1 ULB የዕቆብ አባቱ በኖረበት በከነዓን ምድር ተቀመጠ። BSB BSB: Now Jacob lived in the land where his father had resided, the land of Canaan.
2 ULB የያዕቆብ ትውልድ ታሪክ ይህ ነው። ዮሴፍ የዐሥራ ሰባት ዓመት ወጣት በነበረ ጊዜ፣ ከአባቱ ሚስቶች ከባላቅና ከዘለፋ ከተወለዱት ወንድሞቹ ጋር የአባቱን በጎችና ፍየሎች ይጠብቅ ነበር። እርሱም ስለወንድሞቹ ድርጊት ለአባቱ መጥፎ ወሬ ይዞለት መጣ። BSB BSB: This is the account of Jacob. When Joseph was seventeen years old, he was tending the flock with his brothers, the sons of his father’s wives Bilhah and Zilpah, and he brought their father a bad report about them.
3 ULB እስራኤል ዮሴፍን በስተርጅናው ስለወለደው፣ ከልጆቹ ሁሉ አብልጦ ይወደው ነበር፣ በኅብረ ቀለማት ያጌጠ እጀ ጠባብም ሰፋለት። BSB BSB: Now Israel loved Joseph more than his other sons, because Joseph had been born to him in his old age; so he made him a robe of many colors.
4 ULB ወንድሞቹም አባታቸው ከእነርሱ አብልጦ የሚወደው መሆኑን ሲያዩ ዮሴፍን ጠሉት፤ በቅን አንደበት ሊያናግሩት አልቻሉም። BSB BSB: When Joseph’s brothers saw that their father loved him more than any of them, they hated him and could not speak a kind word to him.
5 ULB ዮሴፍ ሕልም አለመ፤ ሕልሙንም ለወንድሞቹ ሲነግራቸው የባሰ ጠሉት፤ BSB BSB: Then Joseph had a dream, and when he told it to his brothers, they hated him even more.
6 ULB እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ያየሁትን ሕልም ልንገራችሁ አድምጡኝ” BSB BSB: He said to them, “Listen to this dream I had:
7 ULB ‘እኛ ሁላችን በእርሻ ውስጥ ነዶ እናስር ነበር፤ የእኔ ነዶ ተነሣና ቀጥ ብሎ ቆመ፤ የእናንተ ነዶዎች ዙሪያውን ተሰብስበው ለእኔ ነዶ ሰገዱለት’” BSB BSB: We were binding sheaves of grain in the field, and suddenly my sheaf rose and stood upright, while your sheaves gathered around and bowed down to mine.”
8 ULB ወንድሞቹም፣ “ታዲያ በእኛ ላይ ንጉሥ ሆነህ ልትገዛን ታስባለህን?” ብለው ጠየቁት። ስለ ሕልሙና ስለተናገረው ቃል ከፊት ይልቅ ጠሉት። BSB BSB: “Do you intend to reign over us?” his brothers asked. “Will you actually rule us?” So they hated him even more because of his dream and his statements.
9 ULB እንደ ገናም ሌላ ሕልም አለመ፤ ለወንድሞቹም እነሆ፣ ሌላ ሕልም አለምሁ፣ ፀሐይና ጨረቃ፣ ዐሥራ አንድ ክዋክብትም ሲሰግዱልኝ ዐየሁ” ብሎ ነገራቸው። BSB BSB: Then Joseph had another dream and told it to his brothers. “Look,” he said, “I had another dream, and this time the sun and moon and eleven stars were bowing down to me.”
10 ULB ይህንኑ ለወንድሞቹ የነገራቸውን ሕልም ለአባቱም በነገረው ጊዜ፣ አባቱ፣ “ይህ ምን ዐይነት ሕልም ነው? እኔና እናትህ ወንድሞችህም በፊትህ ወደ ምድር ተጎንብሰን በርግጥ ልንሰግድልህ ነው?” ሲል ገሠጸው። BSB BSB: He told his father and brothers, but his father rebuked him and said, “What is this dream that you have had? Will your mother and brothers and I actually come and bow down to the ground before you?”
11 ULB ወንድሞቹ ቀኑበት፤ አባቱ ግን ነገሩን በልቡ ያዘው። BSB BSB: And his brothers were jealous of him, but his father kept in mind what he had said.
12 ULB አንድ ቀን የዮሴፍ ወንድሞች የአባታቸውን መንጋዎች ይዘው ወደ ሴኬም ተሰማሩ፤ BSB BSB: Some time later, Joseph’s brothers had gone to pasture their father’s flocks near Shechem.
