3 ULB ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርሱ ሲመጣ በራእይ በግልጽ ታየው። መልአኩ፣ “ቆርኔሌዎስ!” አለው። BSB BSB: One day at about the ninth hour, he had a clear vision of an angel of God who came to him and said, “Cornelius!”
4 ULB ቆርኔሌዎስ መልአኩን አተኵሮ ተመለከተውና ፈርቶ እንዲህ አለ፤ “ጌታዬ ሆይ፣ ይህ ምንድን ነው?” መልአኩም መልሶ፣ “ጸሎትህና ምጽዋትህ በመታሰቢያነት ወደ እግዚአብሔር ደርሶአል። BSB BSB: Cornelius stared at him in fear and asked, “What is it, Lord?” The angel answered, “Your prayers and gifts to the poor have ascended as a memorial offering before God.
5 ULB ጴጥሮስም ተብሎ የሚጠራውን ስምዖን የሚባለውን ሰውየ ለማስመጣት አሁን ወደ ኢዮጴ ከተማ ሁለት ሰዎችን ላክ። BSB BSB: Now send men to Joppa to call for a man named Simon who is called Peter.
6 ULB ሰውየው ቤቱ በባሕሩ አጠገብ ከሚገኝ ስምዖን ከሚባለው ከቆዳ ፋቂው ጋር አለ” አለው። BSB BSB: He is staying with Simon the tanner, whose house is by the sea.”
7 ULB ያነጋግረው የነበረው መልአክ እንደ ሄደ፣ ቆርኔሌዎስ ከሚያገለግሉት ወታደሮች መካከል እግዚአብሔርን ያመልክ የነበረ አንድ ወታደርንና ከቤት አሽከሮቹ ሁለቱን ጠራ። BSB BSB: When the angel who spoke to him had gone, Cornelius called two of his servants and a devout soldier from among his attendants.
8 ULB ቆርኔሌዎስ የሆነውን ሁሉ ነግሮአቸው ወደ ኢዮጴ ላካቸው። BSB BSB: He explained what had happened and sent them to Joppa.
10 ULB ራበውና አንዳች ነገር ለመብላት ፈለገ፤ ነገር ግን ሰዎች ምግብ በማዘጋጀት ላይ ሳሉ፣ በተመስጦ ውስጥ ገባ፤ BSB BSB: He became hungry and wanted something to eat, but while the meal was being prepared, he fell into a trance.
11 ULB ሰማይ ተከፍቶ፣ ትልቅ ሸማ የሚመስል አንድ መያዣ በአራቱ ጠርዞቹ ተይዞ ወደ ምድር ሲወርድም አየ። BSB BSB: He saw heaven open and something like a large sheet being let down to earth by its four corners.
12 ULB በውስጡም አራት እግር ያላቸው እንስሳት ሁሉና በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጡራን፣ የሰማይ ወፎችም ነበሩበት። BSB BSB: It contained all kinds of four-footed animals and reptiles of the earth, as well as birds of the air.
13 ULB “ጴጥሮስ ሆይ፣ ተነሥና ዐርደህ ብላ” የሚል ድምፅ ለጴጥሮስ መጣ። BSB BSB: Then a voice said to him: “Get up, Peter, kill and eat!”
14 ULB ጴጥሮስም፣ “ጌታ ሆይ፣ አይሆንም፤ ምክንያቱም እኔ ርኩስና አስጸያፊ የሆነ ምንም ነገር ፈጽሞ በልቼ አላውቅም” አለ። BSB BSB: “No, Lord!” Peter answered. “I have never eaten anything impure or unclean.”
15 ULB እንደገናም ድምፅ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ጴጥሮስ መጣ፤ “እግዚአብሔር ቅዱስ ያደረገውን ርኩስ ብለህ አትጥራው” የሚል ድምፅ። BSB BSB: The voice spoke to him a second time: “Do not call anything impure that God has made clean.”
16 ULB ይህም ሦስት ጊዜ ሆነ፤ ከዚያም መያዣው ወዲያው ወደ ሰማይ ተመልሶ ተወሰደ። BSB BSB: This happened three times, and all at once the sheet was taken back up into heaven.
17 ULB ጴጥሮስ ያየው ራእይ ምን ትርጕም ሊኖረው እንደሚችል በጣም ግራ ገብቶት ሳለ፣ ወደ ቤት የሚያስሄደውን መንገድ ጠይቀው ካገኙ በኋላ እነሆ፣ ቆርኔሌዎስ የላካቸው ሰዎች በበሩ ፊት ለፊት ቆሙ። BSB BSB: While Peter was puzzling over the meaning of the vision, the men sent by Cornelius found Simon’s house and approached the gate.
18 ULB ድምፃቸውን ከፍ በማድረግም ጴጥሮስ የሚባለው ስምዖን በዚያ መኖሩንና አለመኖሩን ጠየቁ። BSB BSB: They called out to ask if Simon called Peter was staying there.
