1 ULB አጵሎስ በቆሮንቶስ በነበረ ጊዜ፣ ጳውሎስ በላይኛው አገር አድርጎ ወደ ኤፌሶን ከተማ መጣ፤ በዚያም አንዳንድ ደቀ መዛሙርትን አገኘ። BSB BSB: While Apollos was at Corinth, Paul passed through the interior and came to Ephesus. There he found some disciples
2 ULB ጳውሎስም፣ “ባመናችሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀብላችኋል?” አላቸው። እነርሱም፣ “አልተቀበልንም፤ እንዲያውም መንፈስ ቅዱስ መኖሩን አልሰማንም” አሉት። BSB BSB: and asked them, “Did you receive the Holy Spirit when you became believers?” “No,” they answered, “we have not even heard that there is a Holy Spirit.”
3 ULB ጳውሎስም፣ “ታዲያ፣ በምን ተጠመቃችሁ?” አላቸው። እነርሱም፣ “የተጠመቅነው በዮሐንስ ጥምቀት ነው” አሉት። BSB BSB: “Into what, then, were you baptized?” Paul asked. “The baptism of John,” they replied.
4 ULB ጳውሎስም መልሶ፣ “ዮሐንስ ያጠመቀው በንስሓ ጥምቀት ነው። ሰዎች ከእርሱ በኋላ በሚመጣው፣ በኢየሱስ ማመን እንደሚገባቸውም ነገራቸው” አለ። BSB BSB: Paul explained: “John’s baptism was a baptism of repentance. He told the people to believe in the One coming after him, that is, in Jesus.”
5 ULB ሕዝቡ ይህን ሲሰሙ፣ በጌታ ኢየሱስ ስም ተጠመቁ። BSB BSB: On hearing this, they were baptized into the name of the Lord Jesus.
6 ULB ጳውሎስም እጆቹን በሰዎቹ ላይ በጫነ ጊዜ፣ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው፤ እነርሱም በልዩ ቋንቋ መናገርና መተንበይ ጀመሩ። BSB BSB: And when Paul laid his hands on them, the Holy Spirit came upon them, and they spoke in tongues and prophesied.
7 ULB ቍጥራቸውም ዐሥራ ሁለት ያህል ነበረ። BSB BSB: There were about twelve men in all.
8 ULB ጳውሎስ ከዚህ በኋላ ወደ ምኵራብ እየገባ ሦስት ወር ያህል በድፍረት ይናገር ነበር፤ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እየገለጠ ሰዎችን ያስረዳ ነበር። BSB BSB: Then Paul went into the synagogue and spoke boldly there for three months, arguing persuasively about the kingdom of God.
9 ULB አንዳንድ አይሁድ ግን ልባቸውን አደንድነው በመቃወም፣ በሕዝቡ ፊት የክርስቶስን መንገድ ተሳደቡ፤ ስለዚህ ጳውሎስ ትቶአቸው ሄደ፤ ያመኑትንም ከእነርሱ አራቀ። ጢራኖስ በሚባል የትምህርት አዳራሽም በየዕለቱ ንግግር ያደርግ ጀመር። BSB BSB: But when some of them stubbornly refused to believe and publicly maligned the Way, Paul took his disciples and left the synagogue to conduct daily discussions in the lecture hall of Tyrannus.
10 ULB ይህም፣ በእስያ የሚኖሩ አይሁድና ግሪኮችም ሁሉ የጌታን ቃል እስኪሰሙ ድረስ፣ ሁለት ዓመት ቀጠለ። BSB BSB: This continued for two years, so that everyone who lived in the province of Asia, Jews and Greeks alike, heard the word of the Lord.
11 ULB እግዚአብሔር በጳውሎስ እጅ ታላላቅ ተአምራትን ያደርግ ነበር፤ BSB BSB: God did extraordinary miracles through the hands of Paul,
12 ULB ስለዚህ የጳውሎስ አካል የነካው ጨርቅ ወይም መሐረብ ሲወሰድ፣ የታመሙት ይፈወሱ፣ አጋንንትም ከሰዎች ይወጡ ነበር። BSB BSB: so that even handkerchiefs and aprons that had touched him were taken to the sick, and the diseases and evil spirits left them.
13 ULB አጋንንት እናስወጣለን እያሉ ከቦታ ቦታ የሚዞሩ አይሁድ ነበሩ፤ እነርሱም የኢየሱስን ስም ለገዛ ጥቅማቸው ለማዋል፣ በክፉ መናፍስት ላይ እየጠሩ፣ “እንድትወጡ ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ እናዛችኋለን” ይሉ ነበር። BSB BSB: Now there were some itinerant Jewish exorcists who tried to invoke the name of the Lord Jesus over those with evil spirits. They would say, “I command you by Jesus, whom Paul proclaims.”
