3 ULB ጉባኤው ከጾመ፣ ከጸለየና እጅ ከጫነም በኋላ አሰናበታቸው። BSB BSB: And after they had fasted and prayed, they laid their hands on them and sent them off.
4 ULB በርናባስና ሳውልም ለመንፈስ ቅዱስ ታዘዙና ወደ ሴሌውቅያ ወረዱ፤ ከዚያም በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ደሴት ሄዱ። BSB BSB: So Barnabas and Saul, sent forth by the Holy Spirit, went down to Seleucia and sailed from there to Cyprus.
5 ULB በስልማና ከተማ በነበሩ ጊዜም፣ በአይሁድ ምኵራቦች የእግዚአብሔርን ቃል ሰበኩ። ማርቆስ የተባለው ዮሐንስ ሊረዳቸው አብሯቸው ነበር። BSB BSB: When they arrived at Salamis, they proclaimed the word of God in the Jewish synagogues. And John was with them as their helper.
6 ULB በደሴቲቱም ሁሉ እስከ ጳፉ በሄዱ ጊዜ፣ ስሙ በርያሱስ የተባለ፣ አንድ አይሁዳዊ የሐሰት ነቢይና አስማተኛ አገኙ። BSB BSB: They traveled through the whole island as far as Paphos, where they found a Jewish sorcerer and false prophet named Bar-Jesus,
8 ULB ነገር ግን፣ “አስማተኛው” ኤልማስ ስሙ ሲተረጎም እንዲሁ ነውና ተቃወማቸው፤ አገረ ገዡን ከእምነቱ ለመመለስ ሞከረ። BSB BSB: But Elymas the sorcerer (for that is what his name means) opposed them and tried to turn the proconsul from the faith.
9 ULB ደግሞ ጳውሎስ የተባለው ሳውል ግን በመንፈስ ቅዱስ ተሞላ፤ ትኵር ብሎም ተመለከተውና BSB BSB: Then Saul, who was also called Paul, filled with the Holy Spirit, looked directly at Elymas
10 ULB እንዲህ አለው፤ “አንተ የዲያብሎስ ልጅ፣ ክፋትና ተንኮል ሁሉ የሞላብህ ነህ። የጽድቅ ሁሉ ጠላት ነህ። የቀናችውን የጌታን መንገድ ማጣመምህን አታቆምምን? BSB BSB: and said, “O child of the devil and enemy of all righteousness, you are full of all kinds of deceit and trickery! Will you never stop perverting the straight ways of the Lord?
11 ULB አሁንም ተመልከት፤ የጌታ እጅ በአንተ ላይ ነችና ትታወራለህ። ለጥቂት ጊዜ ፀሐይን አታይም።” ወዲያውኑ በኤልማስ ጨለማና ጭጋግ ወደቀበት፤ እጁንም ይዘው እንዲመሩት ሰዎችን እየጠየቀ ይዘዋወር ጀመር። BSB BSB: Now look, the hand of the Lord is against you, and for a time you will be blind and unable to see the light of the sun.” Immediately mist and darkness came over him, and he groped about, seeking someone to lead him by the hand.
12 ULB አገረ ገዡ የሆነውን ካየ በኋላ፣ ስለ ኢየሱስ በቀረበው ትምህርት ስለ ተደነቀ፣ አመነ። BSB BSB: When the proconsul saw what had happened, he believed, for he was astonished at the teaching about the Lord.
13 ULB ጳውሎስና ጓደኞቹም በመርከብ ከጳፉ ተነሥተው በጵንፍልያ ወዳለችው ወደ ጴርጌን መጡ። ዮሐንስ ግን ትቶአቸው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ። BSB BSB: After setting sail from Paphos, Paul and his companions came to Perga in Pamphylia, where John left them to return to Jerusalem.
15 ULB ሕግና ነቢያት ከተነበቡ በኋላ፣ የምኵራብ አለቆች፣ “ወንድሞች ሆይ፣ እዚህ ላሉት ሕዝብ የሚሆን የሚያበረታታ መልእክት ካላችሁ፣ ተናገሩ” በማለት መልእክት ላኩላቸው። BSB BSB: After the reading from the Law and the Prophets, the synagogue leaders sent word to them: “Brothers, if you have a word of encouragement for the people, please speak.”
