1 ULB ንጉሡ በቤቱ ተደላድሎ ከተቀመጠና እግዚአብሔርም በዙሪያው ካሉት ጠላቶቹ ሁሉ ካሳረፈው በኋላ፣ BSB BSB: After the king had settled into his palace and the LORD had given him rest from all his enemies around him,
2 ULB ለነቢዩ ለናታን ንጉሡ እንደዚህ አለው፣ “እነሆ፤ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤተ መንግሥት ውስጥ እኖራለሁ፤ የእግዚአብሔር ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል” አለው፡፡ BSB BSB: he said to Nathan the prophet, “Here I am, living in a house of cedar, while the ark of God remains in a tent.”
3 ULB ከዚያ በኋላ ናታን ለንጉሡ፣ “እግዚአብሔር ካንተ ጋር ስለሆነ ያሰብኸውን ሁሉ አድርግ” አለው፡፡ BSB BSB: And Nathan replied to the king, “Go and do all that is in your heart, for the LORD is with you.”
4 ULB ነገር ግን በዚያች ሌሊት እንደዚህ የሚል የእግዚአብሔር ቃል ወደ ናታን መጣ፣ BSB BSB: But that night the word of the LORD came to Nathan, saying,
5 ULB “ሂድና ለባሪያዬ ለዳዊት እንደዚህ በለው፣ ‘እግዚአብሔር የሚልህ እንደዚህ ነው፣ የምኖርበትን ቤት አንተ ትሠራልኛለህን? BSB BSB: “Go and tell My servant David that this is what the LORD says: Are you the one to build for Me a house to dwell in?
6 ULB የእስራኤልን ሕዝብ ከግብፅ ካወጣሁበት ጊዜ አንሥቶ እስከ ዛሬ ድረስ በድንኳን ማደሪያ ውስጥ ሆኜ እንቀሳቀስ ነበር እንጂ በቤት ውስጥ ኖሬ አላውቅምና፤ BSB BSB: For I have not dwelt in a house from the day I brought the Israelites up out of Egypt until this day, but I have moved about with a tent as My dwelling.
7 ULB በመላው የእስራኤል ሕዝብ መካከል በተመላለስሁባቸው በሁሉም ስፈራዎች ሕዝቤን እስራኤልን እንዲጠብቁ ከሾምኋቸው መሪዎች ለአንዱ ስንኳ፣ ‘ከዝግባ እንጨት ለምን ቤት አልሠራህልኝም?’ ብያለሁን? BSB BSB: In all My journeys with all the Israelites, have I ever asked any of the leaders I appointed to shepherd My people Israel, ‘Why haven’t you built Me a house of cedar?’
8 ULB እንግዲህ አሁን ለባሪያዬ ለዳዊት እንደዚህ በለው፣ ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሚለው ይህንን ነው፣ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ገዥ ትሆን ዘንድ ከመስክ በጎችን ትከተል ከነበርህበት ስፍራ ወሰድሁህ፤ BSB BSB: Now then, you are to tell My servant David that this is what the LORD of Hosts says: I took you from the pasture, from following the flock, to be the ruler over My people Israel.
9 ULB በሄድህበት ሁሉ እኔ ከአንተ ጋር ነበርሁ፤ ጠላቶችህንም ሁሉ ከፊትህ አጠፋሁልህ’፤ በምድር ላይ ስማቸው ታላቅ እንደሆነው እንደ አንዱ ለአንተ ታላቅ ስም አደርግልሃለሁ፡፡ BSB BSB: I have been with you wherever you have gone, and I have cut off all your enemies from before you. Now I will make for you a name like that of the greatest in the land.
10 ULB ከእንግዲህ ወዲያ በራሳቸው መኖሪያ እንዲኖሩ እንጂ እንዳይናወጡ ለሕዝቤ ለእስራኤል ቦታ እሰጣቸዋለሁ፣ በዚያም እተክላቸዋለሁ፡፡ ከዚህ በፊት እንደሆነውም ከእንግዲህ ወዲህ ክፉ ሕዝብ አይጨቁናቸውም፤ BSB BSB: And I will provide a place for My people Israel and will plant them so that they may dwell in a place of their own and be disturbed no more. No longer will the sons of wickedness oppress them as they did at the beginning
11 ULB መሳፍንትን በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ባዘዝሁበት ጊዜ እንዳደረጉባቸው ከእንግዲህ ወዲህ አያደርጉባቸውም፤ ከጠላቶችህም ሁሉ አሳርፍሃለሁ፡፡ ከዚህም ባሻገር፣ እኔ እግዚአብሔር ቤት እንደምሠራልህ እነግርሃለሁ፡፡ BSB BSB: and have done since the day I appointed judges over My people Israel. I will give you rest from all your enemies. The LORD declares to you that He Himself will establish a house for you.
13 ULB እርሱ ለእኔ ቤት ይሠራልኛል፤ እኔም የመንግሥቱን ዙፋን ለዘላለም አጸናለሁ፡፡ BSB BSB: He will build a house for My Name, and I will establish the throne of his kingdom forever.
14 ULB እኔ አባት እሆነዋለሁ፣ እርሱም ልጄ ይሆናል፡፡ ኃጢአት በሚያደርግበት ጊዜ በሰዎች በትር እቀጣዋለሁ፣ የሰው ልጆች በሚገረፉበትም ግርፋት እገርፈዋለሁ፤ BSB BSB: I will be his Father, and he will be My son. When he does wrong, I will discipline him with the rod of men and with the blows of the sons of men.
15 ULB ከፊትህ ካስወገድሁት ከሳኦል ላይ እንደወሰድሁ ኪዳናዊ ታማኝነቴ ከእርሱ አይርቅም፡፡ BSB BSB: But My loving devotion will never be removed from him as I removed it from Saul, whom I removed from before you.
