1 ULB የእግዚአብሔርን ወንጌል በሐዋርያነት እንዲያገለግል ተለይቶ ከተጠራው ከኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ከጳውሎስ። BSB BSB: Paul, a servant of Christ Jesus, called to be an apostle, and set apart for the gospel of God—
2 ULB ወንጌሉም በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በነቢያቱ አስቀድሞ ተስፋ የሰጠው ነው። BSB BSB: the gospel He promised beforehand through His prophets in the Holy Scriptures,
4 ULB እርሱም በቅድስና መንፈስ ኃይል ከሙታን በመነሳት የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ የተነገረለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር። BSB BSB: and who through the Spirit of holiness was declared with power to be the Son of God by His resurrection from the dead: Jesus Christ our Lord.
5 ULB በስሙ ምክንያት ከእምነት የሚገኝ መታዘዝ በሕዝቦች ሁሉ መካከል እንዲሆን በእርሱ በኩል ጸጋንና ሐዋርያነትን ተቀበልን። BSB BSB: Through Him and on behalf of His name, we received grace and apostleship to call all those among the Gentiles to the obedience that comes from faith.
6 ULB እናንተም በእነዚህ ሕዝቦች መካከል የኢየሱስ ክርስቶስ ለመሆን ተጠራችሁ። BSB BSB: And you also are among those who are called to belong to Jesus Christ.
7 ULB ይህ መልዕክት የተጻፈው በእግዚአብሔር ለተወደዳችሁና ቅዱስ ሕዝብ ለመሆን ለተጠራችሁ በሮም ላላችሁት ሁሉ ነው። ከእግዚአብሔር ከአባታችንና ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። BSB BSB: To all in Rome who are loved by God and called to be saints: Grace and peace to you from God our Father and the Lord Jesus Christ.
8 ULB ስለ እምነታችሁ በመላው ዓለም በመነገሩ ምክንያት አስቀድሜ ስለሁላችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል አምላኬን አመሰግናለሁ። BSB BSB: First, I thank my God through Jesus Christ for all of you, because your faith is being proclaimed all over the world.
9 ULB ባለማቋረጥ እንደማስባችሁ የልጁን ወንጌል በመንፈሴ የማገለግለው እግዚአብሔር ምስክሬ ነው። BSB BSB: God, whom I serve with my spirit in preaching the gospel of His Son, is my witness how constantly I remember you
10 ULB አሁን በተቻለኝ መጠን በእግዚአብሔር ፈቃድ ተሳክቶልኝ ወደ እናንተ እንድመጣ ሁልጊዜ በጸሎቴ እለምናለሁ። BSB BSB: in my prayers at all times, asking that now at last by God’s will I may succeed in coming to you.
11 ULB የሚያበረታችሁን ጥቂት መንፈሳዊ ስጦታ እንዳካፍላችሁ ላያችሁ እናፍቃለሁ፥ BSB BSB: For I long to see you so that I may impart to you some spiritual gift to strengthen you,
12 ULB ይኸውም የእኔና የእናንተ በሆነ የእርስ በርሳችን እምነት አማካይነት እንድንበረታታ ስለምጓጓ ነው። BSB BSB: that is, that you and I may be mutually encouraged by each other’s faith.
13 ULB ወንድሞች ሆይ፥ ብዙ ጊዜ ወደ እናንተ ለመምጣት እንደ ሞከርኩኝና እስካሁን እንደተስተጓጎልኩኝ ሳታውቁ እንድትቀሩ አልፈልግም። ወደ እናንተ መምጣት የፈለግሁበት ምክንያት ከተቀሩት አሕዛብ እንዳገኘሁት ሁሉ ከእናንተ ደግሞ ጥቂት ፍሬ እንዳገኝ ነው። BSB BSB: I do not want you to be unaware, brothers, how often I planned to come to you (but have been prevented from visiting until now), in order that I might have a harvest among you, just as I have had among the other Gentiles.
14 ULB ለግሪኮችና ግሪኮች ላልሆኑት፥ ለጥበበኞችና ለማያስተውሉ ዕዳ አለብኝ። BSB BSB: I am obligated both to Greeks and non-Greeks, both to the wise and the foolish.
15 ULB ስለዚህ፥ በበኩሌ በሮም ለምትገኙት ለእናንተ ደግሞ ወንጌልን ለመስበክ ተዘጋጅቻለሁ። BSB BSB: That is why I am so eager to preach the gospel also to you who are in Rome.
