1 ULB ወደ ኢጣሊያ በመርከብ እንድንሄድ በተወሰነ ጊዜ፣ ጳውሎስንና ሌሎችን እስረኞች የአውግስጦስ ክፍለ ጦር አባል ለሆነ ዩልዮስ ለተባለ የመቶ አለቃ አስረከቡአቸው። BSB BSB: When it was decided that we would sail for Italy, Paul and some other prisoners were handed over to a centurion named Julius, who belonged to the Imperial Regiment.
2 ULB እኛም ከአድራሚጥዮን ተነሥተን በእስያ ጠረፍ ሊሄድ በተዘጋጀ መርከብ ላይ ተሳፍረን ወደ ባሕር ተጓዝን። በመቄዶንያ ካለችው ተሰሎንቄ የሆነው አርስጥሮኮስም ከእኛ ጋር ሄደ። BSB BSB: We boarded an Adramyttian ship about to sail for ports along the coast of Asia, and we put out to sea. Aristarchus, a Macedonian from Thessalonica, was with us.
3 ULB በማግስቱ ወደ ሲዶን ከተማ ደርሰን፣ ከመርከብ ወረድን፤ እዚያም ዩልዮስ ለጳውሎስ ቸርነት አደረገለት፤ ወደ ወዳጆቹ እንዲሄድና እንክብካቤ እንዲያደርጉለትም ፈቀደለት። BSB BSB: The next day we landed at Sidon, and Julius treated Paul with consideration, allowing him to visit his friends and receive their care.
4 ULB ከዚያም ተነሥተን ወደ ባሕር ሄድን፤ ነፋስ ይነፍስብን ስለ ነበር፣ በመርከብ ሆነን ነፋሱ በማያገኛት በቆጵሮስ ደሴት ዙሪያ ተጓዝን። BSB BSB: After putting out from there, we sailed to the lee of Cyprus because the winds were against us.
5 ULB በኪልቅያና በጵንፍልያ አጠገብ ያለውን ባሕር ከተሻገርን በኋላም፣ የሉቅያ ከተማ ወደ ሆነው ወደ ሙራ ደረስን። BSB BSB: And when we had sailed across the open sea off the coast of Cilicia and Pamphylia, we came to Myra in Lycia.
6 ULB በዚያም፣ የመቶ አለቃው ከእስክንድርያ ወደ ኢጣሊያ የሚሄድ መርከብ አግኝቶ አሳፈረን። BSB BSB: There the centurion found an Alexandrian ship sailing for Italy and put us on board.
7 ULB ብዙ ቀንም በዝግታ ተጓዝንና በመጨረሻ በችግር ወደ ቀኒዶስ ደረስን፤ ነፋሱም በዚያ መንገድ እንዳንሄድ ስለከለከለን፣ በሰልሙና አንጻር ያለችውን ቀርጤስን ተገን አድርገን ተጓዝን። BSB BSB: After sailing slowly for many days, we arrived off Cnidus. When the wind impeded us, we sailed to the lee of Crete, opposite Salmone.
8 ULB በላሲያ ከተማ አጠገብ ወዳለው መልካም ወደብ ወደ ተባለው ስፍራ እስከምንደርስ ድረስ በችግር በጠረፉ በኩል ተጓዝን። BSB BSB: After we had moved along the coast with difficulty, we came to a place called Fair Havens, near the town of Lasea.
9 ULB ብዙ ጊዜም አሳለፍን፤ የአይሁድ የጾም ወራት ደግሞ ዐልፎ ነበር፤ ጕዞውን መቀጠልም አደጋ የሚያስከትል ነበር። ስለዚህ ጳውሎስ አስጠነቀቃቸው፤ BSB BSB: By now much time had passed, and the voyage had already become dangerous because it was after the Fast. So Paul advised them,
10 ULB እንዲህም አለ፤ “እናንተ ሰዎች፣ አሁን የምናደርገው ጕዞ አደጋና ብዙ ጉዳት እንደሚኖርበት ይታየኛል፤ አደጋውም በመርከቡና በጭነቱ ብቻ ሳይሆን፣ በእኛም ሕይወት ላይ የሚደርስ ነው።” BSB BSB: “Men, I can see that our voyage will be filled with disaster and great loss, not only to ship and cargo, but to our own lives as well.”
