1 ULB የምድር በውስጣቸው ያሉትም ሕያዋን ፍጡራን አፈጣጠር በዚህ ሁኔታ ተከናወነ። BSB BSB: Thus the heavens and the earth were completed in all their vast array.
2 ULB እግዚአብሔር ይሠራ የነበረውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጽሞ በዚሁ ቀን ከሥራው ሁሉ አረፈ። BSB BSB: And by the seventh day God had finished the work He had been doing; so on that day He rested from all His work.
3 ULB እግዚአብሔር የመፍጠር ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ ያረፈው በዚህ ቀን ስለሆነ ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም። BSB BSB: Then God blessed the seventh day and sanctified it, because on that day He rested from all the work of creation that He had accomplished.
5 ULB እግዚአብሔር አምላክ በምድር ላይ ዝናብ እንዲዘንብ ስላደረገና ምድርንም የሚያለማ ሰው ባለመኖሩ በምድር ላይ ምንም ቡቃያ አልነበረም፣ በምድር ላይ የሚበቅል ተክልም ገና አልበቀለም። BSB BSB: Now no shrub of the field had yet appeared on the earth, nor had any plant of the field sprouted, for the LORD God had not yet sent rain upon the earth, and there was no man to cultivate the ground.
6 ULB ነገር ግን ውሃ ከመሬት እየመነጨ የምድርን ገጽ ያረሰርስ ነበር። BSB BSB: But springs welled up from the earth and watered the whole surface of the ground.
8 ULB እግዚአብሔር አምላክም በስተምሥራቅ በኩል በዔደን የአትክልት ስፍራ አዘጋጀ፣ የአበጀውንም ሰው በዚያ አኖረው። BSB BSB: And the LORD God planted a garden in Eden, in the east, where He placed the man He had formed.
9 ULB ከምድር ውስጥም እግዚአብሔር አምላክ ለዓይን የሚያስደስቱና ለምግብነት የሚጠቅሙ ልዩ ልዩ ዛፎች እንዲበቅሉ አደረገ። በአትክልት ስፍራው መካከልም የሕይወት ዛፍ ነበር፣ መልካሙንና ክፉውን የሚያሳውቀውም ዛፍ በዚያ ነበር። BSB BSB: Out of the ground the LORD God gave growth to every tree that is pleasing to the eye and good for food. And in the middle of the garden were the tree of life and the tree of the knowledge of good and evil.
10 ULB የአትክልት ስፍራውንም የሚያጠጣ ወንዝ ከኤደን ይፈስ ነበር። ወንዙም ከኤደን ከወጣ በኋላ አራት ወንዞች ሆኖ ይከፋፈል ነበር። BSB BSB: Now a river flowed out of Eden to water the garden, and from there it branched into four headwaters:
11 ULB የመጀመሪያው ፊሶን የተባለው ወንዝ ነበር፣ ይህም ወርቅ ይገኝበት የነበረውን መላውን የሐዊላ ምድር አቋርጦ የሚፈስው ወንዝ ነበር። BSB BSB: The name of the first river is the Pishon; it winds through the whole land of Havilah, where there is gold.
12 ULB የዚያ አገር ወርቅ የጠራ ወርቅ ነበር፤ በተጨማሪም በዚያ አገር ሽቶና የከበሩ ድንጋዮች ነበሩ። BSB BSB: And the gold of that land is pure, and bdellium and onyx are found there.
13 ULB የሁለተኛው ወንዝ ስም ግዮን ይባል ነበር፣ እርሱም መላውን የኢትዮጵያ ምድር አቋርጦ ይፈስ ነበር። BSB BSB: The name of the second river is the Gihon; it winds through the whole land of Cush.
14 ULB የሶስተኛው ወንዝ ስም ጤግሮስ ይባል ነበር፣ እርሱም በአሦር በስተምሥራቅ ይፈሳል። አራተኛው ወንዝ ኤፍራጥስ ነበር። BSB BSB: The name of the third river is the Tigris; it runs along the east side of Assyria. And the fourth river is the Euphrates.
15 ULB እግዚአብሔር አምላክም የኤደንን የአትክልት ስፍራ ያለማና ይንከባከብ ዘንድ ሰውን ወስዶ በዚያ አኖረው። BSB BSB: Then the LORD God took the man and placed him in the Garden of Eden to cultivate and keep it.
17 ULB ነገር ግን መልካሙንና ክፉውን ከሚያሳውቀው ዛፍ አትብላ፣ ምክንያቱም ከእርሱ በበላህ ቀን በእርግጥ ትሞታለህ።” BSB BSB: but you must not eat from the tree of the knowledge of good and evil; for in the day that you eat of it, you will surely die.”
20 ULB አዳም ለሁሉም ከብቶች፣ ለሁሉም የሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ሁሉ ስም አወጣላቸው። ነገር ግን ለአዳም ለራሱ የምትመች ረዳት አልተገኘለትም። BSB BSB: The man gave names to all the livestock, to the birds of the air, and to every beast of the field. But for Adam no suitable helper was found.
21 ULB እግዚአብሔር አምላክ በአዳም ላይ ከባድ እንቅልፍ እንዲወስደው አደረገ፣ ስለሆነም አዳም አንቀላፋ። እግዚአብሔር አምላክ አዳም አንቀላፍቶ ሳለ ከጎድን አጥንቶቹ አንዱን ወስዶ አጥንቱን የወሰደበትን ስፍራ በሥጋ ዘጋው። BSB BSB: So the LORD God caused the man to fall into a deep sleep, and while he slept, He took one of the man’s ribs and closed up the area with flesh.
22 ULB እግዚአብሔር አምላክ ከአዳም ከወሰደው የጎድን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት። ወደ አዳምም አመጣት። BSB BSB: And from the rib that the LORD God had taken from the man, He made a woman and brought her to him.
23 ULB አዳምም፦ “አሁን ይህቺ ከአጥንቴ የተገኘች አጥንት ከሥጋዬ የተገኘች ሥጋ ናት። ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል” አለ። BSB BSB: And the man said: “This is now bone of my bones and flesh of my flesh; she shall be called ‘woman,’ for out of man she was taken.”
25 ULB አዳምና ሚስቱ ሁለቱም ራቁታቸውን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ አይተፋፈሩም ነበር። BSB BSB: And the man and his wife were both naked, and they were not ashamed.