1 ULB ዮሴፍ እጅግ ከማዘኑ የተነሣ በአባቱ ፊት ተደፍቶ አለቀሰ ሳመውም። BSB BSB: Then Joseph fell upon his father’s face, wept over him, and kissed him.
2 ULB ከዚያም የአባቱ የእስራኤል አስከሬን እንዳይፈርስ ባለ መድኃኒት የሆኑ አገለጋዮች በመድኃኒት እንዲያሹት አዘዘ። ባለ መድኃኒቶቹም አስከሬኑ እንዳይፈርስ በመድኃኒት አሹት። BSB BSB: And Joseph directed the physicians in his service to embalm his father Israel. So they embalmed him,
3 ULB በአገሩ ልማድ መሠረት አስከሬኑ እንዳይፈርስ ማሸቱ አርባ ቀን ወሰደባቸው፤ ገብፃውያንም ሰባ ቀን አለቀሱለት። BSB BSB: taking the forty days required to complete the embalming. And the Egyptians mourned for him seventy days.
4 ULB የለቅሶው ወራት በተፈጸመ ጊዜ ዮሴፍ የፈርዖንን ባለሥልጣኖች እንዲህ አላቸው፤ “መልካም ፈቃዳችሁ ቢሆን እባካችሁ ለፈርዖን፣ BSB BSB: When the days of mourning had passed, Joseph said to Pharaoh’s court, “If I have found favor in your eyes, please tell Pharaoh that
5 ULB ‘አባቴ ለመሞት ሲቃረብ በከነዓን ምድር ባዘጋጀው መቃብር እንድቀብረው በመሐላ ቃል አስገብቶኛል፤ ስለዚህ ወደዚያ ሄጄ አባቴን ቀብሬ እንድመለስ ይፈቀድልኝ ሲል ጠይቆአል’ ብላችሁ ንገሩልኝ” አላቸው። BSB BSB: my father made me swear an oath when he said, ‘I am about to die. You must bury me in the tomb that I dug for myself in the land of Canaan.’ Now let me go and bury my father, and then return.”
6 ULB ፈርዖንም፣ “ባስማለህ መሠረት ሄደህ አባትህን ቅበር” አለው። BSB BSB: Pharaoh replied, “Go up and bury your father, as he made you swear to do.”
7 ULB ስለዚህ ዮሴፍ አባቱን ለመቅበር ሄደ፣ የፈርዖን ሹማምንት በሙሉ፣ የቤተ መንግሥቱ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች እንዲሁም የግብፅ ከፍተኛ ባለ ሥልጣኖች ሁሉ ተከተሉት። BSB BSB: Then Joseph went to bury his father, and all the servants of Pharaoh accompanied him—the elders of Pharaoh’s household and all the elders of the land of Egypt—
8 ULB እንደዚሁም የዮሴፍ ቤተ ሰቦች ወንድሞቹና ሌሎችም የአባቱ ቤተ ሰቦች ሁሉ ከዮሴር ጋር ሄዱ፣ በጌሤም የቀሩት ሕፃናት ልጆቻቸው፣ የበግ፣ የፍየልና የከብት መንጋዎቻቸው ብቻ ነበሩ። BSB BSB: along with all of Joseph’s household, and his brothers, and his father’s household. Only their children and flocks and herds were left in Goshen.
9 ULB እንዲሁም ሠረገሎች፣ ፈረሰኞች አብረውት ወጡ፤ አጀቡም እጅግ ብዙ ነበር። BSB BSB: Chariots and horsemen alike went up with him, and it was an exceedingly large procession.
10 ULB እነርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ካለው አጣድ ከተባለው ዐውድማ ሲደርሱ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ምርር ብለው አለቀሱ፤ ዮሴፍም በዚያ ለአባቱ ሰባት ቀን ለቅሶ ተቀመጠ። BSB BSB: When they reached the threshing floor of Atad, which is across the Jordan, they lamented and wailed loudly, and Joseph mourned for his father seven days.
11 ULB በዚያ የሚኖሩ ከነዓናውያን በአጣድ ዐውድማ የተደረገውን ልቅሶ ባዩ ጊዜ፣ “ይህ ለግብፃውያን መራራ ልቅሶአቸው ነው” አሉ። በዮርዳኖስ አጠገብ ያለው የዚያ ቦታ ስም አቤል ምጽራይም ተብሎ መጠራቱም ከዚሁ የተነሣ ነበር። BSB BSB: When the Canaanites of the land saw the mourning at the threshing floor of Atad, they said, “This is a solemn ceremony of mourning by the Egyptians.” Thus the place across the Jordan is called Abel-mizraim.
12 ULB በዚህ ሁኔታ የያዕቆብ ልጆች አባታቸው እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ BSB BSB: So Jacob’s sons did as he had charged them.