17 ULB የዚህ የእስራኤል ሕዝብ አምላክ አባቶቻችንን መርጦ በግብፅ ይኖሩ በነበሩበት ጊዜ፣ ሕዝቡን አበዛላቸው፤ በተዘረጋችም ክንድ መርቶ ከዚያ አወጣቸው። BSB BSB: The God of the people of Israel chose our fathers. He made them into a great people during their stay in Egypt, and with an uplifted arm He led them out of that land.
18 ULB ለአርባ ዓመታት ገደማ በምድረ በዳ ታገሣቸው። BSB BSB: He endured their conduct for about forty years in the wilderness.
19 ULB በከነዓን ምድርም ሰባት ሕዝቦችን ካጠፋ በኋላ፣ ምድራቸውን ለሕዝባችን ርስት አድርጎ ሰጠ። BSB BSB: And having vanquished seven nations in Canaan, He gave their land to His people as an inheritance.
20 ULB እነዚህ ሁነቶች ሁሉ በአራት መቶ ሃምሳ ዓመታት ውስጥ ተፈጸሙ። ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ በኋላ፣ እግዚአብሔር እስከ ነቢዩ ሳሙኤል ድረስ መሳፍንትን ሰጣቸው። BSB BSB: All this took about 450 years. After this, God gave them judges until the time of Samuel the prophet.
21 ULB ከዚህ በኋላ፣ ሕዝቡ ንጉሥ ይንገሥልን ብለው ጠየቁ፤ ስለሆነም፣ እግዚአብሔር ከብንያም ነገድ የሆነውን የቂስን ልጅ ሳኦልን ለአርባ ዓመታት ሰጣቸው። BSB BSB: Then the people asked for a king, and God gave them Saul son of Kish, from the tribe of Benjamin, who ruled forty years.
22 ULB ከዚያም እግዚአብሔር እርሱን ከንጉሥነት ከሻረው በኋላ፣ ንጉሣቸው እንዲሆን ዳዊትን አስነሣ። እግዚአብሔር፣ ‘እንደ ልቤ የሆነውን የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ፤ እርሱ እኔ የምፈልገውን ሁሉ ያደርጋል’ በማለት ስለ ዳዊት ተናግሮ ነበር። BSB BSB: After removing Saul, He raised up David as their king and testified about him: ‘I have found David son of Jesse a man after My own heart; he will carry out My will in its entirety.’
23 ULB ከዚህም ሰው ዘር እግዚአብሔር ተስፋ እንደ ሰጠ አዳኝ ኢየሱስን ለእስራኤል አመጣ። BSB BSB: From the descendants of this man, God has brought to Israel the Savior Jesus, as He promised.
24 ULB ይህ መሆን የጀመረው ኢየሱስ ከመምጣቱ በፊት፣ ዮሐንስ መጀመሪያ ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የንስሐን ጥምቀት ባወጀ ጊዜ ነው። BSB BSB: Before the arrival of Jesus, John preached a baptism of repentance to all the people of Israel.
25 ULB ዮሐንስ ሥራውን እንደ ጨረሰ እንዲህ አለ፤ ‘ማን እንደ ሆንሁ ታስባላችሁ? እኔ እርሱ አይደለሁም። ነገር ግን ስሙ፤ የጫማውን ማሰሪያ መፍታት ከማይገባኝ ከእኔ በኋላ እርሱ ይመጣል።’ BSB BSB: As John was completing his course, he said, ‘Who do you suppose I am? I am not that One. But there is One coming after me whose sandals I am not worthy to untie.’
27 ULB በኢየሩሳሌም የሚኖሩ፣ አለቆቻቸውም በእርግጥ ኢየሱስን አላወቁትም፤ በየሰንበቱ የሚነበበውን የነቢያትን ድምፅም በእውነት አልተረዱም፤ ስለ ሆነም በኢየሱስ ላይ ሞት በመፍረድ የነቢያትን ቃል ፈጸሙ። BSB BSB: The people of Jerusalem and their rulers did not recognize Jesus, yet in condemning Him they fulfilled the words of the prophets that are read every Sabbath.