14 ULB ይህን ያደረጉትም የአይሁድ የካህናት አለቃ የነበረው የአስቄዋ ሰባት ወንድ ልጆች ነበሩ። BSB BSB: Seven sons of Sceva, a Jewish chief priest, were doing this.
15 ULB ክፉው መንፈስም፣ “ኢየሱስን ዐውቀዋለሁ፤ ጳውሎስንም ዐውቃለሁ፤ ለመሆኑ እናንተ እነማን ናችሁ?” ብለው መለሱላቸው። BSB BSB: But one day the evil spirit responded, “Jesus I know, and I know about Paul, but who are you?”
16 ULB ክፉ መንፈስ ያለበትም ሰው ዘሎ ያዛቸው፤ አሸንፏቸውም ደበደባቸው። ከዚያም ቤት ቈስለው ዕራቁታቸውን ሸሹ። BSB BSB: Then the man with the evil spirit jumped on them and overpowered them all. The attack was so violent that they ran out of the house naked and wounded.
17 ULB ይህም በኤፌሶን ይኖሩ በነበሩ አይሁድና ግሪኮችም ዘንድ ሁሉ ታወቀ። እነርሱም ሁሉ በፍርሀት ተዋጡ፤ የጌታ ኢየሱስም ስም ተከበረ። BSB BSB: This became known to all the Jews and Greeks living in Ephesus, and fear came over all of them. So the name of the Lord Jesus was held in high honor.
19 ULB አስማተኞችም የጥንቈላ መጻሕፍታቸውን ሰብስበው እያመጡ በሰው ሁሉ ፊት አቃጠሉ፤ ዋጋቸውም ሲተመን ሃምሳ ሺህ ብር ሆነ። BSB BSB: And a number of those who had practiced magic arts brought their books and burned them in front of everyone. When the value of the books was calculated, the total came to fifty thousand drachmas.
20 ULB በዚህም መሠረት የጌታ ቃል በስፋትና በኀይል ተሠራጨ። BSB BSB: So the word of the Lord powerfully continued to spread and prevail.
21 ULB ጳውሎስ በኤፌሶን የነበረውን አገልግሎቱን ከፈጸመ በኋላ፣ በመቄዶንያና በአካይያ አድርጎ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ በመንፈስ ቅዱስ ሆኖ ወሰነ፤ ደግሞም፣ “እዚያ ከደረስሁ በኋላም፣ ሮሜን ማየት ይገባኛል” አለ። BSB BSB: After these things had happened, Paul resolved in the Spirit to go to Jerusalem, passing through Macedonia and Achaia. “After I have been there,” he said, “I must see Rome as well.”
22 ULB ሲረዱት ከነበሩት ደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን፣ ጢሞቴዎስንና ኤርስጦንን ወደ መቄዶንያ ላካቸው። እርሱ ራሱ ግን ጥቂት ጊዜ በእስያ ቆየ። BSB BSB: He sent two of his helpers, Timothy and Erastus, to Macedonia, while he stayed for a time in the province of Asia.
23 ULB በዚህ ጊዜ የጌታን መንገድ በተመለከተ በኤፌሶን ትልቅ ሁከት ተነሣ። BSB BSB: About that time there arose a great disturbance about the Way.
25 ULB ስለዚህ በዚህ ሙያ ላይ የተሰማሩትን ብዙ ሠራተኞች አንድ ላይ ሰብስቦ፣ “ሰዎች ሆይ፤ በዚህ ሙያችን ብዙ ገንዘብ እንደምናገኝ ታውቃላችሁ። BSB BSB: Demetrius assembled the craftsmen, along with the workmen in related trades. “Men,” he said, “you know that this business is our source of prosperity.
26 ULB ይህ ጳውሎስ በኤፌሶን ብቻ ሳይሆን፣ ከብዙ በጥቂቱ በእስያ ሁሉ አብዛኛውን ሕዝብ በቃላት እያባበለ ከእኛ ማራቁን እያያችሁና እየሰማችሁ ነው። በእጅ የሚሠሩ አማልክት የሉም እያላቸው ነው። BSB BSB: And you can see and hear that not only in Ephesus, but in nearly the whole province of Asia, this Paul has persuaded a great number of people to turn away. He says that man-made gods are no gods at all.