11 ULB የመቶ አለቃው የሰማው ግን ጳውሎስ የተናገረውን ሳይሆን፣ በይበልጥ የመርከቡ አዛዥና ባለቤት ያሉትን ነው። BSB BSB: But contrary to Paul’s advice, the centurion was persuaded by the pilot and by the owner of the ship.
12 ULB ክረምቱን ለማሳለፍ ወደቡ ተስማሚ ስላልነበረ፣ አብዛኛዎቹ ተጓዦች የሚቻል ከሆነ ከዚያ ተነሥተን ፊንቄ ወደ ተባለችው ከተማ እንድንሄድና ክረምቱን እዚያ እንድናሳልፍ ምክር ሰጡን። ፊንቄ በሰሜን ምሥራቅና በደቡብ ምሥራቅ አንጻር የምትገኝ የቀርጤስ ወደብ ነች። BSB BSB: Since the harbor was unsuitable to winter in, the majority decided to sail on, hoping that somehow they could reach Phoenix to winter there. Phoenix was a harbor in Crete facing both southwest and northwest.
13 ULB የደቡቡ ነፋስ በቀስታ መንፈስ በጀመረ ጊዜ፣ መርከበኞቹ የፈለጉት እንደተከናወነላቸው ዐሰቡ። ስለዚህ ሸራውን አውርደው በባሕሩ ዳርቻ አቅራቢያ፣ በቀርጤስ በኩል አለፉ። BSB BSB: When a gentle south wind began to blow, they thought they had their opportunity. So they weighed anchor and sailed along, hugging the coast of Crete.
14 ULB ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን፣ የሰሜን ምሥራቅ ዐውሎ ነፋስ የተባለ ኃይለኛ ነፋስ ደሴቲቱን አቋርጦ በመምጣት ይነፍስብን ጀመረ፤ BSB BSB: But it was not long before a cyclone called the Northeaster swept down across the island.
15 ULB መርከቡም ወደ ፊት በተገፋና ነፋሱን መቋቋም ባልቻለ ጊዜ፣ ዝም ብለነው በነፋሱ እየተነዳን ሄድን። BSB BSB: Unable to head into the wind, the ship was caught up. So we gave way and let ourselves be driven along.
16 ULB ቄዳ የተባለችውን ትንሽ ደሴት ተተግነን ተጓዝን፤ በትልቅ ችግርም ሕይወት አድን ጀልባው ላይ መውጣት ቻልን። BSB BSB: Passing to the lee of a small island called Cauda, we barely managed to secure the lifeboat.
17 ULB መርከበኞቹ ጀልባውን ወደ መርከቡ ጎትተው አወጡት፤ ገመዱንም የመርከቡን ዙሪያ ለማሰር ተጠቀሙበት። ስርቲስ በምትባል አሸዋማ ስፍራ እንዳንወድቅ ፈርተው ነበር፤ ስለዚህ የባሕር ሸራውን አውርደው እየተነዱ ሄዱ። BSB BSB: After hoisting it up, the crew used ropes to undergird the ship. And fearing that they would run aground on the sandbars of Syrtis, they lowered the sea anchor and were driven along.
18 ULB ዐውሎ ነፋሱ በጣም ስላየለብን፣ በማግስቱ መርከበኞቹ የመርከቡን ጭነት ወደ ባሕር መጣል ጀመሩ። BSB BSB: We were tossed so violently that the next day the men began to jettison the cargo.
19 ULB በሦስተኛው ቀን መርከበኞቹ በመርከቡ የሚያገለግሉ ዕቃዎችን እያነሡ ጣሉ። BSB BSB: On the third day, they threw the ship’s tackle overboard with their own hands.
20 ULB ለብዙ ቀንም ፀሐይና ከዋክብት ብርሃናቸውን ባልሰጡንና ትልቁ ማዕበልም በወረደብን ጊዜ፣ አንድንም ብለን ተስፋ ቈረጥን። BSB BSB: When neither sun nor stars appeared for many days and the great storm continued to batter us, we abandoned all hope of being saved.