28 ULB ምንም እንኳ በእርሱ ላይ ለሞት የሚያበቃ ምክንያት ባያገኙም፣ እንዲገድለው ጲላጦስን ለመኑት። BSB BSB: And though they found no ground for a death sentence, they asked Pilate to have Him executed.
29 ULB ስለ እርሱ የተጻፈውን ሁሉ በፈጸሙ ጊዜም፣ ከዕንጨት ላይ አውርደው በመቃብር አኖሩት። BSB BSB: When they had carried out all that was written about Him, they took Him down from the tree and laid Him in a tomb.
30 ULB እግዚአብሔር ግን ከሙታን አስነሣው። BSB BSB: But God raised Him from the dead,
31 ULB ከእርሱ ጋር ከገሊላ ወደ ኢየሩሳሌም የወጡት ብዙዎች ለአያሌ ቀናት ዐዩት። እነዚህ ሰዎች አሁን ለሕዝቡ የሚናገሩ የእርሱ ምስክሮች ናቸው። BSB BSB: and for many days He was seen by those who had accompanied Him from Galilee to Jerusalem. They are now His witnesses to our people.
32 ULB ስለ ሆነም እኛ ለአባቶቻችን ስለ ተሰጠው ተስፋ የሚናገር የምሥራች እናመጣላችኋለን፤ BSB BSB: And now we proclaim to you the good news: What God promised our fathers
33 ULB ኢየሱስን ከሙታን በማስነሣት እግዚአብሔር እነዚህን ተስፋዎች ለእኛ ለልጆቻቸው ጠብቆአል። ይህም ደግሞ በሁለተኛው መዝሙር፦ ‘አንተ ልጄ ነህ፣ እኔ ዛሬ ወለድሁህ’ ተብሎ የተጻፈ ነው።’ BSB BSB: He has fulfilled for us, their children, by raising up Jesus. As it is written in the second Psalm: ‘You are My Son; today I have become Your Father.’
34 ULB ደግሞም ሥጋው እንዳይበሰብስ ከሙታን እንዳስነሣው፦ ‘የተቀደሰውንና እውነተኛውን የዳዊት በረከት እሰጥሃለሁ’ ብሎ ተናግሯል። BSB BSB: In fact, God raised Him from the dead, never to see decay. As He has said: ‘I will give you the holy and sure blessings promised to David.’
35 ULB በሌላ መዝሙርም፣ ‘ቅዱስህ መበስበስን እንዲያይ አትፈቅድም’ የሚለው ስለዚህ ነው። BSB BSB: So also, He says in another Psalm: ‘You will not let Your Holy One see decay.’
36 ULB ዳዊትም በዘመኑ የእግዚአብሔርን ዐሳብ አገልግሎ አንቀላፋ፤ ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ፤ መበስበስንም ዐየ። BSB BSB: For when David had served God’s purpose in his own generation, he fell asleep. His body was buried with his fathers and saw decay.
37 ULB እግዚአብሔር ያስነሣው ኢየሱስ ግን መበስበስን አላየም። BSB BSB: But the One whom God raised from the dead did not see decay.
38 ULB ስለ ሆነም ወንድሞች ሆይ፣ በዚህ ሰው በኩል የኃጢአት ይቅርታ እንደ ተሰበከላችሁ ይህ ለእናንተ የታወቀ ይሁን። BSB BSB: Therefore let it be known to you, brothers, that through Jesus the forgiveness of sins is proclaimed to you.
39 ULB በሙሴም ሕግ እንድትጸድቁበት ከማይቻላችሁ ሁሉ፣ በእርሱ የሚያምን ሁሉ ጸድቆአል። BSB BSB: Through Him everyone who believes is justified from everything from which you could not be justified by the law of Moses.
40 ULB እንግዲያው ነቢያት እንዲህ ሲሉ የተናገሩለት ነገር እንዳይደርስባችሁ ተጠንቀቁ፦ BSB BSB: Watch out, then, that what was spoken by the prophets does not happen to you:
41 ULB ‘እናንተ የምትንቁ፣ ተመልከቱ፤ ተደነቁ፣ ጥፉም፤ አንድ ስንኳ ቢነግራችሁ ከቶ የማታምኑትን ሥራ፣ በዘመናችሁ እሠራለሁና።’” BSB BSB: ‘Look, you scoffers, wonder and perish! For I am doing a work in your days that you would never believe, even if someone told you.’”
