1 ULB ርስትም አድርጋችሁ ምድሪቱን በዕጣ በምታካፍሉበት ጊዜ ለእግዚአብሔር መባ ታቀርባላችሁ። ይህም መባ የምድሪቱ የተቀደሰ ሥፍራ ሲሆን ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱም ሀያ ሺህ ክንድ ይሆናል በዳርቻው ሁሉ ዙሪያውን የተቀደሰ ይሆናል። BSB BSB: “When you divide the land by lot as an inheritance, you are to set aside a portion for the LORD, a holy portion of the land 25,000 cubits long and 20,000 cubits wide. This entire tract of land will be holy.
2 ULB ከእርሱም ርዝመቱ አምስት መቶ ወርዱም አምስት መቶ ክንድ አራት ማዕዘን የሆነ ቦታ ለመቅደሱ ይሆናል በዙሪያውም ባዶ ስፍራ የሚሆን አምሳ ክንድ ይሆናል። BSB BSB: Within this area there is to be a section for the sanctuary 500 cubits square, with 50 cubits around it for open land.
3 ULB ከዚያ ቦታ ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱም አሥር ሺህ ክንድ የሆነ ስፍራ ትለካለህ፤ እርሱም ቅዱስ ስፍራና ቅድስተ ቅዱሳን ይሆንልሀል። BSB BSB: From this holy portion, you are to measure off a length of 25,000 cubits and a width of 10,000 cubits, and in it will be the sanctuary, the Most Holy Place.
4 ULB ከምድሪቱም እግዚአብሔርን ለሚያገለግሉና ሊያገለግሉትም ወደ እግዚአብሔር ለሚቀርቡት ለካህናት የተለየ ክፍል ይሆናል። ለቤቶቻቸውም የሚሆን ስፍራ ለመቅደስም የሚሆን የተቀደሰ ስፍራ ይሆናል። BSB BSB: It will be a holy portion of the land to be used by the priests who minister in the sanctuary, who draw near to minister before the LORD. It will be a place for their houses, as well as a holy area for the sanctuary.
5 ULB ርዝመቱም ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም አሥር ሺህ የሆነ ስፍራ ለቤቱ አገልጋዮች ለሌዋውያን ይሆናል፥ ለሚቀመጡባቸውም ከተሞች ለራሳቸውም የርስት ይዞታ ይሆናል። BSB BSB: An adjacent area 25,000 cubits long and 10,000 cubits wide shall belong to the Levites who minister in the temple; it will be their possession for towns in which to live.
6 ULB ለከተማ የሚሆን ሥፍራም ከተቀደሰው የዕጣ ክፍል አጠገብ ወርዱ አምስት ሺህ ርዝመቱም ሀያ አምስት ሺህ የሆነውን ስፍራ ትለያላችሁ። ይህም ከተማ ለእስራኤል ቤት ሁሉ ይሆናል። BSB BSB: As the property of the city, you are to set aside an area 5,000 cubits wide and 25,000 cubits long, adjacent to the holy district. It will belong to the whole house of Israel.
7 ULB ለአለቃ ይዞታ የሆነው የዕጣ ክፍል በተቀደሰው መባና በከተማይቱ ይዞታ አጠገብ በዚህና በዚያ ይሆናል። በምዕራብና በምሥራቅ ይሆናል። ርዝመቱም እንደ አንድ ነገድ ዕጣ ክፍል ሆኖ ከምድሩ ከምዕራቡ ዳርቻ ጀምሮ እስከ ምሥራቁ ዳርቻ ድረስ ይሆናል። BSB BSB: Now the prince will have the area bordering each side of the area formed by the holy district and the property of the city, extending westward from the western side and eastward from the eastern side, running lengthwise from the western boundary to the eastern boundary and parallel to one of the tribal portions.
8 ULB ይህም ለእስራኤል አለቃ ይዞታ ይሆንለታል። አለቆቼም ለእስራኤል ቤት ምድሪቱን እንደ ነገዳቸው መጠን ይሰጡአቸዋል እንጂ ሕዝቤን ከእንግዲህ ወዲህ አያስጨንቋቸውም። BSB BSB: This land will be his possession in Israel. And My princes will no longer oppress My people, but will give the rest of the land to the house of Israel according to their tribes.
9 ULB ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል አለቆች ሆይ፥ ይብቃችሁ ግፍንና ብዝበዛን አስወግዱ፥ ፍርድንና ጽድቅንም አድርጉ! ሕዝቤን መቀማት አቁሙ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር! BSB BSB: For this is what the Lord GOD says: ‘Enough, O princes of Israel! Cease your violence and oppression, and do what is just and right. Stop dispossessing My people, declares the Lord GOD.’
10 ULB እውነተኛ ሚዛን እውነተኛም የኢፍ መስፈሪያ እውነተኛውም የባዶስ መስፈሪያ ይሁንላችሁ። BSB BSB: You must use honest scales, a just ephah, and a just bath.
11 ULB የኢፍና የባዶስ መስፈሪያ መጠናቸው እኩል ሆኖ የባዶስ መስፈሪያ የቆሮስ መስፈሪያ አንድ አሥረኛ ይሆናል፥ መስፈሪያው እንደ ቆሮስ መስፈሪያ ይሁን። BSB BSB: The ephah and the bath shall be the same quantity so that the bath will contain a tenth of a homer, and the ephah a tenth of a homer; the homer will be the standard measure for both.
12 ULB ሰቅሉም ሀያ አቦሊ ይሁን ሀያ ሰቅል፥ ሀያ አምስት ሰቅል፥ አሥራ አምስት ሰቅል፥ ምናን ይሁንላችሁ። BSB BSB: The shekel will consist of twenty gerahs. Twenty shekels plus twenty-five shekels plus fifteen shekels will equal one mina.
