1 ULB ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውስጠኛው አደባባይ ወደ ምሥራቅ የሚመለከተው በር ሥራ በሚሠራበት በስድስቱ ቀን ተዘግቶ ይቈይ ነገር ግን በሰንበት ቀንና በመባቻ ቀን ይከፈት። BSB BSB: “This is what the Lord GOD says: ‘The gate of the inner court that faces east must be kept shut during the six days of work, but on the Sabbath day and on the day of the New Moon it shall be opened.
2 ULB አለቃውም በስተ ውጭ ባለው በር በደጀ ሰላሙ መንገድ ገብቶ ካህናቱም የእርሱን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት እስኪያቀርርቡ ድረስ በበሩ መቃን አጠገብ ይቁም። ከዚያም በበሩ መድረክ ላይ ሰግዶ ይውጣ፥ በሩ ግን እስከ ማታ ድረስ አይዘጋ። BSB BSB: The prince is to enter from the outside through the portico of the gateway and stand by the gatepost, while the priests sacrifice his burnt offerings and peace offerings. He is to bow in worship at the threshold of the gate and then depart, but the gate must not be shut until evening.
3 ULB የአገሩም ሕዝብ በዚያ በር መግቢያ በእግዚአብሔር ፊት በሰንበታትና በመባቻ ይስገዱ። BSB BSB: On the Sabbaths and New Moons the people of the land are also to bow in worship before the LORD at the entrance to that gateway.
4 ULB አለቃውም በሰንበት ቀን ለእግዚአብሔር የሚያቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለባቸው ስድስት የበግ ጠቦቶች ነውርም የሌለበት አንድ አውራ በግ ይሁን BSB BSB: The burnt offering that the prince presents to the LORD on the Sabbath day shall be six unblemished male lambs and an unblemished ram.
5 ULB የእህሉም ቍርባን ለአውራ በጉ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ይሁን፥ ለጠቦቶቹም የእህል ቍርባን የሚቻለውን ያህል ይሁን፥ ለአንዱም የኢፍ መስፈሪያ አንድ የኢን መስፈሪያ ዘይት ያቅርብ። BSB BSB: The grain offering with the ram shall be one ephah, and the grain offering with the lambs shall be as much as he is able, along with a hin of oil per ephah.
6 ULB በመባቻም ቀን ከመንጋው መካከል ነውር የሌለበትን አንድ ወይፈን፥ ነውር የሌለባቸውንም ስድስት ጠቦቶችና አንድ አውራ በግ ያቅርብ BSB BSB: On the day of the New Moon he shall offer a young, unblemished bull, six lambs, and a ram without blemish.
7 ULB ለወይፈኑም አንድ የኢፍ መስፈሪያ ለአውራውም በግ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ለጠቦቶቹም እንደ ተቻለው ያህል፥ የእህል ቁርባን እንዲሁም ለአንዱም የኢፍ መስፈሪያ የእህል ቁርባን አንድ የኢን መስፈሪያ ዘይት ያቅርብ። BSB BSB: He is to provide a grain offering of an ephah with the bull, an ephah with the ram, and as much as he is able with the lambs, along with a hin of oil per ephah.
8 ULB አለቃውም በሚገባበት ጊዜ በበሩ ደጀ ሰላም መንገድ ይግባ በዚያውም ይውጣ። BSB BSB: When the prince enters, he shall go in through the portico of the gateway, and he shall go out the same way.
9 ULB የአገሩ ሕዝብ ግን በየክብረ በዓሉ ቀን ወደ እግዚአብሔር ፊት በመጡ ጊዜ በሰሜን በር በኩል ሊሰግድ የሚገባው በደቡብ በር በኩል ይውጣ፥ በደቡብም በር የሚገባው በሰሜን በር በኩል ይውጣ። በፊት ለፊት ይውጣ እንጂ በገባበቱ በር አይመለስ። BSB BSB: When the people of the land come before the LORD at the appointed feasts, whoever enters by the north gate to worship must go out by the south gate, and whoever enters by the south gate must go out by the north gate. No one is to return through the gate by which he entered, but each must go out by the opposite gate.
10 ULB በሚገቡበት ጊዜ አለቃው በመካከላቸው ይግባ በሚወጡበትም ጊዜ ይውጣ። BSB BSB: When the people enter, the prince shall go in with them, and when they leave, he shall leave.
11 ULB በበዓላትም የእህሉ ቍርባን ለወይፈኑ አንድ የኢፍ መስፈሪያ፥ ለአውራ በጉ አንድ የኢፍ መስፈሪያ፥ ለጠቦቶቹም እንደሚቻለው ያህል፥ ለኢፍ መስፈሪያም አንድ የኢን መስፈሪያ ዘይት ይሆናል። BSB BSB: At the festivals and appointed feasts, the grain offering shall be an ephah with a bull, an ephah with a ram, and as much as one is able to give with the lambs, along with a hin of oil per ephah.
12 ULB አለቃውም በፈቃዱ የሚያቀርበውን መሥዋዕት፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ ወይም በፈቃዱ ለእግዚአብሔር የሚያቀርበውን የደኅንነቱን መሥዋዕት፥ ባቀረበ ጊዜ፥ የምሥራቁን በር ይክፈት፥ በሰንበትም ቀን እንደሚያደርግ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቅርብ ከዚያም በኋላ ይውጣ፥ ከወጣም በኋላ በሩን ይዝጋ። BSB BSB: When the prince makes a freewill offering to the LORD, whether a burnt offering or a peace offering, the gate facing east must be opened for him. He is to offer his burnt offering or peace offering just as he does on the Sabbath day. Then he shall go out, and the gate must be closed after he goes out.
