1 ULB አካዝ በይሁዳ በነገሠ በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በእስራኤል ንጉሥ ሆነ፡፡ እርሱም በሰማርያ ዘጠኝ ዓመት እስራኤልን ገዛ፡፡ BSB BSB: In the twelfth year of the reign of Ahaz over Judah, Hoshea son of Elah became king of Israel, and he reigned in Samaria nine years.
2 ULB እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ፡፡ ሆኖም እርሱ ያደረገው ኃጢአት ከእርሱ በፊት የነበሩ የእስራኤል ነገሥታት የፈጸሙት አልነበረም፡፡ BSB BSB: And he did evil in the sight of the LORD, but not like the kings of Israel who preceded him.
3 ULB የአሦር ንጉሥ ስልምናሶር ጦርነት በገጠመው ጊዜ ተሸንፎ ሆሴዕ እጁን በመስጠት በየዓመቱ ይገብርለት ጀመር፡፡ BSB BSB: Shalmaneser king of Assyria attacked him, and Hoshea became his vassal and paid him tribute.
4 ULB ነገር ግን ከጥቂት ዓመቶች በኋላ ንጉሥ ሆሴዕ ሴጎር ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ግብጽ ንጉሥ መልእክተኞች በመላክ ይረዳው ዘንድ ጠየቀው፤ በየዓመቱ ለአሦር ንጉሥ ይሰጠው የነበረውንም ግብር አቆመ፡፡ ስልምናሶር ይህን በሰማ ጊዜ ሆሴዕን አስይዞ ወህኒ ቤት አስገባው፡፡ BSB BSB: But the king of Assyria discovered that Hoshea had conspired to send envoys to King So of Egypt, and that he had not paid tribute to the king of Assyria as in previous years. Therefore the king of Assyria arrested Hoshea and put him in prison.
5 ULB ከዚህ በኋላ ስልምናሶር አገሪቱን ወርሮ ሰማርያን ለሦስት ዓመት ከበባት፡፡ BSB BSB: Then the king of Assyria invaded the whole land, marched up to Samaria, and besieged it for three years.
7 ULB ይህም ምርኮ የሆነው እስራኤላውያን በሠሩት ኃጢአት ከግብጽ ንጉሥ ከፈርዖን እጅ በመታደግ አውጥቶ ወደ ተስፋይቱ ምድር የመራቸውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን ኃጢአት በመሥራት በማሳዘናቸው ነበር፡፡ ሕዝቡም ባዕዳን አማልክትን አመለኩ፡፡ BSB BSB: All this happened because the people of Israel had sinned against the LORD their God, who had brought them out of the land of Egypt from under the hand of Pharaoh king of Egypt. They had worshiped other gods
8 ULB ሕዝቡም ከፊታቸው ያጠፋላቸውን የአሕዛብን መጥፎ ልማድ ተከተሉ፤ እንዲሁም የእስራኤል ነገሥታት ያሠራጩትን መጥፎ ልማድ ተቀባዮች ሆኑ፡፡ BSB BSB: and walked in the customs of the nations that the LORD had driven out before the Israelites, as well as in the practices introduced by the kings of Israel.
9 ULB እስራኤላውያንም አምላካቸው እግዚአብሔር የሚጠላውን ነገር ሁሉ አደረጉ፡፡ ከዘብ ጠባቂዎች ማማ አንሥቶ እስከ ትልቅ ከተማ ድረስ በገጠር ከተሞቻቸው ሁሉ በየኮረብታዎቹ የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችን ሠሩ፡፡ BSB BSB: The Israelites secretly did things against the LORD their God that were not right. From watchtower to fortified city, they built high places in all their cities.
10 ULB በኮረብቶች ሁሉ ላይና በየዛፉ ጥላ ሥር የድንጋይ አምዶችንና አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስሎች አቆሙ፡፡ BSB BSB: They set up for themselves sacred pillars and Asherah poles on every high hill and under every green tree.
11 ULB እግዚአብሔርም ከፊታቸው ያስወጣቸውን የአረማውያን ሕዝብ ልማድ በመከተል በአሕዛብ መሠዊያዎች ሁሉ ላይ ዕጣን አጠኑ፤ በዚህም ክፉ ሥራቸው ሁሉ የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሡ፤ BSB BSB: They burned incense on all the high places like the nations that the LORD had driven out before them. They did wicked things, provoking the LORD to anger.
12 ULB እግዚአብሔርም እንዳያደርጉ የተናገራቸውን ጣዖታትን አመለኩ፡፡ BSB BSB: They served idols, although the LORD had told them, “You shall not do this thing.”
