1 ULB ወደ መሬት በደኅና በደረስን ጊዜም፣ ደሴቲቱ ማልታ የምትባል መሆንዋን ዐወቅን። BSB BSB: Once we were safely ashore, we learned that the island was called Malta.
2 ULB የዚያች ደሴት ሰዎችም የተለመደውን ደግነት እንኳ አላሳዩንም፤ ሆኖም፣ በማያቋርጠው ዝናብና ብርድ ምክንያት እሳት አንድደው ሁላችንንም ተቀበሉን። BSB BSB: The islanders showed us extraordinary kindness. They kindled a fire and welcomed all of us because it was raining and cold.
3 ULB ነገር ግን ጳውሎስ ጭራሮ ሰብስቦ እሳቱ ላይ በጨመረው ጊዜ፣ ከሙቀቱ የተነሣ አንድ እፉኝት ወጣና በእጁ ላይ ተጣበቀ። BSB BSB: Paul gathered a bundle of sticks, and as he laid them on the fire, a viper, driven out by the heat, fastened itself to his hand.
4 ULB የደሴቲቱ ሰዎችም እፉኝቱ ከእጁ ላይ ተንጠልጥሎ ባዩ ጊዜ፣ እርስ በርሳቸው፣ “ይህ ሰው በእርግጥ ከባሕር ያመለጠ ነፍሰ ገዳይ ስለ ሆነ፣ ፍትሕ በሕይወት እንዲኖር አልፈቀደለትም” ተባባሉ። BSB BSB: When the islanders saw the creature hanging from his hand, they said to one another, “Surely this man is a murderer. Although he was saved from the sea, Justice has not allowed him to live.”
5 ULB ጳውሎስ ግን እፉኝቱን በእሳቱ ላይ አራገፈው፤ አልተጐዳምም። BSB BSB: But Paul shook the creature off into the fire and suffered no ill effects.
6 ULB ሰዎቹም ሰውነቱ በትኵሳት ያብጣል ወይም በድንገት ይሞታል ብለው ይጠባበቁ ነበር። ነገር ግን ረዘም ላለ ጊዜ ተጠባብቀውት ምንም እንዳልደረሰበት ካዩ በኋላ፣ ዐሳባቸውን ለውጠው አምላክ ነው አሉ። BSB BSB: The islanders were expecting him to swell up or suddenly drop dead. But after waiting a long time and seeing nothing unusual happen to him, they changed their minds and said he was a god.
7 ULB በአቅራቢያው ባለ አንድ ስፍራም ፑብልዮስ የተባለ የደሴቲቱ ገዢ መሬት ነበር፤ እርሱም ተቀብሎን ሦስት ቀን በደግነት አስተናገደን። BSB BSB: Nearby stood an estate belonging to Publius, the chief official of the island. He welcomed us and entertained us hospitably for three days.
8 ULB የፑብልዮስ አባት ትኵሳትና ተቅማጥ ይዞት ታሞ ነበር። ጳውሎስ ወደ እርሱ ሄዶ ጸለየ፤ እጆቹን ጫነበት፤ ፈወሰውም። BSB BSB: The father of Publius was sick in bed, suffering from fever and dysentery. Paul went in to see him, and after praying and placing his hands on him, he healed the man.
9 ULB ይህ ከሆነ በኋላ፣ በደሴቲቱ የሚኖሩ ታመው የነበሩ ሌሎች ደግሞ መጡና ተፈወሱ። BSB BSB: After this had happened, the rest of the sick on the island came and were cured as well.
10 ULB ሰዎቹም እጅግ አከበሩን። ለመሄድ በምንዘጋጅበት ጊዜም፣ የሚያስፈልገንን ሰጡን። BSB BSB: The islanders honored us in many ways and supplied our needs when we were ready to sail.
11 ULB ከሦስት ወር በኋላ፣ አፍንጫው ላይ የመንታ ወንድማማች ዓርማ በነበረበት፣ ክረምቱን በደሴቲቱ ባሳለፈ የእስክንድርያ መርከብ ላይ ተሳፍረን ጕዞ ጀመርን። BSB BSB: After three months we set sail in an Alexandrian ship that had wintered in the island. It had the Twin Brothers as a figurehead.
12 ULB ወደ ሲራኩስ ከተማ ከደረስን በኋላም፣ እዚያ ሦስት ቀን ቈየን። BSB BSB: Putting in at Syracuse, we stayed there three days.
13 ULB ከዚያም ተጕዘን ወደ ሬጊዩም ከተማ ደረስን። ከአንድ ቀን በኋላ የደቡብ ነፋስ ተነሣ፤ በሁለት ቀንም ወደ ፑቲዮሉስ ከተማ መጣን። BSB BSB: From there we weighed anchor and came to Rhegium. After one day, a south wind came up, and on the second day we arrived at Puteoli.
14 ULB እዚያም አንዳንድ ወንድሞችን አገኘንና ከእነርሱ ጋር ሰባት ቀን እንድንቈይ ተጋበዝን። በዚህ ዐይነት ወደ ሮም መጣን። BSB BSB: There we found some brothers who invited us to spend the week with them. And so we came to Rome.
15 ULB ከዚያም ወንድሞች ስለ እኛ ከሰሙ በኋላ፣ ሊቀበሉን አፍዩስ ገበያና ሦስቱ ማደሪያዎች ድረስ መጡ። ጳውሎስ ወንድሞችን ባየ ጊዜ፣ እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ተጽናናም። BSB BSB: The brothers there had heard about us and traveled as far as the Forum of Appius and the Three Taverns to meet us. When Paul saw them, he was encouraged and gave thanks to God.
