1 ULB የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የንጉሡ ልብ አቤሴሎምን እንደ ናፈቀ ተረዳ፡፡ BSB BSB: Now Joab son of Zeruiah perceived that the king’s heart longed for Absalom.
2 ULB ስለዚህም ኢዮአብ ወደ ቴቁሔ ልኮ አንዲት ብልኅ የሆነች ሴት አስመጥቶ፣ “ሐዘንተኛ በመምሰል የሐዘን ልብስ ልበሺ፣ እባክሽን ዘይት አትቀቢ ነገር ግን ለብዙ ጊዜ እንዳዘነች መስለሽ ታዪ፡፡ BSB BSB: So Joab sent to Tekoa to bring a wise woman from there. He told her, “Please pretend to be a mourner; put on clothes for mourning and do not anoint yourself with oil. Act like a woman who has mourned for the dead a long time.
3 ULB ከዚያም ወደ ንጉሡ ሄደሽ እኔ የምገልጽልሽን ንገሪው፡፡” ስለዚህ ኢዮአብ ለንጉሡ የምትናገረውን ነገር ነገራት፡፡ BSB BSB: Then go to the king and speak these words to him.” And Joab put the words in her mouth.
4 ULB ከቴቁሔ የመጣችውም ሴት ለንጉሡ ለመንገር በገባችበት ጊዜ በንጉሡ ፊት ለጥ ብላ እጅ በመንሣት፣ “ንጉሥ ሆይ፣ እርዳኝ” አለች፡፡ BSB BSB: When the woman from Tekoa went to the king, she fell facedown in homage and said, “Help me, O king!”
5 ULB ንጉሡም፣ “ችግርሽ ምንድን ነው?” አላት፡፡ ሴቲቱም፣ “እኔ በእውነቱ ባሏ የሞተባት ባልቴት ነኝ፡፡ BSB BSB: “What troubles you?” the king asked her. “Indeed,” she said, “I am a widow, for my husband is dead.
6 ULB እኔ ባሪያህ ሁለት ልጆች ነበሩኝ፣ እነርሱም ሜዳ ላይ እርስ በርሳቸው ተጣሉ፣ የሚገላግላቸውም ሰው አልነበረም፡፡ አንደኛውም ሌላኛውን መታውና ገደለው፡፡ BSB BSB: And your maidservant had two sons who were fighting in the field with no one to separate them, and one struck the other and killed him.
7 ULB መላው ቤተሰብም አሁን በባሪያህ ላይ ተነሥቶ፣’ስለገደለው ስለ ወንድሙ ዋጋ እንዲከፍልና እኛም እንድንገድለው ወንድሙን የገደለውን ሰው አውጥተሸ ስጪን’ አሉኝ፤ ወራሽ የሆነውንም ያጠፉ ዘንድ ይፈልጋሉ፡፡ በዚህም ዓይነት የቀረኝን አንድ የጋለ ፍም አጥፍተው፣ ባሌን በምድር ላይ ያለ ስምና ያለ ዘር ሊያስቀሩት ነው፡፡” BSB BSB: Now the whole clan has risen up against your maidservant and said, ‘Hand over the one who struck down his brother, that we may put him to death for the life of the brother whom he killed. Then we will cut off the heir as well!’ So they would extinguish my one remaining ember by not preserving my husband’s name or posterity on the earth.”
8 ULB ስለዚህ ንጉሡ ለሴቲቱ፣ “አንቺ ወደ ቤትሽ ሂጂ፣ አንድ ነገር እንዲደረግልሽ እኔ ትዕዛዝ እሰጣለሁ” አላት፡፡ BSB BSB: “Go home,” the king said to the woman, “and I will give orders on your behalf.”
9 ULB የቴቁሔዪቱም ሴት ለንጉሡ፣ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ በደሉ በእኔና በአባቴ ቤተሰብ ላይ ይሁን፤ ንጉሡና ዙፋኑ ከበደል የነጹ ይሁኑ” አለች፡፡ BSB BSB: But the woman of Tekoa said to the king, “My lord the king, may any blame be on me and on my father’s house, and may the king and his throne be guiltless.”