17 ULB ናታን ለዳዊት እንደዚህ ተናገረ፣ ይህንንም ሁሉ ነገር ነገረው፤ ጠቅላላውንም ራእይ ገለጸለት፡፡ BSB BSB: So Nathan relayed to David all the words of this entire revelation.
18 ULB ከዚያም ንጉሥ ዳዊት ገባና በእግዚአብሔር ፊት ተቀመጠና እንደዚህ አለ፣ “እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፣ እኔ ማን ነኝ? እስከዚህ ደረጃስ ታደርሰኝ ዘንድ ቤተሰቤስ ምንድን ነው? BSB BSB: Then King David went in, sat before the LORD, and said, “Who am I, O Lord GOD, and what is my house, that You have brought me this far?
19 ULB ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ ይህ በፊትህ ታናሽ ነገር ነው፡፡ ስለ ባሪያህ ቤተሰብ እንኳን ለረጅም ጊዜ የሚሆነውን ተናገርህ፣ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ከዚህ በኋላ የሚኖረውንም ትውልዴን አሳየኸኝ! BSB BSB: And as if this was a small thing in Your eyes, O Lord GOD, You have also spoken about the future of the house of Your servant. Is this Your custom with man, O Lord GOD?
20 ULB እኔ ዳዊት ከዚህ በላይ ለአንተ ምን እላለሁ? ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ባሪያህን አክብረኸዋል፡፡ BSB BSB: What more can David say to You? For You know Your servant, O Lord GOD.
21 ULB ስለ ቃልህ ብለህ፣ ዓላማህንም ትፈጽም ዘንድ ይህን ታላቅ ነገር አድርገሃል፤ ለባሪያህም ገልጸህለታል፡፡ BSB BSB: For the sake of Your word and according to Your own heart, You have accomplished this great thing and revealed it to Your servant.
22 ULB ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ታላቅ ነህና እንደ አንተ ያለም የለም፤ በገዛ ጆሮቻችንም እንደ ሰማን ከአንተም በቀር አምላክ የለም፡፡ BSB BSB: How great You are, O Lord GOD! For there is none like You, and there is no God but You, according to everything we have heard with our own ears.
23 ULB አንተ እግዚአብሔር መጥተህ ለራስህ እንዳዳንከው በምድር ላይ እንዳለው እንደ ሕዝብህ ያለ በምድር ላይ ምን ሕዝብ አለ? ይህንን ያደረግኸው ለራስህ ሕዝብን ታስነሳ ዘንድ፣ ለራስህም ስምህን ታስጠራ ዘንድና ታላቅና አስፈሪ ነገር በምድርህ ታደርግ ዘንድ ነው፡፡ ከግብፅ ከዋጀኸው ከሕዝብህ ፊት አሕዛብንና ጣዖቶቻቸውን አባረርህ፡፡ BSB BSB: And who is like Your people Israel—the one nation on earth whom God went out to redeem as a people for Himself and to make a name for Himself? You performed great and awesome wonders by driving out nations and their gods from before Your people, whom You redeemed for Yourself from Egypt.
24 ULB እስራኤልን ሕዝብህ አድርገህ ለዘላለም አጸናህ፣ አንተም፣ እግዚአብሔር ሆይ አምላክ ሆንህላቸው፡፡ BSB BSB: For You have established Your people Israel as Your very own forever, and You, O LORD, have become their God.
25 ULB አሁንም ባሪያህንና ቤተሰቡን በሚመለከት የሰጠኸውን ተስፋ ለዘላለም አጽናለት፤ እንደተናገርኸውም አድርግለት፡፡ BSB BSB: And now, O LORD God, confirm forever the word You have spoken concerning Your servant and his house. Do as You have promised,
26 ULB የእኔ፣ የባሪያህ የዳዊት ቤት በፊትህ በሚጸናበት ጊዜ ሕዝቦች፣ ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የእስራኤል አምላክ ነው’ ይሉ ዘንድ ስምህ ለዘላለም ታላቅ ይሁን፡፡ BSB BSB: so that Your name will be magnified forever when it is said, ‘The LORD of Hosts is God over Israel.’ And the house of Your servant David will be established before You.
27 ULB አንተ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ የእስራኤል አምላክ ለባሪያህ ቤት እንደምትሠራለት ገልጸህለታልና፤ ለዚህ ነው እኔ ባሪያህ ወደ አንተ ለመጸለይ ድፍረት ያገኘሁት፡፡ BSB BSB: For You, O LORD of Hosts, the God of Israel, have revealed this to Your servant when You said, ‘I will build a house for you.’ Therefore Your servant has found the courage to offer this prayer to You.
28 ULB አሁን፣ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ አምላክ ነህ፣ ቃሎችህም የታመኑ ናቸው፤ ይህንን መልካም የተስፋ ቃል ለባሪያህ ገብተህለታል፡፡ BSB BSB: And now, O Lord GOD, You are God! Your words are true, and You have promised this goodness to Your servant.
29 ULB በፊትህ ለዘላለም የሚቀጥል ይሆን ዘንድ፣ እንግዲህ አሁን የባሪያህን ቤት መባረክ አንተን ደስ ያሰኝህ፡፡ አንተ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ እነዚህን ነገሮች ተናግረሃልና በበረከትህ የባሪያህ ቤት ለዘላለም የተባረከ ይሆናል፡፡” BSB BSB: Now therefore, may it please You to bless the house of Your servant, that it may continue forever before You. For You, O Lord GOD, have spoken, and with Your blessing the house of Your servant will be blessed forever.”
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.