Christ,
22 ULB እርሱ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ አለ፤ መላእክት፣ ሥልጣናትና ኀይላትም ተገዝተውለታል። BSB BSB: who has gone into heaven and is at the right hand of God, with angels, authorities, and powers subject to Him.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.