1 ULB ከዚህም በኋላ የግብፅ ንጉሥ የመጠጥ አሳላፊውና የእንጀራ ቤት ኃላፊው ንጉሡን የሚያሳዝን በደል ፈጸሙ። BSB BSB: Some time later, the king’s cupbearer and baker offended their master, the king of Egypt.
2 ULB ፈርዖንም በመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃና በእንጀራ ቤቱ አዛዡ፣ በሁለቱም ሹማምንቱ ላይ እጅግ ተቆጣ፤ BSB BSB: Pharaoh was angry with his two officers, the chief cupbearer and the chief baker,
3 ULB በዘበኞቹ አለቃ ቤት ወዳለው ዮሴፍ ወደታሠረበት እስር ቤት አስገባቸው። BSB BSB: and imprisoned them in the house of the captain of the guard, the same prison where Joseph was confined.
4 ULB የዘበኞቹም አለቃ እስረኞቹን ለዮሴፍ አስረከባቸው፤ በእስር ቤትም ለጥቂት ጊዜ ቆዩ። BSB BSB: The captain of the guard assigned them to Joseph, and he became their personal attendant. After they had been in custody for some time,
5 ULB ታስረው የነበሩት የግብፅ ንጉሥ የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃና የእንጀራ ቤቱ አዛዥ፣ በአንድ ሌሊት የየራሳቸውን ሕልም ዐዩ፤ የሁለቱም ሕልም ለየራሱ የተለየ ፍቺ ነበረው። BSB BSB: both of these men—the Egyptian king’s cupbearer and baker, who were being held in the prison—had a dream on the same night, and each dream had its own meaning.
6 ULB በማግስቱ ጥዋት ዮሴፍ እነርሱ ወዳሉበት ክፍል በገባ ጊዜ ተክዘው አገኛቸውና፤ BSB BSB: When Joseph came to them in the morning, he saw that they were distraught.
7 ULB “ዛሬ በፊታችሁ ላይ ሐዘን የሚታየው ለምንድን ነው?” አላቸው። BSB BSB: So he asked the officials of Pharaoh who were in custody with him in his master’s house, “Why are your faces so downcast today?”
8 ULB እነርሱም፣ “ሁለታችንም ሕልም ዐየን፤ ነገር ግን የሚተረጉምልን ሰው አጣን” ሲሉ መለሱለት። ዮሴፍም፣ “ሕልም የመተርጎም ችሎታ የሚሰጥ እግዝአብሔር ነው፣ ስለዚህ የእያንዳንዳችሁን ሕልም ንገሩኝ” አላቸው። BSB BSB: “We both had dreams,” they replied, “but there is no one to interpret them.” Then Joseph said to them, “Don’t interpretations belong to God? Tell me your dreams.”
9 ULB ስለዚህ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ እንዲህ ሲል ሕልሙን ለዮሴፍ ነገረው፤ “ከፊት ለፊቴ አንዲት የወይን ተክል ዐየሁ፤ BSB BSB: So the chief cupbearer told Joseph his dream: “In my dream there was a vine before me,
10 ULB ተክሏም ሦስት ሐረጎች ነበሯት፤ ወዲያው እቆጥቁጣ አበበች፤ የወይን ዘለላውም ወዲያው በሰለ። BSB BSB: and on the vine were three branches. As it budded, its blossoms opened and its clusters ripened into grapes.
11 ULB የፈርዖንንም ጽዋ ይዤ ነበር፣ የወይኑን ፍሬ ለቅሜ በጽዋው ውስጥ ጨምቄ ጽዋውን በእጁ ሰጠሁት።” BSB BSB: Pharaoh’s cup was in my hand, and I took the grapes, squeezed them into his cup, and placed the cup in his hand.”
12 ULB ዮሴፍም እንዲህ አለው፤ “እንግዲህ የሕልሙ ትርጓሜ ይህ ነው፤ ሦስቱ ሐረግ ሦስት ቀን ነው፤ BSB BSB: Joseph replied, “This is the interpretation: The three branches are three days.
