1 ULB ያን የምለው ህጻን ሳለ ምንም እንኳ ሁሉም የእርሱ ቢሆንም ወራሹ ከባሪያ አይለይም። BSB BSB: What I am saying is that as long as the heir is a child, he is no different from a slave, although he is the owner of everything.
2 ULB ነገር ግን አባቱ የወሰነልት ቀን እስኪደርስለት ድረስ በተንከባካቢዎቹና በሞግዚቶቹ ስር ይቆያል። BSB BSB: He is subject to guardians and trustees until the date set by his father.
3 ULB እኛም ልጆች ሳለን በዚህ ዓለም ዋና ትምህርቶች እስራት ሥር ነበርን። BSB BSB: So also, when we were children, we were enslaved under the basic principles of the world.
5 ULB ነጻ እንዲያወጣና የልጅነትን መብት እንዲኖረን ከሴት የተወለደውንና በህግ ሥር የተወለደውን ልጁን ላከ። BSB BSB: to redeem those under the law, that we might receive our adoption as sons.
6 ULB ልጆች ስለሆናችሁ «አባ አባት» እያለ የሚጣራውን የልጁን መንፈስ ወደ ልባችን ላከ። BSB BSB: And because you are sons, God sent the Spirit of His Son into our hearts, crying out, “Abba, Father!”
7 ULB በዚህም ምክንያት ከእንግዲህ ልጆች እንጂ ባሮች አይደላችሁም፥ ልጆች ከሆናችሁ ደግሞ የእግዚአብሔር ወራሾች ናችሁ። BSB BSB: So you are no longer a slave, but a son; and since you are a son, you are also an heir through God.
8 ULB ነገር ግን እግዘአብሔርን በማታውቁበት በቀድሞው ዘመን በባህሪያቸው ፈጽሞ አማልክት ላልሆኑት ተገዝታችሁ ኖራችሁ። BSB BSB: Formerly, when you did not know God, you were slaves to those who by nature are not gods.
9 ULB አሁን ግን እግዚአብሔርን አውቃችኋል ይልቁኑም በእግዚአብሔር ታውቃችኋል፥ ታዲያ እንዴት ወደ ደካማና ዋጋ ወደሌለው የዚህ ዓለም ዋና ትምህርት ተመለሳችሁ።እንደገና ባሮች መሆን ትፈልጋላችሁ? BSB BSB: But now that you know God, or rather are known by God, how is it that you are turning back to those weak and worthless principles? Do you wish to be enslaved by them all over again?
10 ULB ልዩ ቀናትን፥አዳዲስ ጨረቃዎችን፥ ወራትና ዓመታትን ታመልካላችሁ። BSB BSB: You are observing special days and months and seasons and years!
11 ULB ስለ እናንተ የደከምኩት ድካም ከንቱ ሆኖብኝ እንዳይሆን ብዬ እፈራለሁ። BSB BSB: I fear for you, that my efforts for you may have been in vain.
12 ULB ወንድሞች ሆይ ልክ እኔ ለእናንተ እንደምሆነው እናንተም ለእኔ እንደዚያው እንድትሆኑ እለምናችኋለሁ። BSB BSB: I beg you, brothers, become like me, for I became like you. You have done me no wrong.
13 ULB ምንም ክፉ አላደርጋችሁብኝም ነገር ግን ወንጌልን በመጀመሪያ በሰብኩላችሁ ጊዜ የሥጋ ህመም አሞኝ እንደነበረ ታውቃላችሁ። BSB BSB: You know that it was because of an illness that I first preached the gospel to you.
14 ULB በሥጋዬ ላይ የነበረው ለእናንተ ከባድ ፈተና ቢሆንም አልተጸየፋችሁኝም አልጣላችሁኝምም፥ ይልቁኑ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ወይም ክርስቶስን በተቀበላችሁብት አቀባበል ተቀበላችሁኝ። BSB BSB: And although my illness was a trial to you, you did not despise or reject me. Instead, you welcomed me as if I were an angel of God, as if I were Christ Jesus Himself.
15 ULB አሁን ደስታችሁ በምንድነው? ዓይናችሁን እንኳ አውጥታችሁ ልትሰጡኝ ፈቃደኛ እንደነበራችሁ እኔ ራሴ ምስክር ነኝ። BSB BSB: What then has become of your blessing? For I can testify that, if it were possible, you would have torn out your eyes and given them to me.
16 ULB ታዲያ እውነትን ስለነገርኳችሁ የእናንተ ጠላት ሆንኩ ማለት ነው? BSB BSB: Have I now become your enemy by telling you the truth?
17 ULB አጥበቀው ይፈልጓችኋል ነገር ግን ለመልካም አይደለም። እነርሱን እንድትከተሉ ከእኔ ሊለዩዋችሁ ይፈልጋሉ። BSB BSB: Those people are zealous for you, but not in a good way. Instead, they want to isolate you from us, so that you may be zealous for them.