13 ULB እግዚአብሔርም እስራኤልንና ይሁዳን የሚያስጠነቅቁ መልእክተኞችንና ነቢያትን በመላክ፣ ከክፉ መንገዳችሁ ሁሉ ተመለሱ፤ አገልጋዮቼ በሆኑት ነቢያትና ባለ ራዕዮች አማካይነት ለቀድሞ አባቶቻችሁና ለእናንተም በሰጠሁት ሕጎችና ትእዛዞች የተጻፈውን ሥርዓቱን ጠብቁ ብሎ ነግሮአቸው ነበር፡፡ BSB BSB: Yet through all His prophets and seers, the LORD warned Israel and Judah, saying, “Turn from your wicked ways and keep My commandments and statutes, according to the entire Law that I commanded your fathers and delivered to you through My servants the prophets.”
14 ULB እነርሱ ግን መታዘዝ አልፈለጉም፤ በአምላካቸው በእግዚአብሔር እንዳልታመኑ እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው እልከኞች ሆኑ፡፡ BSB BSB: But they would not listen, and they stiffened their necks like their fathers, who did not believe the LORD their God.
15 ULB የሰጣቸውንም ድንጋጌ አልተቀበሉም፤ ከቀድሞ አባቶቻቸው ጋር የገባውንም ቃል ኪዳን አልጠበቁም፤ የሰጣቸውንም ማስጠንቀቂያዎች ሁሉ ቸል አሉ፤ ለከንቱ ጣዖቶች በመስገድ ራሳቸውም ከንቱዎች ሆኑ፤ የእነርሱን መጥፎ ምሰሌነት እንዳይወርሱ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ትእዛዝ ባለመስማት በዙሪያቸው የሚኖሩትን የአሕዛብ ልማድ ሁሉ ተከተሉ፡፡ BSB BSB: They rejected His statutes and the covenant He had made with their fathers, as well as the decrees He had given them. They pursued worthless idols and became worthless themselves, going after the surrounding nations that the LORD had commanded them not to imitate.
16 ULB የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ሁሉ ቸል አሉ፡፡ የሚሰግዱላቸውን ከብረት የተሠሩ ሁለት ጥጆችን አቆሙ፡፡ እንዲሁም አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስል ሠሩ፣ ለከዋክብትም ሰገዱ፣ ባዓል ተብሎ ለሚጠራውም ባዕድ አምላክ አገልጋዮች ሆኑ፡፡ BSB BSB: They abandoned all the commandments of the LORD their God and made for themselves two cast idols of calves and an Asherah pole. They bowed down to all the host of heaven and served Baal.
17 ULB ለእነዚያም አሕዛብ አማልክት ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ፤ ከሙታን ጠሪዎችና ከጠንቋዮችም ምክር ጠየቁ፤ እግዚአብሔር ለሚጠላው ክፉ ነገር ሁሉ ራሳቸውን አሳልፈው በመስጠት የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሡ፡፡ BSB BSB: They sacrificed their sons and daughters in the fire and practiced divination and soothsaying. They devoted themselves to doing evil in the sight of the LORD, provoking Him to anger.
18 ULB ስለዚሀም እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ተቆጥቶ የይሁዳን መንግሥት ብቻ በማስቀረት እስራኤላውያንን ከፊቱ አስወገደ፡፡ BSB BSB: So the LORD was very angry with Israel, and He removed them from His presence. Only the tribe of Judah remained,
19 ULB የይሁዳ ሰዎችም ቢሆኑ አምላካቸው እግዚአብሔር የሰጣቸውን ትእዛዞች አልጠበቁም ነበር፡፡ እነርሱም የእስራኤል ሕዝብ የተቀበሉትን ልማድ ተከታዮች ነበሩ፡፡ BSB BSB: and even Judah did not keep the commandments of the LORD their God, but lived according to the customs Israel had introduced.
20 ULB ስለዚህም እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ሁሉ ተዋቸው፤ ከፊቱም እስኪወገዱ ድረስ ለጠላቶቻቸው አሳልፎ በመስጠት ቀጣቸው፡፡ BSB BSB: So the LORD rejected all the descendants of Israel. He afflicted them and delivered them into the hands of plunderers, until He had banished them from His presence.
21 ULB እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከይሁዳ ከለየ በኋላ እስራኤላውያን የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓምን መርጠው አነገሡ፤ ኢዮርብዓምም እግዚአብሔርን እንዲተዉ በማድረግ አሠቃቂ ወደ ሆነ ኃጢአት መራቸው፡፡ BSB BSB: When the LORD had torn Israel away from the house of David, they made Jeroboam son of Nebat king, and Jeroboam led Israel away from following the LORD and caused them to commit a great sin.