13 ULB እስራኤልም ዮሴፍን፣ “እንደምታውቀው ወንድሞችህ መንጎቹን በሴኬም አካባቢ አሰማርተዋል፤ በል ተነሥ፣ ወደ እነርሱ ልላክህ” አለው። ዮሴፍም፣ “እሺ እሄዳለሁ” አለ። BSB BSB: Israel said to him, “Are not your brothers pasturing the flocks at Shechem? Get ready; I am sending you to them.” “I am ready,” Joseph replied.
14 ULB አባቱም፣ “በል እንግዲህ ሄድና የወንድሞችህንና የመንጋዎቹን ደኅንነት አይተህ ንገረኝ” አለው። በዚህ ዓይነት እስራኤል ዮሴፍን ከኬብሮን ሸለቆ ላከው። ዮሴፍም ሴኬም በደረሰ ጊዜ፣ BSB BSB: Then Israel told him, “Go now and see how your brothers and the flocks are faring, and bring word back to me.” So he sent him off from the Valley of Hebron. And when Joseph arrived in Shechem,
15 ULB ሜዳ ላይ ወዲያ ወዲህ ሲባዝን አንድ ሰው አግኝቶት፣ “ምን እየፈለግህ ነው?” ሲል ጠየቀው። BSB BSB: a man found him wandering in the field and asked, “What are you looking for?”
16 ULB ዮሴፍም፣ “ወንድሞቼን እየፈለግኋቸው ነው፤ መንጎቻቸውን የት እንዳሰማሩ ልትነግረኝ ትችላለህ?” አለው። BSB BSB: “I am looking for my brothers,” Joseph replied. “Can you please tell me where they are pasturing their flocks?”
17 ULB ሰውዬውም፣ “ከዚህ ሄደዋል፤ ደግሞም ‘ወደ ዶታይን እንሂድ’ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ” አለው። ከዚያም ዮሴፍ ወንድሞቹን ፍለጋ ሄደ፣ በዶታይን አቅራቢያም አገኛቸው። BSB BSB: “They have moved on from here,” the man answered. “I heard them say, ‘Let us go to Dothan.’” So Joseph set out after his brothers and found them at Dothan.
18 ULB ወንድሞቹም ዮሴፍ ወደ እነርሱ ሲመጣ በሩቅ ዐዩት፣ ወደ ነበሩበትም ስፍራ ከመድረሱ በፊት ሊገድሉት ተማከሩ። BSB BSB: Now Joseph’s brothers saw him in the distance, and before he arrived, they plotted to kill him.
19 ULB እነርሱ እንዲህ ተባባሉ፦ “ያ ሕልም አላሚ መጣ፤ BSB BSB: “Here comes that dreamer!” they said to one another.
20 ULB ኑ እንግደለውና ከጉድጓዶቹ በአንዱ ውስጥ እንጣለው፤ ከዚያም፣ ‘ክፉ አውሬ ነጥቆ በላው’ እንላለን፤ እስቲ ሕልሞቹ ሲፈጸሙ እናያለን።” BSB BSB: “Come now, let us kill him and throw him into one of the pits. We can say that a vicious animal has devoured him. Then we shall see what becomes of his dreams!”
21 ULB ሮቤል ግን ይህን ምክር ሲሰማ ከእጃቸው ሊያድነው ፈለገ እንዲህም አለ፤ “አንግደለው፤ BSB BSB: When Reuben heard this, he tried to rescue Joseph from their hands. “Let us not take his life,” he said.
22 ULB የሰው ደም አታፍስሱ፣ ከምትገድሉት ይልቅ በዚህ በበረሃ ባለው ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት” አላቸው። ሮቤል ይህን ያለው ሕይወቱን ከእጃቸው አትርፎ ወደ አባቱ ሊመልሰው ዐስቦ ነበር። BSB BSB: “Do not shed his blood. Throw him into this pit in the wilderness, but do not lay a hand on him.” Reuben said this so that he could rescue Joseph from their hands and return him to his father.
23 ULB ዮሴፍ ወደ ወንድሞቹ እንደደረሰ፣ የለበሳትን በኅብረ ቀለማት የጌጠች እጀ ጠባቡን ገፈፉት፤ BSB BSB: So when Joseph came to his brothers, they stripped him of his robe—the robe of many colors he was wearing—
24 ULB ይዘውም ወደ ጉድጓድ ጣሉት፤ ጉድጓዱም ውሃ የሌለበት ደረቅ ነበር። BSB BSB: and they took him and threw him into the pit. Now the pit was empty, with no water in it.