13 ULB በየዕለቱም ለሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለበትን የአንድ ዓመት በግ ጠቦት ለእግዚአብሔር ታቀርባላችሁ፤ ይህንንም በየማለዳው ታደርጋላችሁ። BSB BSB: And you shall provide an unblemished year-old lamb as a daily burnt offering to the LORD; you are to offer it every morning.
14 ULB ከእርሱም ጋር እንደ ቋሚ ሥርዓት የእህልን ቍርባን፥ በኢን መስፈሪያ ሢሶ ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ ስድስተኛ እጅ መልካም ዱቄትን፥ በየማለዳው ታቀርባላችሁ። BSB BSB: You are also to provide with it every morning a grain offering of a sixth of an ephah with a third of a hin of oil to moisten the fine flour—a grain offering to the LORD. This is a permanent statute.
15 ULB እንዲሁ ዘወትር ለሚቃጠለው መሥዋዕት ጠቦቱንና የእህሉን ቍርባን ዘይቱንም በየማለዳው ያቅርብ። BSB BSB: Thus they shall provide the lamb, the grain offering, and the oil every morning as a regular burnt offering.’
16 ULB ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አለቃው ከልጆቹ ለአንዱ ከርስቱ ስጦታ ቢሰጥ የልጁ ውርስ ይሆናል። የልጆቹ ንብረት ውርስ ይሆንላቸዋል። BSB BSB: This is what the Lord GOD says: ‘If the prince gives a gift to any of his sons as an inheritance, it will belong to his descendants. It will become their property by inheritance.
17 ULB ነገር ግን ከባሪያዎቹ ለአንዱ ከርስቱ ስጦታ ቢሰጥ እስከ ነጻነት ዓመት ድረሰ ለእርሱ ይሁን፥ ከዚያም በኋላ ለአለቃው ይመለስ። ርስቱ ግን ለልጆቹ ይሁን። BSB BSB: But if he gives a gift from his inheritance to one of his servants, it will belong to that servant until the year of freedom; then it will revert to the prince. His inheritance belongs only to his sons; it shall be theirs.
18 ULB አለቃውም ሕዝቡን ከይዞታቸው ያወጣቸው ዘንድ ከርስታቸው በግድ አይውሰድ ሕዝቤ ሁሉ ከይዞታቸው እንዳይነቀሉ ከገዛ ይዞታው ለልጆች ርስትን ይስጥ። BSB BSB: The prince must not take any of the inheritance of the people by evicting them from their property. He is to provide an inheritance for his sons from his own property, so that none of My people will be displaced from his property.’”
19 ULB ከዚያም ሰውዬው ወደ ሰሜን ወደሚመለከተው ለካህናት ወደሚሆን ወደ ተቀደሱ ክፍሎች እነሆም፥ በስትምዕራብ በኩል አንድ ስፍራ ነበረ። BSB BSB: Then the man brought me through the entrance at the side of the gate into the holy chambers facing north, which belonged to the priests, and he showed me a place there at the far western end
20 ULB እርሱም፥ "ካህናቱ ሕዝቡን ለመቀደስ ወደ ውጭው አደባባይ እንዳያወጡ የበደሉን መሥዋዕትና የኃጢአቱን መሥዋዕት የሚቀቅሉበት፥ የእህሉንም ቍርባን የሚጋግሩበት ስፍራ ይህ ነው አለኝ። BSB BSB: and said to me, “This is the place where the priests shall boil the guilt offering and the sin offering, and where they shall bake the grain offering, so that they do not bring them into the outer court and transmit holiness to the people.”
21 ULB በውጭው አደባባይ አወጣኝ በአደባባይም ወዳለው በአራቱ ማዕዘን በኩል አሳለፈኝ እነሆም፥ በእያንዳንዱ የአደባባዩ ማዕዘን ሌላ አደባባይ እንዳለ አየሁ። BSB BSB: Then he brought me into the outer court and led me around to its four corners, and I saw a separate court in each of its corners.
22 ULB በአደባባዩ በአራቱ ማዕዘን ርዝመቱ አርባ ክንድ ወርዱም ሠላሳ ክንድ የሆነ አደባባይ ነበረ። በማዕዘኑ ላሉ ለእነዚህ ለአራቱ ስፍራዎች አንድ ልኬቱ እኩል ነበረ። BSB BSB: In the four corners of the outer court there were enclosed courts, each forty cubits long and thirty cubits wide. Each of the four corner areas had the same dimensions.
23 ULB በአራቱም ዙሪያ ሁሉ ግንብ ነበረ፥ በግንቡም ሥር በዙሪያው የመቀቀያ ቦታ ነበረ። BSB BSB: Around the inside of each of the four courts was a row of masonry with ovens built at the base of the walls on all sides.
24 ULB ሰውዬውም፥ "እነዚህ የቤቱ አገልጋዮች የሕዝቡን መሥዋዕት የሚቀቅሉባቸው ስፍራዎች ናቸው አለኝ። BSB BSB: And he said to me, “These are the kitchens where those who minister at the temple will cook the sacrifices offered by the people.”
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.