27 ULB የእኛ ሞያዊ ጥበብ አላስፈላጊ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ የታላቅዋ አምላክ የዲያና ቤተ መቅደስም እንደ ከንቱ ነገር የመቍጠር አደጋ ያሠጋል፤ እስያ ሁሉና ዓለሙ የሚያመልካት ይህች አምላክም ዝናዋን ታጣለች።” BSB BSB: There is danger not only that our business will fall into disrepute, but also that the temple of the great goddess Artemis will be discredited and her majesty deposed—she who is worshiped by all the province of Asia and the whole world.”
28 ULB ሕዝቡም ይህን በሰሙ ጊዜ፣ በቍጣ ተሞልተው፣ “የኤፌሶንዋ ዲያና ታላቅ ናት” እያሉ ጮኹ። BSB BSB: When the men heard this, they were enraged and began shouting, “Great is Artemis of the Ephesians!”
30 ULB ጳውሎስ ወደ ሕዝቡ ሊደባለቅ ፈልጎ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ከለከሉት። BSB BSB: Paul wanted to go before the assembly, but the disciples would not allow him.
31 ULB ደግሞም፣ የጳውሎስ ወዳጆች የነበሩ አንዳንድ የአካባቢ ሹሞች ጳውሎስ ወደ ቲያትር ማሳያ ቦታ እንዳይገባ መልእክት ላኩበት። BSB BSB: Even some of Paul’s friends who were officials of the province of Asia sent word to him, begging him not to venture into the theatre.
32 ULB ሕዝቡ ሁሉ ግራ ተጋብቶ ነበርና፣ አንዳንዶቹ ስለ አንድ ነገር ሲጮኹ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ስለ ሌላ ነገር ይጮኹ ነበር። አብዛኛዎቹ ደግሞ ለምን ተሰብስበው እንደ ወጡ እንኳ አያውቁም ነበር። BSB BSB: Meanwhile the assembly was in turmoil. Some were shouting one thing and some another, and most of them did not even know why they were there.
33 ULB አይሁድም እስክንድሮስን ገፋፍተው ወደ ሕዝቡ ፊት አወጡት። እስክንድሮስ ለሕዝቡ በእጅ ምልክት እያሳየ ሊያስረዳቸው ሞከረ። BSB BSB: The Jews in the crowd pushed Alexander forward to explain himself, and he motioned for silence so he could make his defense to the people.
34 ULB ሕዝቡም አይሁዳዊ መሆኑን በተረዱ ጊዜ ሁሉም በአንድ ድምፅ፣ “የኤፌሶንዋ ዲያና ታላቅ ናት” እያሉ ለሁለት ሰዓት ያህል ጮኹ። BSB BSB: But when they realized that he was a Jew, they all shouted in unison for about two hours: “Great is Artemis of the Ephesians!”
36 ULB እንግዲህ ይህ የማይካድ ነገር መሆኑ ከታያችሁ፣ ጸጥ ልትሉ፣ አንዳች ነገርም በችኰላ ልታደርጉ አይገባም፤ BSB BSB: Since these things are undeniable, you ought to be calm and not do anything rash.
37 ULB ምክንያቱም አብያተ መቅደስን ያልሰረቁ፣ አማልክታችንንም ያልሰደቡ እነዚህን ሰዎች ወደዚህ ፍርድ ቤት አምጥታችኋል። BSB BSB: For you have brought these men here, though they have neither robbed our temple nor blasphemed our goddess.
38 ULB ስለዚህ ድሜጥሮስና ከእርሱ ጋር ያሉ አንጥረኞች የሚከሱት ሰው ካለ፣ ፍርድ ቤቱ ክፍት ነው፤ ዳኞችም አሉ፤ እዚያ እርስ በርስ ይካሰሱ። BSB BSB: So if Demetrius and his fellow craftsmen have a complaint against anyone, the courts are open and proconsuls are available. Let them bring charges against one another there.
39 ULB ስለ ሌላ ጉዳይ የምትፈልጉት ነገር ካለ ግን፣ ችግሩ በመደበኛው ጉባኤ ይፈታል፤ BSB BSB: But if you are seeking anything beyond this, it must be settled in a legal assembly.
40 ULB ምክንያቱም በዛሬው ቀን የነበረው ዐመፅ ሳያስጠይቀን አይቀርም። የነበረው ግርግር መንሥኢ የለውም፤ እንዲህ ነው ብለን ልንገልጸውም አንችልም።” BSB BSB: For we are in jeopardy of being charged with rioting for today’s events, and we have no justification to account for this commotion.”
41 ULB ጸሓፊው ይህን ተናግሮ ጉባኤውን አሰናበተው። BSB BSB: After he had said this, he dismissed the assembly.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.