2 ULB ጳውሎስና በርናባስም ከእነርሱ ጋር ጥልና ክርክር በገጠሙ ጊዜ፣ ጳውሎስና በርናባስ እንዲሁም ሌሎች ሰዎች ስለዚህ ጉዳይ በኢየሩሳሌም ወደ ነበሩ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች እንዲወጡ ወንድሞች ወሰኑ። BSB BSB: And after engaging these men in sharp debate, Paul and Barnabas were appointed, along with some other believers, to go up to Jerusalem to see the apostles and elders about this question.
3 ULB ስለዚህ በቤተ ክርስቲያን ተልከው፣ በፊንቄና በሰማርያ በኩል አድርገው ሲሄዱ፣ የአሕዛብን መለወጥ እያወጁ ዐለፉ፤ ይህም ወንድሞችን ሁሉ እጅግ ደስ አሰኛቸው። BSB BSB: Sent on their way by the church, they passed through Phoenicia and Samaria, recounting the conversion of the Gentiles and bringing great joy to all the brothers.
4 ULB ወደ ኢየሩሳሌም በመጡ ጊዜም፣ ቤተ ክርስቲያን፣ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች በደስታ ተቀበሏቸው፤ እነ ጳውሎስም እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ሆኖ የሠራውን ሁሉ ነገሯቸው። BSB BSB: On their arrival in Jerusalem, they were welcomed by the church and apostles and elders, to whom they reported all that God had done through them.
5 ULB ከፈሪሳውያን ወገን ያመኑ አንዳንድ ሰዎች ግን ተነሥተው፣ «እነርሱን መግረዝና የሙሴንም ሕግ እንዲጠብቁ ማዘዝ ያስፈልጋል» አሉ። BSB BSB: But some believers from the party of the Pharisees stood up and declared, “The Gentiles must be circumcised and required to obey the law of Moses.”
6 ULB ስለዚህ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ይህን ጉዳይ ለማየት ተሰበሰቡ። BSB BSB: So the apostles and elders met to look into this matter.
7 ULB ከብዙ ጭቅጭቅ በኋላ ጴጥሮስ ተነሥቶ ቆመና እንዲህ አለ፦ «ወንድሞች ሆይ፣ አሕዛብ የወንጌልን ቃል ከአፌ እንዲሰሙና እንዲያምኑ፣ እግዚአብሔር ከጥቂት ጊዜያት በፊት ከእናንተ መካከል እኔን እንደ መረጠኝ ታውቃላችሁ።» BSB BSB: After much discussion, Peter got up and said to them, “Brothers, you know that in the early days God made a choice among you that the Gentiles would hear from my lips the message of the gospel and believe.
8 ULB ልብን የሚያውቅ አምላክ፣ ለእኛ እንዳደረገው ሁሉ፣ ለእነርሱም መንፈስ ቅዱስን በመስጠት መሰከረላቸው፤ BSB BSB: And God, who knows the heart, showed His approval by giving the Holy Spirit to them, just as He did to us.
9 ULB በእኛና በእነርሱ መካከልም ልባቸውን በእምነት በማንጻት ልዩነት አላደረገም። BSB BSB: He made no distinction between us and them, for He cleansed their hearts by faith.
10 ULB እንግዲህ አባቶቻችንና እኛ መሽከም ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ በመጫን ለምን እግዚአብሔርን ትፈታተናላችሁ? BSB BSB: Now then, why do you test God by placing on the necks of the disciples a yoke that neither we nor our fathers have been able to bear?
11 ULB ነገር ግን እኛም በጌታ በኢየሱስ ጸጋ እንደ እነርሱ እንደምንድን እናምናለን።» BSB BSB: On the contrary, we believe it is through the grace of the Lord Jesus that we are saved, just as they are.”
12 ULB በርናባስና ጳውሎስ እግዚአብሔር በእነርሱ አማካይነት በአሕዛብ መካከል ስለ ሠራው ምልክትና ድንቅ ሲናገሩ፣ ሕዝቡ ሁሉ በጸጥታ አደመጡ። BSB BSB: The whole assembly fell silent as they listened to Barnabas and Paul describing the signs and wonders God had done among the Gentiles through them.