25 ULB ምግባቸውን ለመብላት ተቀመጡ፤ አሻግረው ሲመለከቱም ከገለዓድ የሚመጡ እስማኤላውያን ነጋዴዎች ጓዛቸውን በግመሎች ላይ ጭነው ተመለከቱ። ነጋዴዎቹ ሽቶ፣ በለሳን፣ ከርቤ በግመሎቻቸው ጭነው ወደ ግብፅ የሚወርዱ ነበሩ። BSB BSB: And as they sat down to eat a meal, they looked up and saw a caravan of Ishmaelites coming from Gilead. Their camels were carrying spices, balm, and myrrh on their way down to Egypt.
26 ULB ይሁዳም ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፤ “ወንድማችንን መግደልና አሟሟቱን መደበቅ ምን ይጠቅመናል? BSB BSB: Then Judah said to his brothers, “What profit will we gain if we kill our brother and cover up his blood?
27 ULB ከዚህ ይልቅ ለእስማኤላውያን ነጋዴዎች እንሽጠው፤ እጃችንን ግን በእርሱ ላይ አናንሳ። ምንም ቢሆን የሥጋ ወንድማችን ነው” ወንድሞቹም በሃሳቡ ተስማሙ። BSB BSB: Come, let us sell him to the Ishmaelites and not lay a hand on him; for he is our brother, our own flesh.” And they agreed.
28 ULB የምድያም ነጋዴዎች የሆኑ እስማሴላውያን በዚያ በኩል ያልፉ ነበር፤ ስለዚህ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጉድጓድ ጎትተው በማውጣት ለእነዚህ እስማኤላውያን በሃያ ብር ሸጡላቸው፣ እነርሱም ወደ ግብፅ ይዘውት ሄዱ። BSB BSB: So when the Midianite traders passed by, his brothers pulled Joseph out of the pit and sold him for twenty shekels of silver to the Ishmaelites, who took him to Egypt.
29 ULB ሮቤል ወደ ጉድጓዱ ተመልሶ ሲያይ፣ ዮሴፍን በማጣቱ ልብሱን በሐዘን ቀደደ። BSB BSB: When Reuben returned to the pit and saw that Joseph was not there, he tore his clothes,
30 ULB ወደ ወንድሞቹም ተመልሶ፣ “እነሆ፣ ልጁ እዚያ የለም! እንግዲህ እኔ ወዴት ብሄድ ይሻለኛል?” አለ። BSB BSB: returned to his brothers, and said, “The boy is gone! What am I going to do?”
31 ULB ከዚህ በኋላ አንድ ፍየል አረዱና የዮሴፍን ልብስ በደም ነከሩት። BSB BSB: Then they took Joseph’s robe, slaughtered a young goat, and dipped the robe in its blood.
32 ULB በኅብረ ቀለማት ያጌጠችውን እጀ ጠባብ ወደ አባታቸው ወስደው፣ “ይህን ወድቆ አገኘነው፤ የልጅህ እጀ ጠባብ መሆን አለመሆኑን እስቲ እየው” አሉት። BSB BSB: They sent the robe of many colors to their father and said, “We found this. Examine it to see whether it is your son’s robe or not.”
33 ULB እርሱ የልጁ ልብስ መሆኑን ተረድቶ፣ “ይህማ የልጄ እጀ ጠባብ ነው!፤ ክፉ አውሬ በልቶታል፣ በእርግጥም ዮሴፍ ተቦጫጭቆአል” አለ። BSB BSB: His father recognized it and said, “It is my son’s robe! A vicious animal has devoured him. Joseph has surely been torn to pieces!”
34 ULB ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ልብሱን ቀደደ፤ ማቅም ለብሶ ስለ ልጁ ብዙ ቀን አለቀሰ፤ BSB BSB: Then Jacob tore his clothes, put sackcloth around his waist, and mourned for his son many days.
35 ULB ወንዶችና ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት መጡ፤ እርሱ ግን ሊጽናና አልቻለም፣ “በሐዘን እንደተኮራመትሁ ልጄ ወዳለበት መቃብር እወርዳለሁ” አለ። ስለ ልጁም አለቀሰ። BSB BSB: All his sons and daughters tried to comfort him, but he refused to be comforted. “No,” he said. “I will go down to Sheol mourning for my son.” So his father wept for him.
36 ULB በዚህ ጊዜ የምድያም ነጋዴዎች ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወስደው፣ ከፈርዖን ሹማምንት አንዱ ለነበረው ለዘበኞች አለቃ፣ ለጲጥፋራ ሸጡት። BSB BSB: Meanwhile, the Midianites sold Joseph in Egypt to Potiphar, an officer of Pharaoh and captain of the guard.