17 ULB ቀን በኋላ፣ ጳውሎስ በአይሁድ መካከል መሪዎች የነበሩትን ሰዎች አንድ ላይ ጠራ። በተሰበሰቡ ጊዜም፣ እንዲህ አላቸው፤ “ወንድሞች ሆይ፣ በሕዝቡ ወይም በአባቶች ሥርዓት ላይ የፈጸምሁት ስሕተት ባይኖርም እንኳ፣ ከኢየሩሳሌም በእስረኝነት ለሮማውያን እጅ ተላልፌ ተሰጠሁ። BSB BSB: After three days, he called together the leaders of the Jews. When they had gathered, he said to them, “Brothers, although I have done nothing against our people or the customs of our fathers, I was taken prisoner in Jerusalem and handed over to the Romans.
18 ULB እነርሱ ከመረመሩኝ በኋላ ለሞት የሚያበቃኝ ምክንያት ስላልነበረብኝ፣ በነጻ ሊለቁኝ ፈልገው ነበር። BSB BSB: They examined me and wanted to release me, because there was no basis for a death sentence against me.
19 ULB ነገር ግን አይሁድ የሮማውያንን ፍላጎት ተቃውመው በተናገሩ ጊዜ፣ በሕዝቤ ላይ የማቀርበው ክስ ባይኖረኝም እንኳ፣ ወደ ቄሣር ይግባኝ ለማለት ተገደድሁ። BSB BSB: But when the Jews objected, I was compelled to appeal to Caesar, even though I have no charge to bring against my nation.
20 ULB በዚህ ምክንያት፣ ላያችሁና ላነጋግራችሁ ልመና አቅርቤአለሁ፤ ምክንያቱም እኔ በዚህ ሰንሰለት የታሰርሁት ለእስራኤል ስለ ተሰጠው እምነት ነው።” BSB BSB: So for this reason I have called to see you and speak with you. It is because of the hope of Israel that I am bound with this chain.”
21 ULB ከዚያም እነርሱ እንዲህ አሉት፤ “ከይሁዳ ስለ አንተ ደብዳቤ አልደረሰንም፤ ከወንድሞች መካከልም ስለ አንተ ያወራ ወይም ክፉ የተናገረ የለም። BSB BSB: The leaders replied, “We have not received any letters about you from Judea, nor have any of the brothers from there reported or even mentioned anything bad about you.
22 ULB ነገር ግን በሁሉም ስፍራ ተቃውሞ እየተወራበት መሆኑን እኛ ስለምናውቅ፣ ስለዚህ የሃይማኖት ወገን ምን እንደምታስብ ከአንተ መስማት እንፈልጋለን።” BSB BSB: But we consider your views worth hearing, because we know that people everywhere are speaking against this sect.”
23 ULB ለጳውሎስ ቀን በቀጠሩለት ጊዜም፣ ብዙ ሰዎች ወደ መኖሪያ ቤቱ መጡ። እርሱም ጉዳዩን ገለጠላቸው፤ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትም መሰከረላቸው። ከጠዋት እስከ ማታም ከሙሴ ሕግና ከነቢያት እየጠቀሰ፣ ስለ ኢየሱስ ሊያሳምናቸው ጥረት አደረገ። BSB BSB: So they set a day to meet with Paul, and many people came to the place he was staying. He expounded to them from morning to evening, testifying about the kingdom of God and persuading them about Jesus from the Law of Moses and the Prophets.
24 ULB አንዳንዶች የተናገረውን ቃል ሲያምኑ፣ ሌሎች ግን አላመኑም። BSB BSB: Some of them were convinced by what he said, but others refused to believe.
25 ULB እርስ በርሳቸው ሳይስማሙ ሲቀሩ፣ ጳውሎስ ይህን አንድ ቃል ከተናገረ በኋላ ሄዱ፤ “መንፈስ ቅዱስ በነቢዩ ኢሳይያስ አማካይነት ለአባቶቻችሁ በትክክል ተናገረ። BSB BSB: They disagreed among themselves and began to leave after Paul had made this final statement: “The Holy Spirit was right when He spoke to your fathers through Isaiah the prophet:
26 ULB እንዲህም አለ፤ ‘ወደዚህ ሕዝብ ሂድና እንደዚህ በላቸው፤ ‘መስማትስ ትሰማላችሁ፤ ነገር ግን አታስተውሉም፤ ማየትስ ታያላችሁ፤ ነገር ግን ልብ አታደርጉም። BSB BSB: ‘Go to this people and say, “You will be ever hearing but never understanding; you will be ever seeing but never perceiving.”
27 ULB በዐይናቸው እንዳያዩ፣ በጆሮአቸው እንዳይሰሙ፣ በልባቸው እንዳያስተውሉ፣ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፣ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአል፤ ዐይናቸውም ተጨፍኖአል።’ BSB BSB: For this people’s heart has grown callous; they hardly hear with their ears, and they have closed their eyes. Otherwise they might see with their eyes, hear with their ears, understand with their hearts, and turn, and I would heal them.’
28 ULB ስለዚህ፣ ይህ የእግዚአብሔር ድነት ወደ አሕዛብ እንደ ተላከ፣ እነርሱም እንደሚቀበሉት ዕወቁ። BSB BSB: Be advised, therefore, that God’s salvation has been sent to the Gentiles, and they will listen!”
31 ULB የእግዚአብሔርን መንግሥት ይሰብክ፣ ያስተምርም ነበር። ይህንም ሲያደርግ ማንም አልከለከለውም። BSB BSB: Boldly and freely he proclaimed the kingdom of God and taught about the Lord Jesus Christ.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.