14 ULB እግዚአብሔር ለስሙ የሚሆንን ሕዝብ ከእነርሱ መካከል ይወስዱ ዘንድ፣ አሕዛብን በመጀመሪያ በጸጋ እንደ ረዳ ስምዖን ተናግሮአል። BSB BSB: Simon has told us how God first visited the Gentiles to take from them a people to be His own.
15 ULB የነቢያት ቃል ከዚህ ጋር ይስማማል እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፤ BSB BSB: The words of the prophets agree with this, as it is written:
16 ULB ከእነዚህ ነገሮች በኋላ እመለሳለሁ፤ ፍርስራሹንም መልሼ እተክላለሁ፤ እንደገናም ዐድሳለሁ፤ BSB BSB: ‘After this I will return and rebuild the fallen tent of David. Its ruins I will rebuild, and I will restore it,
17 ULB ይኸውም የተረፉት ሰዎችና በስሜ የተጠሩ አሕዛብ፣ እግዚአብሔርን እንዲፈልጉ ነው። BSB BSB: so that the remnant of men may seek the Lord, and all the Gentiles who are called by My name, says the Lord who does these things
18 ULB እነዚህ ጥንታዊ ነገሮች እንዲታወቁ የሚያደርግ ጌታ የሚለው ይህን ነው። BSB BSB: that have been known for ages.’
20 ULB ነገር ግን በጣዖታት ከመርከስ፣ ከዝሙት፣ ከታነቀና ከደም እንዲርቁ እንጻፍላቸው። BSB BSB: Instead, we should write and tell them to abstain from food polluted by idols, from sexual immorality, from the meat of strangled animals, and from blood.
22 ULB ስለዚህ በርስያን የተባለው ይሁዳንና ሲላስን የቤተ ክርስቲያን መሪዎች አድርገው እንዲመርጡና፣ ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ እንዲልኳቸው ለሐዋርያትና ለሽማግሌዎች፣ ከቤተ ክርስቲያን ሁሉ ጋር መልካም መስሎ ታያቸው። BSB BSB: Then the apostles and elders, with the whole church, decided to select men from among them to send to Antioch with Paul and Barnabas. They chose Judas called Barsabbas and Silas, two leaders among the brothers,
23 ULB እንዲህም ብለው ጻፉ፤ «ለሐዋርያት፣ ለሽማግሌዎችና ወንድሞች፣ እንዲሁም በአንጾኪያ፣ በሶርያና በኪልቅያ ለሚገኙ ከአሕዛብ ወገን ለሆኑ ወንድሞች፣ ሰላም ለእናንተ ይሁን። BSB BSB: and sent them with this letter: The apostles and the elders, your brothers, To the brothers among the Gentiles in Antioch, Syria, and Cilicia: Greetings.
24 ULB እኛ ያላዘዝናቸው አንዳንድ ሰዎች ከእኛ ዘንድ መጥተው ነፍሳችሁን በሚያስጨንቅ ትምህርት እንዳስቸገሩአችሁ ሰምተናል። BSB BSB: It has come to our attention that some went out from us without our authorization and unsettled you, troubling your minds by what they said.
25 ULB ስለዚህ በአንድ ልብ ሆነን ሰዎችን መርጠን ከወዳጆቻችን ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር ወደ እናንተ መላክ ለሁላችንም መልካም መስሎ ታየን፤ BSB BSB: So we all agreed to choose men to send to you along with our beloved Barnabas and Paul,
26 ULB እነዚህ ሰዎች ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሲሉ ለሕይወታቸው እንኳ ያልሣሡ ናቸው። BSB BSB: men who have risked their lives for the name of our Lord Jesus Christ.
27 ULB ይህንኑ እንዲነግሯችሁ ይሁዳንና ሲላስን ወደ እናንተ ልከናል፤ BSB BSB: Therefore we are sending Judas and Silas to tell you in person the same things we are writing.