22 ULB በአገልጋዮቹ ነቢያት ሁሉ አማካይነት እግዚአብሔር እስራኤልን ከፊቱ እስኪያስወግድ ድረስ እስራኤላውያን የኢዮርብዓምን ኃጢአት ሲሠሩ ኖሩ እንጂ ከዚያ አልራቁም፡፡ BSB BSB: The Israelites persisted in all the sins that Jeroboam had committed and did not turn away from them.
23 ULB ስለዚህ እስራኤላውያን ከአገራቸው ተማርከው በመወሰድ እስከ ዛሬ ድስ በአሦር ይኖራሉ፡፡ BSB BSB: Finally, the LORD removed Israel from His presence, as He had declared through all His servants the prophets. So Israel was exiled from their homeland into Assyria, where they are to this day.
24 ULB የአሦር ንጉሠ ነገሥት በባቢሎን ኩታ፣ ዓዋና፣ ሐማትና ሴፈርዋይ ተብለው በሚጠሩት ከተሞች ይኖሩ የነበሩትን አሕዛብ አምጥቶ ተሰደው በሄዱት በእስራኤላውያን እግር በመተካት በሰማርያ ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ፤ እነርሱም እነዚህን ከተሞች ወርሰው በዚያ መኖር ጀመሩ፡፡ BSB BSB: Then the king of Assyria brought people from Babylon, Cuthah, Avva, Hamath, and Sepharvaim and settled them in the towns of Samaria to replace the Israelites. They took possession of Samaria and lived in its towns.
25 ULB እነርሱም በዚያ ሰፍረው መኖር እንደ ጀመሩ እግዚአብሔርን አላመለኩትም ነበር፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር አንበሶችን በመላክ ከእነርሱ ጥቂቶቹን ሰባብረው እንዲገድሉ አደረገ፡፡ BSB BSB: Now when the settlers first lived there, they did not worship the LORD, so He sent lions among them, which killed some of them.
26 ULB ለአሦርም ንጉሠ ነገሥት በሰማርያ ከተሞች ሰፍረው እንዲኖሩ ያደረግሃቸው ሕዝቦች የዚያችን አገር አምላክ ሕግ የሚያውቁ ሆነው አልተገኙም፤ ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ሰባብረው የሚገድሉ አንበሶችን ላከባቸው የሚል ወሬ ደረሰው፡፡ BSB BSB: So they spoke to the king of Assyria, saying, “The peoples that you have removed and placed in the cities of Samaria do not know the requirements of the God of the land. Because of this, He has sent lions among them, which are indeed killing them off.”
27 ULB ስለዚህ ንጉሠ ነገሥቱ ማርኮ ካመጣቸው ካህናት አንዱን ወደዚያ ላኩ፤ ወደዚያ ተመልሶ በመሄድ የዚያች አገር አምላክ ያዘዘውን ሕግ ለሕዝቡ እንዲያስተምራቸው አድርጉ ሲል አዘዘ፡፡ BSB BSB: Then the king of Assyria commanded: “Send back one of the priests you carried off from Samaria, and have him go back to live there and teach the requirements of the God of the land.”
28 ULB ስለዚህም ከሰማርያ ተማርኮ የተወሰደ አንድ እስራኤላዊ ካህን ተመልሶ በመሄድ በቤተል ተቀመጠ፤ በዚያ ሕዝቡ እግዚአብሔርን እንዴት ማምለክ እንደሚገባቸው አስተማራቸው፡፡ BSB BSB: Thus one of the priests they had carried away came and lived in Bethel, and he began to teach them how they should worship the LORD.
29 ULB በሰማርያ የሰፈሩት ሕዝቦች ግን የየራሳቸውን ጣዖት መሥራት ቀጥለው እስራኤላውያን ባሠሩአቸው በከፍተኛ ማምለኪያ ቦታዎች አኖሩአቸው፤ እያንዳንዱ ቡድን በሚኖርበት ከተማ ሁሉ የየራሱን ጣዖት አቆመ፡፡ BSB BSB: Nevertheless, the people of each nation continued to make their own gods in the cities where they had settled, and they set them up in the shrines that the people of Samaria had made on the high places.
30 ULB በዚህም ዓይነት የባቢሎን ሰዎች ሱኮትበኖት በተባለው አምላክ ስም ጣዖት ሠሩ፤ እንዲሁም የኩታ ሰዎች ኤርጌል ተብሎ በሚጠራው ባዕድ አምላክ ስም ጣዖት ሠሩ፤ የሐማት ሕዝብ አሲማት ተብሎ በሚጠራው ባዕድ አምላክ ስም ጣዖት ሠሩ፤ BSB BSB: The men of Babylon made Succoth-benoth, the men of Cuth made Nergal, the men of Hamath made Ashima,
31 ULB የዓዋ ሕዝብ ኤልባዝርና ተርታቅ ተብለው በሚጠሩ አማልክቶቻቸው ስም ጣዖቶቻቸውን ሠሩ፤ የሴፈርዋይምም ሕዝብ አድራሜሌክና ዓናሜሌክ ተብለው ለሚጠሩ አማልክቶቻቸው ልጆቻቸውን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ፡፡ BSB BSB: the Avvites made Nibhaz and Tartak, and the Sepharvites burned their children in the fire to Adrammelech and Anammelech the gods of Sepharvaim.