13 ULB በሦስት ቀን ውስጥ ፈርዖን ከእስር ቤት ያወጣሃል፣ ወደ ቀድሞ ሹመትህም ይመልስሃል፤ በፊት የመጠጥ አሳላፊ በነበርህበት ጊዜ ታደርግ እንደነበረው ኡሉ የፈርዖንን ጽዋ በእጁ ትሰጠዋለህ። BSB BSB: Within three days Pharaoh will lift up your head and restore your position. You will put Pharaoh’s cup in his hand, just as you did when you were his cupbearer.
14 ULB እንግዲህ፣ በጎ ነገር በገጠመህ ጊዜ፣ እኔን አስበህ ቸርነት አድርግልኝ፣ ስለ እኔም ለፈርዖን ንገርልኝ፤ ከዚህም እስር ቤት አስወጣኝ፤ BSB BSB: But when it goes well for you, please remember me and show me kindness by mentioning me to Pharaoh, that he might bring me out of this prison.
15 ULB ከዕብራውያን ምድር ወደዚህ የመጣሁት በአፈና ነው፤ አሁንም ቢሆን እዚህ እስር ቤት የተጣልሁት አንዳች ጥፋት ኖሮብኝ አይደለም።” BSB BSB: For I was kidnapped from the land of the Hebrews, and even here I have done nothing for which they should have put me in this dungeon.”
16 ULB የእንጀራ ቤት አዛዡም፣ ለመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ሕልም የተሰጠው ፍቺ ደስ የሚያሰኝ መሆኑን ሲሰማ፣ የራሱን ሕልም ለዮሴፍ እንዲህ ሲል ነገረው፤ “እኔም ደግሞ ሕልም አይቻለሁ፣ ሦስት መሶቦች በራሴ ላይ ተሸክሜ ነበር፤ BSB BSB: When the chief baker saw that the interpretation was favorable, he said to Joseph, “I too had a dream: There were three baskets of white bread on my head.
17 ULB በላይኛው መሶብ ውስጥ ለፈርዖን የተዘጋጀ የተለያየ ምግብ ነበረበት፣ ነገር ግን ወፎች ምግቡን ከመሶቡ እያነሱ የበሉት ነበር።” BSB BSB: In the top basket were all sorts of baked goods for Pharaoh, but the birds were eating them out of the basket on my head.”
18 ULB ዮሴፍም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “የሕልሙ ፍቺ ይህ ነው፤ ሦስቱ መሶብ ሦስት ቀን ነው፤ BSB BSB: Joseph replied, “This is the interpretation: The three baskets are three days.
19 ULB በሦስት ቀን ውስጥ ፈርዖን ራስህን ካስቆረጠ በኋላ በእንጨት ላይ ይሰቅልሃል፤ ወፎችም ሥጋህን የበሉታል።” BSB BSB: Within three days Pharaoh will lift off your head and hang you on a tree. Then the birds will eat the flesh of your body.”
20 ULB በሦስተኛው ቀን የፈርዖን ልደት በዓል ስለነበር ለመኳንንቱ ሁሉ ግብዣ አደረገ፤ በዚያኑ ዕለትም የመጠጥ አሳላፊዎቹን አለቃና የእንጀራ ቤት አዛዡን ሹማምንቱ ካሉበት ከእስር ቤት አወጣቸው። BSB BSB: On the third day, which was Pharaoh’s birthday, he held a feast for all his officials, and in their presence he lifted up the heads of the chief cupbearer and the chief baker.
21 ULB የመጠጥ አሳላፊዎቹን አለቃ ወደ ቀድሞ ሹመቱ መለሰው፤ እርሱም እንደ ቀድሞው ጽዋውን ለፈርዖን በእጁ ይሰጠው ጀመር፤ BSB BSB: Pharaoh restored the chief cupbearer to his position, so that he once again placed the cup in Pharaoh’s hand.
22 ULB የእንጀራ ቤት አዛዡን ግን ልክ ዮሴፍ እንደተረጎመላቸው ሰቀለው። BSB BSB: But Pharaoh hanged the chief baker, just as Joseph had described to them in his interpretation.
23 ULB የሆነው ሆኖ፣ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ዮሴፍን አላስታወሰውም፤ ረሳው። BSB BSB: The chief cupbearer, however, did not remember Joseph; he forgot all about him.