1 ULB ሳዖል ከሞተ በኋላ፣ ዳዊት በአማሌቃውያን ላይ ጥቃት ከማድረስ በመመለስ በጺቅላግ ሁለት ቀን ቆየ፡፡ BSB BSB: After the death of Saul, David returned from the slaughter of the Amalekites and stayed in Ziklag two days.
2 ULB በሦስተኛው ቀን የተቀዳደደ ልብስ የለበሰ፣ በራሱም ላይ ትቢያ የነሰነሰ አንድ ሰው ከሳኦል ሰፈር መጣ፡፡ ወደ ዳዊት እንደ ደረሰም ወደ መሬት ለጥ ብሎ ሰገደለት፡፡ BSB BSB: On the third day a man with torn clothes and dust on his head arrived from Saul’s camp. When he came to David, he fell to the ground to pay him homage.
3 ULB ዳዊትም “ከወዴት መጣህ?” ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም፣ “ከእስራኤላውያን ሰፈር አምልጬ የመጣሁ ነኝ” ሲል መለሰ፡፡ BSB BSB: “Where have you come from?” David asked. “I have escaped from the Israelite camp,” he replied.
4 ULB ዳዊትም፣ “እስቲ የሆነውን ሁሉ ንገረኝ” አለው፡፡ እርሱም “ሰዎቹ ከጦርነት ሸሽተዋል፤ ብዙዎቹ ወድቀዋል ደግሞም ሞተዋል፤ ሳዖልና ልጁ ዮናታንም ሞተዋል” አለ፡፡ BSB BSB: “What was the outcome?” David asked. “Please tell me.” “The troops fled from the battle,” he replied. “Many of them fell and died. And Saul and his son Jonathan are also dead.”
5 ULB ዳዊትም ለወጣቱ፤ “ሳኦልና ልጁ ዮናታን መሞታቸውን እንዴት አወቅህ?” ሲል ጠየቀው፡፡ BSB BSB: Then David asked the young man who had brought him the report, “How do you know that Saul and his son Jonathan are dead?”
6 ULB ወጣቱም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ድንገት ወደ ጊልቦዓ ተራራ ወጥቼ ነበር፤ እዚያም ሳኦል ጦሩን ተደግፎ ሳለ፣ ሠረገሎችና ፈረሰኞች ተከታትለው ደረሱበት፤ BSB BSB: “I happened to be on Mount Gilboa,” he replied, “and there was Saul, leaning on his spear, with the chariots and the cavalry closing in on him.
7 ULB ወደ ኋላውም ዞር ሲል እኔን ስላየ ጠራኝ፤ እኔም ‘እነሆኝ አለሁ’ አልኩት፡፡ BSB BSB: When he turned around and saw me, he called out to me, and I answered, ‘Here I am!’
8 ULB እርሱም፣ ‘አንተ ማን ነህ?’ ሲል ጠየቀኝ፡፡ አኔም፣ ‘አማሌቃዊ ነኝ’ ብዬ መለስሁለት፡፡ BSB BSB: ‘Who are you?’ he asked. So I told him, ‘I am an Amalekite.’
9 ULB እርሱም አለኝ ‘እኔ በታላቅ ስቃይ ውስጥ እገኛለሁ፤ ነፍሴ ግን አልወጣችም፤ እባክህ በላዬ ቆመህ ግደለኝ’ አለኝ፡፡ BSB BSB: Then he begged me, ‘Stand over me and kill me, for agony has seized me, but my life still lingers.’
10 ULB ስለሆነም፣ ከወደቀ በኋላ እንደማይተርፍ ስላወቅሁ፤ በላዩ ቆሜ ገደልሁት፤ በራሱ ላይ የነበረውን ዘውድና የክንዱን አንባር ወስጄ እነሆ፣ ለጌታዬ አምጥቻለሁ፡፡” አለው፡፡ BSB BSB: So I stood over him and killed him, because I knew that after he had fallen he could not survive. And I took the crown that was on his head and the band that was on his arm, and I have brought them here to my lord.”
11 ULB ከዚያም ዳዊት ልብሱን ቀደደ፤ ከእርሱም ጋር የነበሩት ሁሉ እንደዚሁ አደረጉ፡፡ BSB BSB: Then David took hold of his own clothes and tore them, and all the men who were with him did the same.
12 ULB የወደቁት በሰይፍ ነበርና ለሳኦል ለልጁ ለዮናታንና ለእግዚአብሔር ሕዝብ አዘኑ፤ አለቀሱ፤ እስከ ማታም ድረስ ጾ፡፡ BSB BSB: They mourned and wept and fasted until evening for Saul and his son Jonathan, and for the people of the LORD and the house of Israel, because they had fallen by the sword.
13 ULB ዳዊትም ወጣቱን ሰውዬ፣ “የየት አገር ሰው ነህ?” ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም፣ “በአገሪቱ ውስጥ በመጻተኛነት የሚኖር አማሌቃዊ ልጅ ነኝ” ብሎ መለሰ፡፡ BSB BSB: And David inquired of the young man who had brought him the report, “Where are you from?” “I am the son of a foreigner,” he answered. “I am an Amalekite.”
