1 ULB ከዚያም ሰውዬው ወደ መቅደሱም ቅዱስ ስፍራ አገባኝ፥ የግንቡንም አዕማድ ወርድ በዚህ ወገን ስድስት ክንድ በዚያም ወገን ስድስት ክንድ አድርጎ ለካ። BSB BSB: Then the man brought me into the outer sanctuary and measured the side pillars to be six cubits wide on each side.
2 ULB የመግቢያውም ወርድ አሥር ክንድ ነበረ፥ የመግቢያውም መቃኖች በዚህ ወገን አምስት ክንድ በዚያም ወገን አምስት ክንድ ነበሩ።ቀጥሎም ሰውዬው ቅዱስ ስፍራውን ርዝመቱ አርባ ክንድ ወርዱም ሀያ ክንድአድርጎ ለካ። BSB BSB: The width of the entrance was ten cubits, and the sides of the entrance were five cubits on each side. He also measured the length of the outer sanctuary to be forty cubits, and the width to be twenty cubits.
3 ULB ከዚያም ሰውዬው ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ገባ፥ የመግቢያውንም የግንብ አዕማድ ወርድ ሁለት ክንድ አድርጎ ለካ የመግቢያውም ወርድ ስድስት ክንድ ነበረ። የመግቢያውም ግንብ ወርድ በዚህ ወገን ሰባት ክንድ በዚያም ወገን ሰባት ክንድ ነበረ። BSB BSB: And he went into the inner sanctuary and measured the side pillars at the entrance to be two cubits wide. The entrance was six cubits wide, and the walls on each side were seven cubits wide.
4 ULB የክፍሉንም ርዝመት ወደ መቅደሱ ፊት ለፊት ሀያ ክንድ ወርዱንም ሀያ ክንድ አድርጎ ለካና፥ "ይህ ቅድስተ ቅዱሳን ነው" አለኝ። BSB BSB: Then he measured the room adjacent to the inner sanctuary to be twenty cubits long and twenty cubits wide. And he said to me, “This is the Most Holy Place.”
5 ULB የመቅደሱንም ግንብ ስድስት ክንድ አድርጎ። በመቅደሱም ዙሪያ ሁሉ ያሉትን የጓዳዎቹን ሁሉ ወርድ አራት ክንድ ነበረ። BSB BSB: Next he measured the wall of the temple to be six cubits thick, and the width of each side room around the temple was four cubits.
6 ULB ጓዳዎቹም አንዱ ከአንዱ በላይ በሦስት ደርብ ነበሩ፥ በእያንዳንዱም ደርብ ሠላሳ ጓዳዎች ነበሩ። በመቅደሱም ግንብ ዙሪያ ድጋፍ የሆኑ መደርደሪያዎች ነበሩ፥ ምክንያቱም በመቅደሱ ግንብ ውስጥ ድጋፎች አልነበሩም። BSB BSB: The side rooms were arranged one above another in three levels of thirty rooms each. There were ledges all around the wall of the temple to serve as supports for the side rooms, so that the supports would not be fastened into the wall of the temple itself.
7 ULB ላይኞቹ ጓዳዎች ከታችኞቹ ጓዳዎች ይበልጡ ነበር ከታችኛውም ደርብ ወደ መካከለኛው ከመካከለኛውም ደርብ ወደ ላይኛው የሚወጣበት ደረጃ ነበረ። BSB BSB: The side rooms surrounding the temple widened at each successive level, because the structure surrounding the temple ascended by stages corresponding to the narrowing of the temple wall as it rose upward. And so a stairway went up from the lowest story to the highest, through the middle one.
8 ULB በመቅደሱም ዙሪያ የጓዳዎቹም መሠረት የሆነ ከፍ ያለ ወለል እንዳለ አየሁ ቁመቱም ሙሉ ዘንግ የሚያህል ስድስት ክንድ ነበረ። BSB BSB: I saw that the temple had a raised base all around it, forming the foundation of the side rooms. It was the full length of a rod, six long cubits.
9 ULB የጓዳዎቹም የውጭው ግንብ ውፍረት አምስት ክንድ ነበረ። በመቅደሱም ጓዳዎች ውጭ የቀረ አንድ ባዶ ስፍራ ነበረ። BSB BSB: The outer wall of the side rooms was five cubits thick, and the open area between the side rooms of the temple
10 ULB በዚህም ባዶ ስፍራ በአንድ ወገን የካህናት በረንዳዎች ነበሩ፤ የባዶውም ስፍራ ወርድ በዙሪያ አምስት ክንድ ነበረ። ይህም ባዶ ሥፍራ በመቅደሱ ዙሪያ ወርዱ ሀያ ክንድ ነበረ። BSB BSB: and the outer chambers was twenty cubits wide all around the temple.
11 ULB በዚህም በባዶው ስፍራ አንዱ በሰሜን በኩል አንዱም በደቡብ በኩል የጓዳዎች መግቢያ ነበረ። የባዶውም ስፍራ ዙሪያ ወርድ አምስት ክንድ ነበረ። BSB BSB: The side rooms opened into this area, with one entrance on the north and another on the south. The open area was five cubits wide all around.
12 ULB በምዕራብም በኩል ባለው ግቢ አንጻር ያለው ህንጻ ስፋቱ ሰባ ክንድ ነበረ። በግቢውም ዙሪያ የነበረ ግንብ ውፍረቱ አምስት ክንድ ርዝመቱም ዘጠና ክንድ ነበረ። BSB BSB: Now the building that faced the temple courtyard on the west was seventy cubits wide, and the wall of the building was five cubits thick all around, with a length of ninety cubits.