42 ULB ጳውሎስና በርናባስ እንደ ወጡ፣ በሚቀጥለው ሰንበት ይህንኑ ቃል ደግመው እንዲናገሩ ሕዝቡ ለመኑአቸው። BSB BSB: As Paul and Barnabas were leaving the synagogue, the people urged them to continue this message on the next Sabbath.
43 ULB የምኵራቡ ስብሰባ እንዳበቃም፣ ከአይሁድና ወደ ይሁዲነት ከገቡ ከሚያመልኩ ብዙዎቹ፣ በእግዚአብሔር ጸጋ እንዲጸኑ የመከሩአቸውን ጳውሎስና በርናባስን ተከተሉአቸው። BSB BSB: After the synagogue was dismissed, many of the Jews and devout converts to Judaism followed Paul and Barnabas, who spoke to them and urged them to continue in the grace of God.
44 ULB በሚቀጥለውም ሰንበት፣ ጥቂቶች ሲቀሩ፣ መላው ከተማ የጌታን ቃል ለመስማት አንድ ላይ ተሰበሰበ። BSB BSB: On the following Sabbath, nearly the whole city gathered to hear the word of the Lord.
45 ULB አይሁድ ሕዝቡን ባዩ ጊዜ፣ ቅንዓት ሞላባቸውና ጳውሎስ የተናገረውን ተቃወሙ፣ ሰደቡትም። BSB BSB: But when the Jews saw the crowds, they were filled with jealousy, and they blasphemously contradicted what Paul was saying.
46 ULB ጳውሎስና በርናባስ በድፍረት ተናገሩ፤ እንዲህም አሉ፤ “የእግዚአብሔር ቃል መጀመሪያ ለእናንተ መነገሩ አስፈላጊ ነበር። ቃሉን ከራሳችሁ ስትገፉትና ለዘላለም ሕይወት የተገባችሁ እንዳልሆናችሁ ራሳችሁን ስትቈጥሩ ዐይተናችሁ፣ ወደ አሕዛብ ዘወር የምንል መሆናችንን ተመልከቱ። BSB BSB: Then Paul and Barnabas answered them boldly: “It was necessary to speak the word of God to you first. But since you reject it and do not consider yourselves worthy of eternal life, we now turn to the Gentiles.
47 ULB ጌታ፣ ‘እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ለድነት ትሆን ዘንድ፣ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ’” በማለት አዞናልና። BSB BSB: For this is what the Lord has commanded us: ‘I have made you a light for the Gentiles, to bring salvation to the ends of the earth.’”
48 ULB አሕዛብ ይህን እንደ ሰሙ ደስ አላቸው። የጌታንም ቃል አከበሩ። ለዘላለም ሕይወት የተመረጡትም አመኑ። BSB BSB: When the Gentiles heard this, they rejoiced and glorified the word of the Lord, and all who were appointed for eternal life believed.
49 ULB የጌታም ቃል በአገሩ ሁሉ ተስፋፋ። BSB BSB: And the word of the Lord spread throughout that region.
50 ULB አይሁድ ግን የሚያመልኩትን ታዋቂ ሴቶችን፣ የከተማይቱን ታላላቅ ወንዶችንም ቀሰቀሱ። በጳውሎስና በበርናባስ ላይም ስደት አስነሥተው ከከተማቸው ዳርቻ ወዲያ አውጥተው ጣሏቸው። BSB BSB: The Jews, however, incited the religious women of prominence and the leading men of the city. They stirred up persecution against Paul and Barnabas and drove them out of their district.
51 ULB ጳውሎስና በርናባስ ግን የእግራቸውን ትቢያ አራገፉባቸው። ከዚያም ወደ ኢቆንዮን ከተማ ሄዱ። BSB BSB: So they shook the dust off their feet in protest against them and went to Iconium.
52 ULB ደቀ መዛሙርቱም ደስታና መንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ነበር። BSB BSB: And the disciples were filled with joy and with the Holy Spirit.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.