10 ULB ንጉሡም፣ “ማንም ሰው ቢናገርሽ ወደ እኔ ዘንድ አምጪው ከዚያ በኋላም አያስቸግርሽም” በማለት መለሰላት፡፡ BSB BSB: “If anyone speaks to you,” said the king, “bring him to me, and he will not trouble you again!”
11 ULB ከዚያ በኋላ ሴቲቱ፣ “ደም ተበቃዩ ሌላ ሰው እንዳያጠፋና ልጄንም እንዳያጠፉት፣ እባክህን ንጉሥ እግዚአብሔር አምላክህን አሳስብልኝ” አለችው፡፡ ንጉሡም፣ “ሕያው እግዚአብሔርን ከልጅሽ ራስ አንዲት ፀጉር እንኳ አትወድቅም” ብሎ መለሰላት፡፡ BSB BSB: “Please,” she replied, “may the king invoke the LORD your God to prevent the avenger of blood from increasing the devastation, so that my son may not be destroyed!” “As surely as the LORD lives,” he vowed, “not a hair of your son’s head will fall to the ground.”
12 ULB ከዚያ በኋላም ሴቲቱ፣ “ባሪያህ ለጌታዬ ለንጉሡ ተጨማሪ ቃል እንድናገር እባክህ ፍቀድልኝ” አለችው፡፡ ንጉሡም፣ “ተናገሪ” አላት፡፡ BSB BSB: Then the woman said, “Please, may your servant speak a word to my lord the king?” “Speak,” he replied.
13 ULB ስለዚህ ሴቲቱ፣ “ታዲያ፣ እንዲሀ ያለውን ነገር በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ያሰብኸው ለምንድን ነው? ምክንያቱም ይህንን በመናገሩ ንጉሡ ራሱን በደለኛ እንደሚያደርግ ሰው ነው፣ የኮበለለውን ልጁን ንጉሡ ወደ ቤቱ አልመለሰውምና፡፡ BSB BSB: The woman asked, “Why have you devised a thing like this against the people of God? When the king says this, does he not convict himself, since he has not brought back his own banished son?
14 ULB ሁላችንም እንሞት ዘንድ ይገባናልና፣ እንደገናም ሊሰበሰብ እንደማይችል እንደ ፈሰሰ ውሃ ነንና፡፡ እግዚአብሔር ግን የሰውን ሕይወት አይወስድም ይልቁንም ከፊቱ ራሱን ያስኮበለለውን ሰው ወደ ራሱ የሚመልስበት መንገድ ይፈልጋል እንጂ፡፡ BSB BSB: For we will surely die and be like water poured out on the ground, which cannot be recovered. Yet God does not take away a life, but He devises ways that the banished one may not be cast out from Him.
15 ULB እንግዲህ አሁን ለጌታዬ ለንገሡ ይህንን ልናገር የመጣሁት ሕዝቡ እንድፈራ ስላደረጉኝ ነው፡፡ ከዚህም የተነሣ ባሪያህ ለራሷ፣ ‘አሁን ለንጉሡ እናገራለሁ፣ ምናልባትም ንጉሡ የባሪያውን ጥያቄ ይቀበል ያደርግላት ይሆናል፡፡ BSB BSB: Now therefore, I have come to present this matter to my lord the king because the people have made me afraid. Your servant thought, ‘I will speak to the king. Perhaps he will grant the request of his maidservant.
16 ULB እኔንና ልጄን ከእግዚአብሔር ርስት ሊያጠፋን ካለው ሰው እጅ ያድን ዘንድ ባሪያውን ያወጣ ዘንድ ንጉሡ ይሰማኛልና፣’ አለች፡፡ BSB BSB: For the king will hear and deliver his maidservant from the hand of the man who would cut off both me and my son from God’s inheritance.’