19 ULB ጴጥሮስ ስለ ራእዩ በማሰብ ላይ ሳለ፣ መንፈስ ቅዱስ ጴጥሮስን እንዲህ አለው፤ “እነሆ፣ ሦስት ሰዎች ይፈልጉሃል። BSB BSB: As Peter continued to reflect on the vision, the Spirit said to him, “Behold, three men are looking for you.
20 ULB ተነሥና ውረድ፤ ከእነርሱም ጋር ሂድ። ዐብረሃቸው ለመሄድ አትፍራ፤ ምክንያቱም የላክኋቸው እኔ ነኝ።” BSB BSB: So get up! Go downstairs and accompany them without hesitation, because I have sent them.”
21 ULB ስለዚህም ጴጥሮስ ወደ ሰዎቹ ወርዶ፣ “የምትፈልጉት ሰው እኔ ነኝ። የመጣችሁት ለምንድን ነው?” አላቸው። BSB BSB: So Peter went down to the men and said, “Here am I, the one you are looking for. Why have you come?”
22 ULB እነርሱም እንዲህ አሉት፤ "እግዚአብሔርን የሚያመልክ፣ በአይሁድ ሕዝብ ሁሉ ዘንድም የተመሰገነ ቆርኔሌዎስ የሚባል ጻድቅ ሰው፣ ወደ ቤቱ ሰው ልኮ እንዲያስመጣህ የእግዚአብሔር መልአክ ነገረው፤ እንዲህ ያደረገውም ከአንተ መልእክትን መስማት እንዲችል ነው።” BSB BSB: “Cornelius the centurion has sent us,” they said. “He is a righteous and God-fearing man with a good reputation among the whole Jewish nation. A holy angel instructed him to request your presence in his home so he could hear a message from you.”
23 ULB ጴጥሮስም እንዲገቡና ከእርሱና ዐብረውት ከነበሩ ሰዎች ጋር እንዲቈዩ በእንግድነት ተቀበላቸው። በማግስቱ ጧት ጴጥሮስ ተነሣና ከእነርሱ ጋር ሄደ፤ በኢዮጴ ከነበሩት ወንድሞችም አንዳንዶቹ ዐብረውት ሄዱ። BSB BSB: So Peter invited them in as his guests. And the next day he got ready and went with them, accompanied by some of the brothers from Joppa.
24 ULB በሚቀጥለው ቀን ቂሣርያ ደረሱ። ቆርኔሌዎስ እየጠበቃቸው ነበር፤ ዘመዶቹንና የቅርብ ወዳጆቹንም ጠርቶ እንዲሰበሰቡ አደረገ። BSB BSB: The following day he arrived in Caesarea, where Cornelius was expecting them and had called together his relatives and close friends.
25 ULB ጴጥሮስ ሲገባ፣ ቆርኔሌዎስ አግኝቶት እግሩ ላይ ወድቆ ሰገደለት። BSB BSB: As Peter was about to enter, Cornelius met him and fell at his feet to worship him.
26 ULB ነገር ግን ጴጥሮስ አነሣውና፣ “ተነሥ ቁም፤ እኔ ራሴም ሰው ነኝ” አለው። BSB BSB: But Peter helped him up. “Stand up,” he said, “I am only a man myself.”
27 ULB ጴጥሮስ ከቆርኔሌዎስ ጋር እየተነጋገረ ወደ ውስጥ ሲገባ፣ የተሰበሰቡ ብዙ ሰዎችን አገኘ። BSB BSB: As Peter talked with him, he went inside and found many people gathered together.
29 ULB ሲላክብኝ ሳልከራከር የመጣሁት ከዚህ የተነሣ ነው። ስለዚህ ለምን እንደ ላካችሁብኝ እጠይቃችኋለሁ።" BSB BSB: So when I was invited, I came without objection. I ask, then, why have you sent for me?”
30 ULB ቆርኔሌዎስም እንዲህ አለ፤ “ከአራት ቀን በፊት ልክ በዚህ ሰዓት በዘጠኝ ሰዓት በቤቴ ውስጥ እጸልይ ነበር፤ እነሆም ነጭ ልብስ ለብሶ ፊት ለፊቴ ቆመና፣ BSB BSB: Cornelius answered: “Four days ago I was in my house praying at this, the ninth hour. Suddenly a man in radiant clothing stood before me
31 ULB ‘ቆርኔሌዎስ ሆይ፣ ጸሎትህ በእግዚአብሔር ዘንድ ተሰምቶአል፤ ምጽዋትህም መታሰቢያ ሆኖልሃል። BSB BSB: and said, ‘Cornelius, your prayer has been heard, and your gifts to the poor have been remembered before God.
32 ULB ስለዚህ ወደ ኢዮጴ ሰው ላክና ጴጥሮስም የሚባለውን ስምዖንን ወደ አንተ ጠርተህ አስመጣ። እርሱ በቆዳ ፋቂው በስምዖን ቤት በባሕር አጠገብ ተቀምጦአል’ አለኝ። BSB BSB: Therefore send to Joppa for Simon, who is called Peter. He is a guest in the home of Simon the tanner, by the sea.’