13 ULB የመቅደሱንም ርዝመት መቶ ክንድ፥ የልዩውን ስፍራና ግቢውን ከግንቡ ጋር አንድ መቶ ክንድ አድርጎ ለካ። BSB BSB: Then he measured the temple to be a hundred cubits long, and the temple courtyard and the building with its walls were also a hundred cubits long.
14 ULB ደግሞም ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት የሚገኘው ግቢ የፊት ለፊት ወርዱ አንድ መቶ ክንድ ነበር። BSB BSB: The width of the temple courtyard on the east, including the front of the temple, was a hundred cubits.
15 ULB ቀጥሎም ሰውዬው ከቤተ መቅደሱ በስተዋላ ያለውን ህንጻ የምዕራብ ክፍል በዚህና በዚያ ከነበሩት ፎቆች ጋር እንዲሁም ቅዱስ ስፍራውና መድረኩን አንድ መቶ ክንድ አድርጎ ለካ። BSB BSB: Next he measured the length of the building facing the temple courtyard at the rear of the temple, including its galleries on each side; it was a hundred cubits. The outer sanctuary, the inner sanctuary, and the porticoes facing the court,
16 ULB ውስጠኛዎቹ ግድግዳዎች፥ ጠባቦቹን ጨምሮ መስኮቶቹ እንዲሁም በሶስት ደረጃዎች ያሉ ፎቆች በእንጨት ተለብጠው ነበር። BSB BSB: as well as the thresholds and the beveled windows and the galleries all around with their three levels opposite the threshold, were overlaid with wood on all sides. They were paneled from the ground to the windows, and the windows were covered.
17 ULB ከደጁም በላይ እስከ ውስጠኛው ክፍል ድረስ፥ በውጭም ግንቡ ሁሉ ውስጡም ውጭውም ተለብጦ ነበር። BSB BSB: In the space above the outside of the entrance to the inner sanctuary on all the walls, spaced evenly around the inner and outer sanctuary,
18 ULB በኪሩቤልና በዘንባባ ዛፎች ተውቦ ነበር የዘንባባውም ዛፍ ከኪሩብና ከኪሩብ መካከል ነበረ እያንዳንዱም ኪሩብ ሁለት ፊት ነበረው። BSB BSB: were alternating carved cherubim and palm trees. Each cherub had two faces:
19 ULB የሰው ፊት የሚመስለው በአንድ ወገን ወዳለው የዘንባባ ዛፍ ይመለከት ነበር፥ የአንበሳ ፊት የሚመስለው ደግሞ በሌላ ወገን ወዳለው የዘንባባ ዛፍ ይመለከት ነበር። ይህም በዙሪያ ያሉትን ቤቶች አስውቦ ነበር። BSB BSB: the face of a man was toward the palm tree on one side, and the face of a young lion was toward the palm tree on the other side. They were carved all the way around the temple.
20 ULB ከመሬት አንሥቶ እስከ ደጁ አናት ድረስ እና በመቅደሱ ላይ በኪሩቤልና በዘንባባ ዛፎች ተውበው ነበር። BSB BSB: Cherubim and palm trees were carved on the wall of the outer sanctuary from the floor to the space above the entrance.
21 ULB የመቅደሱ መቃኖችም አራት ማዕዘን ነበሩ፥ ሁሉም ለእርስ በእርስ ትይዩ ነበሩ። BSB BSB: The outer sanctuary had a rectangular doorframe, and the doorframe of the sanctuary was similar.
22 ULB ከቅዱሱ ሥፍራ ፊት ለፊት የሚገኘው ከእንጨት የተሰራው መስዋዕት ቁመቱ ሦስት ክንድ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ወርዱም ሁለት ክንድ ነበር። ማዕዘኖቹም እግሩም አገዳዎቹም ከእንጨት ተሠርተው ነበር። ሰውዬውም፥ "ይህች በእግዚአብሔር ፊት ያለችው ገበታ ናት" አለኝ። BSB BSB: There was an altar of wood three cubits high and two cubits square. Its corners, base, and sides were of wood. And the man told me, “This is the table that is before the LORD.”
23 ULB ለተቀደሰው ስፍራና ለቅድስተ ቅዱሳኑ ሁለት መዝጊያዎች ነበሩአቸው። BSB BSB: Both the outer sanctuary and the inner sanctuary had double doors,
24 ULB ለእያንዳንዱ መዝጊያም ሁለት ተዘዋዋሪ ሳንቃዎች ነበሩት ለአንዱ መዝጊያ ሁለት ለሌላውም መዝጊያ ሁለት ሳንቃዎች ነበሩት። BSB BSB: and each door had two swinging panels. There were two panels for one door and two for the other.
25 ULB ግንቦቹን እንዳስዋቡት ዓይነት በእነዚህ በቅዱስ ስፍራው መዝጊያዎች ላይ ኪሩቤልና የዘንባባ ዛፎች ተቀርጸው ነበር፣ በስተ ውጭም ባለው በደጀ ሰላሙ ፊት የእንጨት ጣራ ነበረ። BSB BSB: Cherubim and palm trees like those on the walls were carved on the doors of the outer sanctuary, and there was a wooden canopy outside, on the front of the portico.
26 ULB በደጀ ሰላሙም በሁለቱ ወገን በዚህና በዚያ ጠባብ መስኮቶችና የተቀረጹ የዘንባባ ዛፎች ነበሩበት። እነዚህም የመቅደሱም ጓዳዎች ነበሩ፥ እነርሱም ተንጠልጣይ ጣሪያዎችም ነበሯቸው። BSB BSB: There were beveled windows and palm trees on the sidewalls of the portico. The side rooms of the temple also had canopies.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.