17 ULB ከዚያ በኋላም ባሪያህ፣ ‘እግዚአብሔር ሆይ፣ የጌታዬ የንጉሡ ቃል እፎይታን የሚሰጠኝ ይሁን፣ ምክንያቱም መልካሙን ከክፉው በመለየት ጌታዬ ንጉሡ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነውና’ እግዚአብሔር አምላክህ ከአንተ ጋር ይሁን፡፡” BSB BSB: And now your servant says, ‘May the word of my lord the king bring me rest, for my lord the king is able to discern good and evil, just like the angel of God. May the LORD your God be with you.’”
18 ULB ከዚያ በኋላም ንጉሡ ለሴቲቱ፣ “እኔ ለምጠይቅሽ ጥያቄ እባክሽ ምንም ነገር አትደብቂኝ” አላት፡፡ BSB BSB: Then the king said to the woman, “I am going to ask you something; do not conceal it from me!” “Let my lord the king speak,” she replied.
19 ULB ንጉሡም፣ “በዚህ ሁሉ የኢዮአብ እጅ ከአንቺ ጋር የለም?” ሴቲቱም፣ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፤ ጌታዬ ንጉሡ ከተናገረው አንዳችም ነገር ማንም ሰው ወደ ቀኝም ወደ ግራም ማምለጥ አይችልም፡፡ ያዘዘኝና ባሪያህም የተናገረችውን እነዚህን ነገሮች እንድናገር የነገረኝ ባሪያህ ኢዮአብ ነው፡፡ BSB BSB: So the king asked, “Is the hand of Joab behind all this?” The woman answered, “As surely as you live, my lord the king, no one can turn to the right or to the left from anything that my lord the king says. Yes, your servant Joab is the one who gave me orders; he told your maidservant exactly what to say.
20 ULB ባሪያህ ኢዮአብ ይህንን ያደረገው ነገሮች እየሄዱበት ያለውን አቅጣጫ ለመለወጥ ነው፡፡ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ጥበብ ጌታዬ ጠቢብ ነው፤ በምድሪቱም የሚሆነውን ማንኛውንም ነገር ያውቃል፡፡” BSB BSB: Joab your servant has done this to bring about this change of affairs, but my lord has wisdom like the wisdom of the angel of God, to know everything that happens in the land.”
21 ULB ስለዚህ ንጉሡ ለኢዮአብ፣ “እነሆ፣ እኔ አሁን ይህንን አደርጋለሁ፡፡ እንግዲህ ሂድና ወጣቱን አቤሴሎምን አምጣው” አለው፡፡ BSB BSB: Then the king said to Joab, “I hereby grant this request. Go, bring back the young man Absalom.”
22 ULB ስለዚህ ኢዮአብ ለንጉሡ አክብሮቱንና ምስጋናውን ለመግለጽ ጎንበስ ብሎ እጅ ነሳ፡፡ ኢዮአብም፣ “ዛሬ ባሪያህ በጌታዬ በንጉሡ ፊት ሞገስ እንዳገኘ አወቅሁ፣ ንጉሡ የባሪያውን ጥያቄ ፈጽሞለታልና” BSB BSB: Joab fell facedown in homage and blessed the king. “Today,” said Joab, “your servant knows that he has found favor in your eyes, my lord the king, because the king has granted his request.”
23 ULB ስለዚህ ኢዮአብ ተነሥቶ ወደ ጌሹር ሄደ፣ አቤሴሎምንም ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ፡፡ BSB BSB: So Joab got up, went to Geshur, and brought Absalom to Jerusalem.
24 ULB ንጉሡም፣ “ወደ ራሱ ቤት መመለስ ይችላል፣ ነገር ግን ፊቴን አያይም” ስለዚህ አቤሴሎም ወደ ቤቱ ተመለሰ፣ የንጉሡን ፊት ግን አላየም፡፡ BSB BSB: But the king added, “He may return to his house, but he must not see my face.” So Absalom returned to his own house, but he did not see the face of the king.
25 ULB በመላው እስራኤል ከአቤሴሎም ይልቅ በመልከ መልካምነቱ የተመሰገነ ማንም አልነበረም፡፡ ከእግር ተረከዙ ጀምሮ እስከ አናቱ ድረስ ምንም እንከን አልነበረበትም፡፡ BSB BSB: Now there was not a man in all Israel as handsome and highly praised as Absalom. From the sole of his foot to the top of his head, he did not have a single flaw.