13 ULB የምታቀርቡት መባ ይህ ነው ከአንድ ቆሮስ መስፈሪያ ስንዴ የኢፍ መስፈሪያ አንድ ስድስተኛ፥ ከአንድም ቆሮስ መስፈሪያ ገብስ የኢፍ መስፈሪያ አንድ ስድስተኛ ትሰጣላችሁ። BSB BSB: This is the contribution you are to offer: a sixth of an ephah from each homer of wheat, and a sixth of an ephah from each homer of barley.
14 ULB የዘይቱም ደንብ፥ ከእያንዳንዱ የቆሮስ መስፈሪያ የባዶስን አንድ አሥረኛ ወይም ለእያንዳንዱ ቆሮስ ምክንያቱም አሥር የባዶስ መስፈሪያ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ነው። BSB BSB: The prescribed portion of oil, measured by the bath, is a tenth of a bath from each cor (a cor consists of ten baths or one homer, since ten baths are equivalent to a homer).
15 ULB ውኃም ካለበት ከእስራኤል አውራጃ ከመንጋው ከሁለቱ መቶ አንዱን የበግ ጠቦት ትሰጣላችሁ ይህ ያስተሰርይላችሁ ዘንድ ለእህል ቍርባንና ለሚቃጠል መሥዋዕት ለደኅንነትም መሥዋዕት ይሆናል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦ BSB BSB: And one sheep shall be given from each flock of two hundred from the well-watered pastures of Israel. These are for the grain offerings, burnt offerings, and peace offerings, to make atonement for the people, declares the Lord GOD.
16 ULB የአገሩም ሕዝብ ሁሉ ይህን መባ ለእስራኤል አለቃ ይሰጣሉ። BSB BSB: All the people of the land must participate in this contribution for the prince in Israel.
17 ULB በየበዓላቱም በየመባቻውም በየሰንበታቱም በእስራኤልም ቤት ዓመት በዓል ሁሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን የመጠጡንም ቍርባን በየመደቡ ማዘጋጀት የአለቃው ይሆናል። እርሱ የእስራኤል ቤት ወክሎ የኃጢአቱን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቀርባል። BSB BSB: And it shall be the prince’s part to provide the burnt offerings, grain offerings, and drink offerings for the feasts, New Moons, and Sabbaths—for all the appointed feasts of the house of Israel. He will provide the sin offerings, grain offerings, burnt offerings, and peace offerings to make atonement for the house of Israel.
18 ULB ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመጀመሪያው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ነውር የሌለበትን ወይፈን ውሰድ ስለ መቅደሱም የኃጢአት መስዋዕት ታቀርባላችሁ። BSB BSB: This is what the Lord GOD says: ‘On the first day of the first month you are to take a young bull without blemish and purify the sanctuary.
19 ULB ካህኑም ከኃጢአቱ መሥዋዕት ደም ወስዶ በመቅደሱ መቃኖችና በመሠዊያው እርከን በአራቱ ማዕዘን በውስጠኛውም አደባባይ በበሩ መቃኖች ላይ ይርጨው. BSB BSB: And the priest is to take some of the blood from the sin offering and put it on the doorposts of the temple, on the four corners of the ledge of the altar, and on the gateposts of the inner court.
20 ULB ይህንንም ከወሩ በሰባተኛው ቀን ስለ ሳተውና ስላላወቀው ታደርጋለህ። በዚህ መንገድ ለቤተ መቅድሱ ታስተስርያላችሁ። BSB BSB: You must do the same thing on the seventh day of the month for anyone who strays unintentionally or in ignorance. In this way you will make atonement for the temple.
21 ULB በመጀመሪያ ወር ከወሩም በአሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካን በዓል ታደርጋላችሁ። የሰባት ቀንም በዓል ይሆናል። የቂጣ እንጀራም ትበላላችሁ። BSB BSB: On the fourteenth day of the first month you are to observe the Passover, a feast of seven days, during which unleavened bread shall be eaten.
22 ULB በዚያም ቀን አለቃው ለራሱና ለአገሩ ሕዝብ ሁሉ የኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን ያቀርባል። BSB BSB: On that day the prince shall provide a bull as a sin offering for himself and for all the people of the land.
23 ULB በበዓሉም በሰባቱ ቀኖች የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቅርብ፡ ሰባቱንም ቀኖች በየዕለቱ ነውር የሌለባቸውን ሰባት ወይፈንና ሰባት አውራ በጎች ያቅርብ ለኃጢአትም መሥዋዕት በየዕለቱ አንድ አውራ ፍየል ያቅርብ። BSB BSB: Each day during the seven days of the feast, he shall provide seven bulls and seven rams without blemish as a burnt offering to the LORD, along with a male goat for a sin offering.
24 ULB ለአንድም ወይፈን አንድ የኢፍ መስፈሪያ ለአንድም አውራ በግ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ለአንድም የኢፍ መስፈሪያ አንድ የኢን መስፈሪያ ዘይት ለእህል ቍርባን ያቅርብ። BSB BSB: He shall also provide as a grain offering an ephah for each bull and an ephah for each ram, along with a hin of olive oil for each ephah of grain.
25 ULB አለቃው በሰባተኛውም ወር ከወሩም በአሥራ አምስተኛው ቀን በበዓሉ ሰባት ቀኖች፥ የኃጢአቱን መሥዋዕት የሚቃጠለውንም መሥዋዕት የእህሉንም ቍርባን ከዘይቱ ጋር እንዲሁ ያቅርብ። BSB BSB: During the seven days of the feast that begins on the fifteenth day of the seventh month, he is to make the same provision for sin offerings, burnt offerings, grain offerings, and oil.’
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.