17 ULB "ጻድቅ በእምነት ይኖራል" ተብሎ እንደተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ በወንጌል ከእምነት ወደ እምነት ተገልጧልና። BSB BSB: For the gospel reveals the righteousness of God that comes by faith from start to finish, just as it is written: “The righteous will live by faith.”
21 ULB ምክንያቱም ስለ እግዚአብሔር ቢያውቁም እንደ እግዚአብሔርነቱ ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት ነው። ይልቁንም በሀሳባቸው ሞኞች ሆኑ፥ የማያስተውለው ልባቸውም ጨለመ። BSB BSB: For although they knew God, they neither glorified Him as God nor gave thanks to Him, but they became futile in their thinking and darkened in their foolish hearts.
22 ULB ጥበበኞች ነን ቢሉም የማያስተውሉ ሆኑ። BSB BSB: Although they claimed to be wise, they became fools,
23 ULB የማይጠፋውን የእግዚአብሔር ክብር በሚጠፋ ሰው አምሳል፥በወፎች፥ አራት እግር ባላቸው አራዊትና በደረታቸው በሚሳቡ ፍጥረታት መልክ ለወጡ። BSB BSB: and exchanged the glory of the immortal God for images of mortal man and birds and animals and reptiles.
24 ULB ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሰውነታቸውን እንዲያዋርዱ እግዚአብሔር ለልባቸው የክፋት ምኞት ለእርኩሰት አሳልፎ ሰጣቸው። BSB BSB: Therefore God gave them over in the desires of their hearts to impurity for the dishonoring of their bodies with one another.
26 ULB ከዚህም የተነሳ እግዚአብሔር ለአስነዋሪ ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፥ ሴቶቻቸውም ለተፈጥሮአቸው የሚገባውን ተግባር ተገቢ ባልሆነው ለወጡ። BSB BSB: For this reason God gave them over to dishonorable passions. Even their women exchanged natural relations for unnatural ones.
27 ULB እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለተፈጥሮአቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወተ-ሥጋ ምኞት ተቃጠሉ። እነዚህ ወንዶች የማይገባውን ነገር ከወንድ ጋር በማድረጋቸው ስለ ነውራቸው ቅጣትን የተቀበሉ ናቸው። BSB BSB: Likewise, the men abandoned natural relations with women and burned with lust for one another. Men committed indecent acts with other men and received in themselves the due penalty for their error.
28 ULB እግዚአብሔርን ለማወቅ ስላልፈቀዱ እነዚያን ተገቢ ያልሆኑ ነገሮች እንዲያደርጉ ለማይረባ አዕምሮ አሳልፎ ሰጣቸው። BSB BSB: Furthermore, since they did not see fit to acknowledge God, He gave them up to a depraved mind, to do what ought not to be done.
29 ULB እነርሱ በአመጻ ሁሉ፥ በጨካኝነት፥ በክፉ ምኞትና በምቀኝነት፥ በቅናት፥ በነፍስ መግደል፥ በጸብ፥ በማታለልና በክፉ ሃሳብ የተሞሉ ናቸው። BSB BSB: They have become filled with every kind of wickedness, evil, greed, and depravity. They are full of envy, murder, strife, deceit, and malice. They are gossips,
30 ULB ሐሜተኞች፥ የሰው ስም አጥፊዎችና እግዚአብሔርን የሚጠሉ፥ ቁጡዎች፥ ዕብሪተኞችና ትዕቢተኞች ናቸው። ክፉ ነገሮችን የሚያመነጩና ለወላጆቻችው የማይታዘዙ፥ BSB BSB: slanderers, God-haters, insolent, arrogant, and boastful. They invent new forms of evil; they disobey their parents.
31 ULB ማስተዋል የሌላቸው፤ እምነት የማይጣልባቸው፥ ፍቅር የሌላቸውና የማይምሩ ናቸው። BSB BSB: They are senseless, faithless, heartless, merciless.
32 ULB እንደዚህ ያሉትን ነገሮች የሚያደርጉ ሞት እንደሚገባቸው የሚናገረውን የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ያውቃሉ፥እነርሱ ግን እነዚህኑ ነገሮች ራሳቸው የሚያደርጉ ብቻ ሳይሆኑ የሚያደርጉትን ሌሎችን የሚያበረታቱ ናቸው። BSB BSB: Although they know God’s righteous decree that those who do such things are worthy of death, they not only continue to do these things, but also approve of those who practice them.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.