21 ULB ተጓዦቹ ምግብ ሳይበሉ ብዙ ቀን ቈይተው ነበር፤ በዚያን ጊዜ ጳውሎስ በተጓዦቹ መካከል ቆሞ እንዲህ አለ፤ “እናንተ ሰዎች፣ ይህ አደጋና ጉዳት እንዳይደርስባችሁ፣ ከቀርጤስ አትነሡ ብዬ የነገርኋችሁን መስማት ነበረባችሁ፤ BSB BSB: After the men had gone a long time without food, Paul stood up among them and said, “Men, you should have followed my advice not to sail from Crete. Then you would have averted this disaster and loss.
22 ULB አሁንም መርከቡ ብቻ ይጎዳል እንጂ ከመካከላችሁ የሚሞት አይኖርምና አይዞአችሁ ብዬ እመክራችኋለሁ። BSB BSB: But now I urge you to keep up your courage, because you will not experience any loss of life, but only of the ship.
23 ULB ምክንያቱም ባለፈው ሌሊት የእርሱ የሆንሁትና ደግሞም የማመልከው የእግዚአብሔር መልአክ በአጠገቤ ቆሞ እንዲህ ብሏል፤ BSB BSB: For just last night an angel of the God to whom I belong and whom I serve stood beside me
24 ULB “ጳውሎስ ሆይ፣ አትፍራ። በቄሣር ፊት ልትቆም ይገባሃል፤ ተመልከት፤ እግዚአብሔር በቸርነቱ ዐብረውህ የሚጓዙትን ሁሉ ሰጥቶሃል። BSB BSB: and said, ‘Do not be afraid, Paul; you must stand before Caesar. And look, God has granted you the lives of all who sail with you.’
25 ULB ስለዚህ እናንተ ሰዎች፣ አይዞአችሁ፤ ልክ እንደ ተናገረኝ እንደሚሆን እግዚአብሔርን አምነዋለሁ። BSB BSB: So take courage, men, for I believe God that it will happen just as He told me.
26 ULB ነገር ግን ወደ አንዲት ደሴት ደርሰን ልናርፍ ይገባል።” BSB BSB: However, we must run aground on some island.”
27 ULB በዐሥራ አራተኛውም ሌሊት፣ በአድርያቲክ ባሕር ወዲያና ወዲህ እየተንገላታን እያለን፣ እኩለ ሌሊት ገደማ፣ መርከበኞቹ ወደ መሬት የቀረቡ መሰላቸው። BSB BSB: On the fourteenth night we were still being driven across the Adriatic Sea. About midnight the sailors sensed they were approaching land.
28 ULB የባሕር ጥልቀት መለኪያ ገመድ ጣሉና ጥልቀቱን አርባ ሜትር ሆኖ አገኙት፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ መለኪያውን ሲጥሉም ሠላሳ ሜትር ሆኖ አገኙት። BSB BSB: They took soundings and found that the water was twenty fathoms deep. Going a little farther, they took another set of soundings that read fifteen fathoms.
29 ULB ከዐለቶቹ ጋር እንጋጫለን ብለውም ፈሩ፤ ስለዚህ ከኋላ አራት መልሕቆችን አውርደው ቶሎ እንዲነጋ ጸለዩ። BSB BSB: Fearing that we would run aground on the rocks, they dropped four anchors from the stern and prayed for daybreak.
30 ULB መርከበኞቹ መርከቡን ትተው ለመሄድ መንገድ ይፈልጉና ሕይወት አድን ጀልባውን ወደ ባሕሩ ውስጥ ያወርዱ ነበር፤ መልሕቆቹንም ከቀስቱ የሚወረውሩ መሰሉ። BSB BSB: Meanwhile, the sailors attempted to escape from the ship. Pretending to lower anchors from the bow, they let the lifeboat down into the sea.
31 ULB ጳውሎስ ግን መቶ አለቃውንና ወታደሮቹን፣ “እነዚህ ሰዎች በመርከቡ ካልቆዩ በቀር፣ እናንተ መዳን አትችሉም” አላቸው። BSB BSB: But Paul said to the centurion and the soldiers, “Unless these men remain with the ship, you cannot be saved.”
32 ULB ከዚያም ወታደሮቹ የጀልባውን ገመዶች ቈረጡት፤ እንዲንሳፈፍም አደረጉት። BSB BSB: So the soldiers cut the ropes to the lifeboat and set it adrift.