13 ULB አስከሬኑን ወደ ከነዓን ወስደው ከመምሬ በስተምሥራቅ በምትገኘው በማክፌላ ዋሻ ቀበሩት፤ ይህም ዋሻ አብርሃም ለመቃብር ቦት እንዲሆን ከኬጢያዊው ከኤፍሮን በገዛው እርሻ ውስጥ የሚገኝ ነው። BSB BSB: They carried him to the land of Canaan and buried him in the cave at Machpelah in the field near Mamre, which Abraham had purchased from Ephron the Hittite as a burial site.
14 ULB ዮሴፍ አባቱን ከቀበረ በኋላ ከወንድሞቹና ለቀብር አጅበውት ከሄዱት ሰዎች ሁሉ ጋር ሆኖ ወደ ግብፅ ተመለሰ። BSB BSB: After Joseph had buried his father, he returned to Egypt with his brothers and all who had gone with him to bury his father.
15 ULB የዮሴፍ ወንድሞች ከአባታቸው ሞት በኋላ፣ “ከፈጸምንበት በደል የተነሣ ዮሴፍ ቂም ይዞ በበቀልን ምን እናደርጋለን ተባባሉ። BSB BSB: When Joseph’s brothers saw that their father was dead, they said, “What if Joseph bears a grudge? Then he will surely repay us for all the evil that we did to him.”
16 ULB ስለዚህ እንዲህ የሚል መልእክት ላኩ፣ አባትህ ከመሞቱ በፊት፣ BSB BSB: So they sent word to Joseph, saying, “Before he died, your father commanded,
17 ULB ‘ለዮሴፍ ወንድሞችህ በአንተ ላይ የፈጸሙትን ኃጢአትና ክፉ በደል ይቅር በላቸው’ ብላችሁ ንገሩት የሚል ትእዛዝ አስተላልፎ ነበር። አሁንም የአባትህን አምላክ አገልጋዮች ኃጢአት ይቅር በለን።” ዮሴፍ ይህን በሰማ ጊዜ አለቀሰ። BSB BSB: ‘This is what you are to say to Joseph: I beg you, please forgive the transgression and sin of your brothers, for they did you wrong.’ So now, Joseph, please forgive the transgression of the servants of the God of your father.” When their message came to him, Joseph wept.
18 ULB ከዚያም ወንድሞቹ መጡና በፊቱ ተደፍተው፣ “እኛ የአንተ አገልጋዮች ነን” አሉት። BSB BSB: His brothers also came to him, bowed down before him, and said, “We are your slaves!”
19 ULB ዮሴፍ ግን እንዲህ አላቸው፤ “አትፍሩ፣ እኔ በእግዚአብሔር ምትክ የተቀመጥሁ አይደለሁም፣ BSB BSB: But Joseph replied, “Do not be afraid. Am I in the place of God?
21 ULB አሁንም ቢሆን አትፍሩ፤ ለእናንተና ለልጆቻችሁ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አደርግላችኋለሁ” በማለት በመልካም ንግግር አረጋጋቸው። BSB BSB: Therefore do not be afraid. I will provide for you and your little ones.” So Joseph reassured his brothers and spoke kindly to them.
22 ULB ዮሴፍ ከአባቱ ቤተ ሰቦች ጋር በግብፅ ተቀመጠ፤ አንድ መቶ ዐሥር ዓመትም ኖረ፤ BSB BSB: Now Joseph and his father’s household remained in Egypt, and Joseph lived to the age of 110.
23 ULB የኤፍሬምንም የልጅ ልጆች እስከ ሦስት ትውልድ ድረስ ዐየ። ከምናሴ የተወለደውንም የማኪርንም ልጆች በጭኑ ላይ አድርጎ አቀፋቸው። BSB BSB: He saw Ephraim’s sons to the third generation, and indeed the sons of Machir son of Manasseh were brought up on Joseph’s knees.
24 ULB ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፣ እኔ የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ እናንተ ግን እግዚአብሔር በረድኤት ይጎበኛችኋል፤ ከዚህም አገር አውጥቶ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ለመስጠት በመሐላ ቃል ወደገባላቸው ምድር ይመልሳችኋል። BSB BSB: Then Joseph said to his brothers, “I am about to die, but God will surely visit you and bring you up from this land to the land He promised on oath to Abraham, Isaac, and Jacob.”
25 ULB እግዚአብሔር በሚጎበኛችሁና ወደዚያች ምድር በሚመልሳችሁ ጊዜ ዐጽሜን ከዚህ ይዛችሁ የምትወጡ መሆናችሁን በማረጋገጥ ቃል ግቡልኝ” ብሎ አስማላቸው። BSB BSB: And Joseph made the sons of Israel take an oath and said, “God will surely attend to you, and then you must carry my bones up from this place.”
26 ULB ዮሴፍም ዕድሜው መቶ ዐሥር ዓመት ሲሞላው ሞተ፣ አስከሬኑንም መድኃኒት ቀብተው በሬሳ ሳጥን ካስገቡት በኋላ በግብፅ ምድር አስቀመጡት። BSB BSB: So Joseph died at the age of 110. And they embalmed his body and placed it in a coffin in Egypt.