26 ULB ይከብደው ስለ ነበረ የራሱን ፀጉር በሚቆረጥበት ጊዜ ፀጉሩን ይመዝነው ነበር፣ በንጉሡም የመመዘኛ ልክ ሁለት መቶ ሰቅል ይመዝን ነበር፡፡ BSB BSB: And when he cut the hair of his head—he shaved it every year because his hair got so heavy—he would weigh it out to be two hundred shekels, according to the royal standard.
27 ULB አቤሴሎምም ሦስት ወንዶች ልጆችና ትዕማር የምትባል አንድ ሴት ልጅ ነበሩት፡፡ ሴት ልጁም ውብ ነበረች፡፡ BSB BSB: Three sons were born to Absalom, and a daughter named Tamar, who was a beautiful woman.
28 ULB አቤሴሎምም የንጉሡን ፊት ሳያይ ሁለት ሙሉ ዓመት በኢየሩሳሌም ኖረ፡፡ BSB BSB: Now Absalom lived in Jerusalem two years without seeing the face of the king.
29 ULB ከዚህ በኋላ ወደ ንጉሡ ይወስደው ዘንድ አቤሴሎም ወደ ኢዮአብ መልእክት ላከ፣ ኢዮአብ ግን ሊመጣ አልፈለገም፡፡ ስለዚህ አቤሴሎም ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ኢዮአብ መልእክት ላከ፣ ኢዮአብ ግን አሁንም አልመጣም፡፡ BSB BSB: Then he sent for Joab to send him to the king, but Joab refused to come to him. So Absalom sent a second time, but Joab still would not come.
30 ULB ስለዚህ አቤሴሎም ለአገልጋዮቹ፣ “ኢዮአብ በእኔ እርሻ አጠገብ እርሻ አለው፣ በዚያም ገብስ አለው፤ ሂዱና በገብሱ ላይ እሳት ልቀቁበት” አላቸው፡፡ ስለዚህ የአቤሴሎም አገልጋዮች በእርሻው ላይ እሳት ለቀቁበት፡፡ BSB BSB: Then Absalom said to his servants, “Look, Joab’s field is next to mine, and he has barley there. Go and set it on fire!” And Absalom’s servants set the field on fire.
31 ULB ከዚያም ኢዮአብ ተነስቶ ወደ አቤሴሎም ቤት መጣና፣ “አገልጋዮችህ በእርሻዬ ላይ እሳት የለቀቁበት ለምንድን ነው?” አለው፡፡ BSB BSB: Then Joab came to Absalom’s house and demanded, “Why did your servants set my field on fire?”
32 ULB አቤሴሎምም ለኢዮአብ፣ “እነሆ፣ ወደ አንተ ዘንድ፣ ‘ወደ ንጉሡ እልክህ ዘንድ ወደ እኔ ዘንድ መጥተህ ለንጉሡ፣ ከጌሹር ለምን መጣሁ? እዚያው ብቆይ ይሻለኝ ነበር’ ብለህ እንድትነግርልኝ መልእክት ልኬብህ ነበር፡፡ ስለዚህ አሁን የንጉሡን ፊት ልይ፣ በደለኛ ከሆንኩም ይግደለኝ” አለው፡፡ BSB BSB: “Look,” said Absalom, “I sent for you and said, ‘Come here. I want to send you to the king to ask: Why have I come back from Geshur? It would be better for me if I were still there.’ So now, let me see the king’s face, and if there is iniquity in me, let him kill me.”
33 ULB ስለዚህ ኢዮአብ ወደ ንጉሡ ዘንድ ሄዶ ነገረው፡፡ ንጉሡም አቤሴሎምን ባስጠራው ጊዜ አቤሴሎም በንጉሡ ፊት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ፣ ንጉሡም አቤሴሎምን ሳመው፡፡ BSB BSB: So Joab went and told the king, and David summoned Absalom, who came to him and bowed facedown before him. Then the king kissed Absalom.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.