33 ULB ስለዚህ ወዲያው ላክሁብህ። አሁን መምጣትህ መልካም አደረግህ። አሁን እንግዲህ እኛ ሁላችን እግዚአብሔር እንድትናገር ያዘዘህን ሁሉ ለመስማት በእግዚአብሔር ፊት እንገኛለን።" BSB BSB: So I sent for you immediately, and you were kind enough to come. Now then, we are all here in the presence of God to listen to everything the Lord has instructed you to tell us.”
35 ULB ይልቁን በማንኛውም ሕዝብ ውስጥ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ የጽድቅ ተግባራትንም የሚፈጽም ሁሉ በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት አለው። BSB BSB: but welcomes those from every nation who fear Him and do what is right.
36 ULB እግዚአብሔር በሁሉ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሰላምን የምሥራች ባወጀበት ጊዜ፣ ወደ እስራኤል ሕዝብ የላከውን መልእክት ታውቃላችሁ፦ BSB BSB: He has sent this message to the people of Israel, proclaiming the gospel of peace through Jesus Christ, who is Lord of all.
37 ULB ዮሐንስ ካወጀው ጥምቀት በኋላ፣ በገሊላ በመጀመር በይሁዳ ሁሉ የታዩትን የተፈጸሙ ሁነቶችን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ፤ BSB BSB: You yourselves know what has happened throughout Judea, beginning in Galilee with the baptism that John proclaimed:
38 ULB ሁነቶቹም እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስና በኀይል እንዴት እንደ ቀባው የናዝሬቱን ኢየሱስን የሚመለከቱ ናቸው። ኢየሱስ መልካም እያደረገና ለዲያብሎስ የተገዙትን እየፈወሰ ዞረ፤ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና። BSB BSB: how God anointed Jesus of Nazareth with the Holy Spirit and with power, and how Jesus went around doing good and healing all who were oppressed by the devil, because God was with Him.
39 ULB በዕንጨት ላይ ሰቅለው የገደሉት ይህ ኢየሱስ ከአይሁድ አገርም በኢየሩሳሌምም ለፈጸማቸው ተግባራት ሁሉ እኛ ምስክሮች ነን። BSB BSB: We are witnesses of all that He did, both in the land of the Jews and in Jerusalem. And although they put Him to death by hanging Him on a tree,
40 ULB ይህን ሰው እግዚአብሔር በሦስተኛው ቀን አስነሣው፤ እንዲገለጥም አደረገው፤ BSB BSB: God raised Him up on the third day and caused Him to be seen—
41 ULB ይኸውም እግዚአብሔር አስቀድሞ መርጦአቸው ለነበሩ ምስክሮች እንጂ፣ ለሕዝቡ ሁሉ አይደለም፦ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ዐብረነው የበላንና የጠጣን እኛው ራሳችን ነን። BSB BSB: not by all the people, but by the witnesses God had chosen beforehand, by us who ate and drank with Him after He rose from the dead.
42 ULB ለሕዝቡ እንድንሰብክና በሕያዋንና በሙታን ላይ እንዲፈርድ፣ እግዚአብሔር የመረጠው ይህ እንደ ሆነ እንድንመሰክር አዘዘን። BSB BSB: And He commanded us to preach to the people and to testify that He is the One appointed by God to judge the living and the dead.
43 ULB በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኀጢአትን ይቅርታ እንዲቀበል ነቢያት ሁሉ የሚመሰክሩት ስለ እርሱ ነው።” BSB BSB: All the prophets testify about Him that everyone who believes in Him receives forgiveness of sins through His name.”
44 ULB ጴጥሮስ እነዚህን ነገሮች ገና እየተናገረ ሳለ፣ መልእክቱን በሚሰሙት ሁሉ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው። BSB BSB: While Peter was still speaking these words, the Holy Spirit fell upon all who heard his message.
45 ULB ከተገረዙት ወገን የሆኑ አማኞች፦ ከጴጥሮስ ጋር የመጡትም ሁሉ ተደነቁ፤ ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ በአሕዛብም ላይ ወርዶ ነበር። BSB BSB: All the circumcised believers who had accompanied Peter were astounded that the gift of the Holy Spirit had been poured out even on the Gentiles.
46 ULB እነዚህ አሕዛብ በሌሎች ቋንቋዎች ሲናገሩና እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ሰምተዋቸዋልና። ከዚያም በኋላ ጴጥሮስ መልሶ፣ BSB BSB: For they heard them speaking in tongues and exalting God. Then Peter said,
47 ULB “እንደ እኛ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ እነዚህ ሰዎች እንዳይጠመቁ ማን ውሃ ሊከለክላቸው ይችላል?” አለ። BSB BSB: “Can anyone withhold the water to baptize these people? They have received the Holy Spirit just as we have!”
48 ULB በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲጠመቁም አዘዛቸው። ከዚያ በኋላ ከእነርሱ ጋር ጥቂት ቀን እንዲቈይ ጴጥሮስን ለመኑት። BSB BSB: So he ordered that they be baptized in the name of Jesus Christ. Then they asked him to stay for a few days.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.