33 ULB ቀኑ ሊነጋ ሲልም፣ ምግብ እንዲበሉ ጳውሎስ ሁሉንም መከራቸው። እንዲህም አላቸው፤ “ምንም ሳትበሉ ከቈያችሁ ይህ ዐሥራ አራተኛ ቀናችሁ ነው። BSB BSB: Right up to daybreak, Paul kept urging them all to eat: “Today is your fourteenth day in constant suspense, without taking any food.
34 ULB ስለዚህ በሕይወት እንድትኖሩ፣ ጥቂት ምግብ እንድትበሉ እለምናችኋለሁ፤ ከራሳችሁ ላይ አንዲቱም ጠጕር አትጠፋም።” BSB BSB: So for your own preservation, I urge you to eat something, because not a single hair of your head will be lost.”
35 ULB ይህን ተናግሮ፣ እንጀራ አነሣና በሁሉም ፊት እግዚአብሔርን አመሰገነ። ከዚያም እንጀራውን ቈርሶ መብላት ጀመረ። BSB BSB: After he had said this, Paul took bread and gave thanks to God in front of them all. Then he broke it and began to eat.
36 ULB በዚያን ጊዜ ሁሉም ተጽናንተው ምግብ በሉ። BSB BSB: They were all encouraged and took some food themselves.
37 ULB በመርከቡ ውስጥ 276 ሰዎች ነበርን። BSB BSB: In all, there were 276 of us on board.
38 ULB በልተው በጠገቡ ጊዜም፣ ስንዴውን ወደ ባሕሩ በመጣል የመርከቡን ጭነት አቃለሉ። BSB BSB: After the men had eaten their fill, they lightened the ship by throwing the grain into the sea.
39 ULB በነጋታውም፣ የነበሩበትን ምድር አላወቁትም፤ ነገር ግን በዳርቻ ያለውን የባሕር ሰርጥ አዩ፤ መርከቡን ወደ ሰርጡ መግፋት ይችሉ እንደሆነም ተነጋገሩ። BSB BSB: When daylight came, they did not recognize the land, but they sighted a bay with a sandy beach, where they decided to run the ship aground if they could.
40 ULB ስለዚህ መልሕቆቹን ቈርጠው ባሕሩ ላይ ተዉአቸው። በዚሁ ጊዜም የመቅዘፊያዎቹን ገመዶች ፈትተው ሸራውን ወደ ነፋሱ ከፍ አደረጉና ወደ ባሕሩ ዳርቻ ለመውጣት ሄዱ። BSB BSB: Cutting away the anchors, they left them in the sea as they loosened the ropes that held the rudders. Then they hoisted the foresail to the wind and made for the beach.
41 ULB ነገር ግን ሁለት ማዕበሎች ወደ ተገናኙበት ስፍራ መጡ፤ መርከቡም ወደ መሬት ገባ፤ የመርከቡ ቅስትም በዚያ ተተከለና የማይነቃነቅ ሆነ፤ የኋላ ክፍሉ ግን ከማዕበሉ ነውጥ የተነሣ ይሰባበር ጀመር። BSB BSB: But the ship struck a sandbar and ran aground. The bow stuck fast and would not move, and the stern was being broken up by the pounding of the waves.
42 ULB የወታደሮቹ ዕቅድ ከመካከላቸው ማንም ዋኝቶ እንዳያመልጥ እስረኞቹን ለመግደል ነበር። BSB BSB: The soldiers planned to kill the prisoners so none of them could swim to freedom.
43 ULB የመቶ አለቃው ግን ጳውሎስን ለማዳን ፈለገ፤ ስለዚህ ዕቅዳቸውን አልተቀበለም፤ መዋኘት የሚችሉትም በመጀመሪያ ከመርከቡ ላይ እየዘለሉ ወደ የብስ እንዲወጡ አዘዘ። BSB BSB: But the centurion, wanting to spare Paul’s life, thwarted their plan. He commanded those who could swim to jump overboard first and get to land.
44 ULB ከዚያም የቀሩት ሰዎች በሳንቃዎችና ከመርከቡ በተገኙ ስብርባሪዎች ላይ ሆነው ተከትለው እንዲወጡ አደረገ። በዚህ ዐይነት ሁላችንም በደኅና ወደ የብስ ወጣን። BSB BSB: The rest were to follow on planks and various parts of the ship. In this way everyone was brought safely to land.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.