29 ULB ይኸውም ለጣዖት ከተሠዋ፣ ከደም፣ ከታነቀ፣ ከዝሙትም እንድትርቁ ነው። ራሳችሁን ከእነዚህ ብትጠብቁ መልካም ይሆንላችኋል፤ ደኅና ሁኑ።» BSB BSB: You must abstain from food sacrificed to idols, from blood, from the meat of strangled animals, and from sexual immorality. You will do well to avoid these things. Farewell.
30 ULB ከዚያም ተሰናብተው ወደ አንጾኪያ ወረዱ፤ ሕዝቡንም ሰብስበው ደብዳቤውን ሰጡአቸው። BSB BSB: So the men were sent off and went down to Antioch, where they assembled the congregation and delivered the letter.
31 ULB ደብዳቤውንም አንብበው ስለ ተጽናኑ በጣም ደስ አላቸው። BSB BSB: When the people read it, they rejoiced at its encouraging message.
32 ULB ደግሞም ይሁዳና ሲላስ ነቢያት ስለ ነበሩ፣ወንድሞችን በብዙ ቃል በመምከር አበረታቱአቸው። BSB BSB: Judas and Silas, who themselves were prophets, said much to encourage and strengthen the brothers.
33 ULB በዚያም ጥቂት ጊዜ ከተቀመጡ በኋላ፣ከወንድሞች በሰላም ተሰናብተው ወደ ላኳቸው ሄዱ። BSB BSB: After spending some time there, they were sent off by the brothers in peace to return to those who had sent them.
34 ULB ሲላስ ግን እዚያው መቆየት መልካም መስሎ ታየው። BSB BSB: Not in the BSB
35 ULB ጳውሎስና በርናባስ ግን የጌታን ቃል ባስተማሩበትና በሰበኩበት በአንጾኪያ ከሌሎች ብዙ ሰዎች ጋር ተቀመጡ። BSB BSB: But Paul and Barnabas remained at Antioch, along with many others, teaching and preaching the word of the Lord.
36 ULB ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ ጳውሎስ በርናባስን፣ «ተመልሰን የጌታን ቃል በሰበክንበት ከተማ ሁሉ ያሉትን ወንድሞች እንጐብኝ፤ በምን ሁኔታ እንዳሉም እንወቅ» አለ። BSB BSB: Some time later Paul said to Barnabas, “Let us go back and visit the brothers in every town where we proclaimed the word of the Lord, to see how they are doing.”
37 ULB በርናባስም ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስን ደግሞ ከእነሱ ጋር ይዞ ለመሄድ ፈለገ። BSB BSB: Barnabas wanted to take John, also called Mark.
38 ULB ጳውሎስ ግን ማርቆስን ይዞ መሄድ አልፈለገም፤ ምክንያቱም ማርቆስ ከዚህ ቀደም ከእነርሱ ጋር ለሥራ በመሄድ ፈንታ፣ በጵንፍልያ ተለይቶአቸው ቀርቶ ነበር። BSB BSB: But Paul thought it best not to take him, because he had deserted them in Pamphylia and had not accompanied them in the work.
39 ULB በመካከላቸው ከፍተኛ አለምስማማት ስለ ተፈጠረም፣ ተለያዩ፤ በርናባስም ማርቆስን ይዞ ወደ ቆጵሮስ በመርከብ ሄደ። BSB BSB: Their disagreement was so sharp that they parted company. Barnabas took Mark and sailed for Cyprus,
40 ULB ጳውሎስ ግን ሲላስን መረጠ፤ ወንድሞች ለጌታ ጸጋ አደራ ከሰጡት በኋላ፣ ተለይቶአቸው ሄደ። BSB BSB: but Paul chose Silas and left, commended by the brothers to the grace of the Lord.
41 ULB ከዚያም አብያተ ክርስቲያናትን እያበረታታ በሶርያና በኪልቅያ ይዞር ነበር። BSB BSB: And he traveled through Syria and Cilicia, strengthening the churches.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.