14 ULB ዳዊትም፣ “እግዚአብሔር የቀባውን ንጉሥ በገዛ እጅህ ስትገድል ለምን አልፈራህም?” ሲል ጠየቀው፡፡ BSB BSB: So David asked him, “Why were you not afraid to lift your hand to destroy the LORD’s anointed?”
15 ULB ዳዊትም ከጎልማሶቹ አንዱን ጠርቶ፣ “ግደለው” አለው፤ ጎልማሳው ሰው ሄዶ መታው፣ አማሌቃዊውም ሞተ፡፡ BSB BSB: Then David summoned one of the young men and said, “Go, execute him!” So the young man struck him down, and he died.
16 ULB ከዚያም ዳዊት ለሞተው አማሌቃዊ፣ “‘እግዚአብሔር የቀባውን ገድያለሁ’ ስትል አፍህ መስክሮብሃልና ደምህ በራስህ ላይ ነው” አለው፡፡ BSB BSB: For David had said to the Amalekite, “Your blood be on your own head because your own mouth has testified against you, saying, ‘I killed the LORD’s anointed.’”
17 ULB ከዚያም ዳዊት ለሳዖልና ለልጁ ለዮናታን የሚከተለውን የሐዘን እንጉርጉሮ አንጎራጎረ፡፡ BSB BSB: Then David took up this lament for Saul and his son Jonathan,
18 ULB እንዲሁም የቀስት እንጉርጉሮ የተባለውን ለይሁዳ ሕዝብ እንዲያስተምሩ አዘዘ፤ ይህም በያሸር መጽሐፍ ተጽፎአል፡፡ BSB BSB: and he ordered that the sons of Judah be taught the Song of the Bow. It is written in the Book of Jashar:
19 ULB “እስራኤል ሆይ፣ ክብርህ ሞቶአል፣ በተራሮችህ ላይ ተገድሎአል! ኃያላኑ እንዴት ወደቁ! BSB BSB: “Your glory, O Israel, lies slain on your heights. How the mighty have fallen!
20 ULB የፍልስጥኤም ሴቶች ልጆች እንዳይደሰቱ፣ ያልተገረዙት ሴት ልጆች ፌሽታ እንዳያደርጉ ይህን በጌት አትናገሩ፣ በአስቆሎናም መንገዶች አታውጁት፡፡ BSB BSB: Tell it not in Gath; proclaim it not in the streets of Ashkelon, lest the daughters of the Philistines rejoice, and the daughters of the uncircumcised exult.
21 ULB እናንት የጊልቦዓ ተራሮች ሆይ ጠል አያረስርሳችሁ፣ ዝናብም አይውረድባችሁ፤ የቁርባን እህል የሚያበቅሉም እርሻዎች በዚያ አይኑሩ፤ በዚያ የኃያሉ ሰው ጋሻ ረክሶአልና፣ የሳዖል ጋሻ ከእንግዲህ በዘይት አይወለወልም፡፡ BSB BSB: O mountains of Gilboa, may you have no dew or rain, no fields yielding offerings of grain. For there the shield of the mighty was defiled, the shield of Saul, no longer anointed with oil.
22 ULB ከሞቱት ሰዎች ደም፣ ከኃያላኑም ገላ የዮናታን ቀስት ተመልሶ አልመጣም፤ የሳዖልም ሰይፍ በከንቱ አልተመለሰም፡፡ BSB BSB: From the blood of the slain, from the fat of the mighty, the bow of Jonathan did not retreat, and the sword of Saul did not return empty.
23 ULB ሳዖልና ዮናታን በሕይወት እያሉ የሚዋደዱና ግርማ ያላቸው ነበሩ፤ ሲሞቱም አልተለያዩም፤ከንስርም ይልቅ ፈጣኖች ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ፡፡ BSB BSB: Saul and Jonathan, beloved and delightful in life, were not divided in death. They were swifter than eagles; they were stronger than lions.
24 ULB እናንተ የእስራኤል ቆነጃጅት ሆይ፤ ሐምራዊ ቀሚስና ቀጭን ፈትል ላለበሳችሁ፤ ልብሶቻችሁንም በወርቀ-ዘቦ ላስጌጠላችሁ ለሳዖል አልቅሱለት፡፡ BSB BSB: O daughters of Israel, weep for Saul, who clothed you in scarlet and luxury, who decked your garments with ornaments of gold.
25 ULB ኃያላን እንዴት እንዲህ በጦርነት መካከል ወደቁ! ዮናታን ከፍ ባሉ ስፍራዎቻችሁ ላይ ሞቶአል፡፡ BSB BSB: How the mighty have fallen in the thick of battle! Jonathan lies slain on your heights.
26 ULB ወንድሜ ዮናታን ሆይ፤ እኔ ስለ አንተ አዘንሁ፤ አንተ ለእኔ እጅግ ውድ ነበርህ፤ ፍቅርህ ለእኔ ድንቅ ነበር፤ ከሴት ፍቅርም የላቀ ነበር፡፡ BSB BSB: I grieve for you, Jonathan, my brother. You were delightful to me; your love to me was extraordinary, surpassing the love of women.
27 ULB ኃያላን እንዴት ወደቁ፤ የጦር መሣሪዎቹስ እንዴት ከንቱ ሆኑ!” BSB BSB: How the mighty have fallen, and the weapons of war have perished!”
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.