32 ULB እነዚሁ ሰዎች በተጨማሪ ለእውነተኛው አምላክ ለእግዚአብሔር ይሰግዱ ነበር፡፡ ከእያንዳዳቸውም ቡድን በአረማውያን የማምለኪያ ስፍራዎች የሚያገለግሉና መሥዋዕት የሚያቀርቡላቸውን ካህናት መረጡ፡፡ BSB BSB: So the new residents worshiped the LORD, but they also appointed for themselves priests of all sorts to serve in the shrines of the high places.
33 ULB በዚህ ዓይነት እግዚአብሔርን ማክበርና ማምለክ ጀመሩ፡፡ በሌላ በኩል ግን ቀድሞ ይኖሩባቸው በነበሩት ሕዝቦች ይፈጽሙት በነበረው ልማድ መሠረት ለባዕዳን አማልክት ይሰግዱ ነበር፡፡ BSB BSB: They worshiped the LORD, but they also served their own gods according to the customs of the nations from which they had been carried away.
34 ULB ይህንኑ አሮጌ ልማዳቸውን እስከ አሁን ድረስ በመፈጸም ላይ ናቸው፡፡ እነርሱም እግዚአብሔርን አያመልኩም ወይም ስሙ እስራኤል ተብሎ ለተጠራው ለያዕቆብ ልጆች እግዚአብሔር በሰጣቸው ደንቦች፣ ሥርዓቶች፣ ሕጎችና ትእዛዞች ጸንተው አልኖሩም፡፡ BSB BSB: To this day they are still practicing their former customs. None of them worship the LORD or observe the statutes, ordinances, laws, and commandments that the LORD gave the descendants of Jacob, whom He named Israel.
35 ULB እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን በመግባት እስራኤላውያንን እንዲህ ሲል አዞአቸው ነበር፡- ባዕዳን አማልክትን አታምልኩ፣ ለእነርሱም አገልጋዮች በመሆን አትስገዱላቸው፣ መሥዋዕትንም አታቅርቡላቸው፡፡ BSB BSB: For the LORD had made a covenant with the Israelites and commanded them, “Do not worship other gods or bow down to them; do not serve them or sacrifice to them.
36 ULB በታላቅ ኃይልና በሥልጣን ከግብጽ ምድር ላወጣኋችሁ ለእኔ ለእግዚአብሔር ታዛዦች ሁኑ፤ መስገድና መሥዋዕት ማቅረብ የሚገባችሁ ለእኔ ብቻ ነው፡፡ BSB BSB: Instead, worship the LORD, who brought you out of the land of Egypt with great power and an outstretched arm. You are to bow down to Him and offer sacrifices to Him.
37 ULB ጽፌ የሰጠኋችሁንም ድንጋጌና ሥርዓቱን ሕጎችና ትእዛዞቹን ሁልጊዜ ጠብቁ፣ ባዕዳን አማልክትንም አትከተሉ፡፡ BSB BSB: And you must always be careful to observe the statutes, ordinances, laws, and commandments He wrote for you. Do not worship other gods.
38 ULB እኔ ከእናንተ ጋር የገባሁትንም ቃል ኪዳን አትርሱ፤ ባዕዳን አማልክትንም አታምልኩ፡፡ BSB BSB: Do not forget the covenant I have made with you. Do not worship other gods,
39 ULB እኔን አምላካችሁን እግዚአብሔርን ፍሩ፤ እኔም ከኃይለኛው ጠላቶቻችሁ እጅ አድናችኋለሁ፡፡ BSB BSB: but worship the LORD your God, and He will deliver you from the hands of all your enemies.”
40 ULB ነገር ግን እነዚያ ሕዝቦች ይህን መስማት ትተው አሮጌ ልማዳቸውን ተከተሉ፡፡ BSB BSB: But they would not listen, and they persisted in their former customs.
41 ULB እነዚያ ሕዝቦች በዚሁ ዓይነት እግዚአብሔርን ማምለክ ጀመሩ፤ በሌላ በኩል ግን ለጣዖቶቻቸው ይሰግዱ ነበር፤ ዘሮቻቸውም እስከ ዛሬ ድረስ ይህንኑ ዓይነት አምልኮ እንደ ቀጠሉ ናቸው፡፡ BSB BSB: So these nations worshiped the LORD but also served their idols, and to this day their children and grandchildren continue to do as their fathers did.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.