18 ULB እኔ ከእናንተ ጋር ስሆን ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜ ለመልካም ነገር መትጋት ተገቢ ነው። BSB BSB: Nevertheless, it is good to be zealous if it serves a noble purpose—at any time, and not only when I am with you.
19 ULB ጨቅላ ልጆቼ ሆይ ክርስቶስ በውስጣችሁ እስኪቀረጽ ድረስ ስለእናንተ ምጥ ይዞኛል! BSB BSB: My children, for whom I am again in the pains of childbirth until Christ is formed in you,
20 ULB የእናንተ ነገር ግራ ስለገባኝ በመካከላችሁ ተገኝቼ በቁጣ ልናገራችሁ እመኛለሁ። BSB BSB: how I wish I could be with you now and change my tone, because I am perplexed about you.
21 ULB እስኪ እናንተ በህግ ሥር ለመሆን የምትፈልጉ ንገሩኝ ህጉ ምን እንደሚል አልሰማችሁምን? BSB BSB: Tell me, you who want to be under the law, do you not understand what the law says?
22 ULB አብርሃም አንድ ባሪያ ከነበረች ሴት አንድ ደግሞ ነጻ ከነበረች ሴት የተወለዱ ሁለት ልጆች እንደነበሩት ተጽፏል። BSB BSB: For it is written that Abraham had two sons, one by the slave woman and the other by the free woman.
23 ULB ነገር ግን ከባሪያይቱ የተወለደው በሥጋ ብቻ የተወለደ ነው፥ ከነጻይቱ የተወለደው ግን በተስፋ የተወለደ ነው። BSB BSB: His son by the slave woman was born according to the flesh, but his son by the free woman was born through the promise.
24 ULB እነዚህ ነገሮች እንደ ምሳሌ ሊገለጹ ይችላሉ።እነኚህ ሴቶች እንደ ሁለቱ ቃል ኪዳኖች ናቸው፥ አንደኛዋ በሲና ተራራ የተሰጠውንና ባርነትን የወለደውን ታመለክታለች፥ እርሷም አጋር ናት። BSB BSB: These things serve as illustrations, for the women represent two covenants. One covenant is from Mount Sinai and bears children into slavery: This is Hagar.
25 ULB እንግዲህ አጋር በአረቢያ ምድር የሚገኘው የሲና ተራራ ስትሆን ከልጆቿ ጋር በባርነት የምትኖረውን የአሁኗን ኢየሩሳሌምን ትወክላለች። BSB BSB: Now Hagar stands for Mount Sinai in Arabia and corresponds to the present-day Jerusalem, because she is in slavery with her children.
26 ULB ነገር ግን እናታችን የሆነችው ላይኛይቱ ጽዮን ነጻ ነች። BSB BSB: But the Jerusalem above is free, and she is our mother.
27 ULB ምክንያቱም እንዲህ ተብሎ ተጽፏል «አንቺ ያልወለድሽና መካን የሆንሽ ሴት ሀሴት አድርጊ፥አንቺ መውለድን ያልተለማምድሽ ውጪና በደስታ ጩኺ፤ ባል ካላቱ ይልቅ የመካኗ ልጆች በዝተዋልና»። BSB BSB: For it is written: “Rejoice, O barren woman, who bears no children; break forth and cry aloud, you who have never travailed; because more are the children of the desolate woman than of her who has a husband.”
28 ULB እንግዲህ እናንተ ወንድሞቼ እንደ ይስሀቅ የተስፋ ልጆች ናችሁ። BSB BSB: Now you, brothers, like Isaac, are children of promise.
29 ULB ነገር ግን እንደ ሥጋ ፈቃድ የተወለደው እንደ መንፈስ ፈቃድ የተወለደውን እንዳሳደደው አሁንም እየሆነ ያለው እንደዚያው ነው። BSB BSB: At that time, however, the son born by the flesh persecuted the son born by the Spirit. It is the same now.
30 ULB መጽሀፍ ስለዚህ ነገር ምን ይላል«የባሪያይቱ ልጅ ከነጻይቱ ልጅ ጋር አይወርስምና ባሪያይቱንና ልጇን አስወጣ»። BSB BSB: But what does the Scripture say? “Expel the slave woman and her son, for the slave woman’s son will never share in the inheritance with the free woman’s son.”
31 ULB ስለዚህ ወንድሞች ሆይ እኛ የነጻይቱ እንጂ የባሪያይቱ ልጆች አይደለንም። BSB BSB: Therefore, brothers, we are not children of the slave woman, but of the free woman.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.