1 ULB የሰው ልጆች በምድር ላይ እየበዙ ሲሄዱ ሴቶች ልጆች ተወለዱላቸው። BSB BSB: Now when men began to multiply on the face of the earth and daughters were born to them,
2 ULB የእግዚአብሔር ልጆችም የሰዎች ሴቶች ልጆች የሚስብ ውበት እንዳላቸው ተመለከቱ። ከእነርሱ መካከልም የመረጧቸውን ሚስቶች አድርገው ወሰዱ። BSB BSB: the sons of God saw that the daughters of men were beautiful, and they took as wives whomever they chose.
3 ULB እግዚአብሔርም፦ “እርሱ ሥጋ ስለሆነ መንፈሴ በሰው ላይ ለዘላለም አይኖርም፤ ዕድሜውም 120 ዓመት ይሆናል” አለ። BSB BSB: So the LORD said, “My Spirit will not contend with man forever, for he is mortal; his days shall be 120 years.”
4 ULB የእግዚአብሔር ልጆች ከሰዎች ሴቶች ልጆች ጋብቻ በፈጸሙና ልጆችን በወለዱበት በዚያን ጊዜ ከዚያም በኋላ ኔፊሊም የተባሉ ግዙፍ ሰዎች በምድር ላይ ነበሩ። እነርሱም በጥንት ዘመን ዝናን ያተረፉ ኅያላን ነበሩ። BSB BSB: The Nephilim were on the earth in those days—and afterward as well—when the sons of God had relations with the daughters of men. And they bore them children who became the mighty men of old, men of renown.
6 ULB እግዚአብሔር የሰው ልጆችን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ ልቡም አዘነ። BSB BSB: And the LORD regretted that He had made man on the earth, and He was grieved in His heart.
7 ULB በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር፦ “የፈጠርሁትን የሰው ልጅ ከምድር ገጽ አጠፋለሁ፤ ስለፈጠርኋቸው ተጸጽቻለሁና ከእነርሱም ጋር እንስሳትን፣ በደረታቸው የሚሳቡትን ፍጥረታትና የሰማይ ወፎችን ሁሉ አጠፋለሁ” አለ። BSB BSB: So the LORD said, “I will blot out man, whom I have created, from the face of the earth—every man and beast and crawling creature and bird of the air—for I am grieved that I have made them.”
8 ULB ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ አገኘ። BSB BSB: Noah, however, found favor in the eyes of the LORD.
9 ULB የኖኅ ታሪክ እንደሚከተለው ነው። ኖኅ በዘመኑ ከነበሩት ሰዎች ሁሉ ይልቅ ጻድቅና ከበደል የራቀ ሰው ነበር፤ የእግዚአብሔርንም መንገድ የሚከተል ሰው ነበር። BSB BSB: This is the account of Noah. Noah was a righteous man, blameless in his generation; Noah walked with God.
10 ULB ኖኅ ሴም፣ ካምና ያፌት የተባሉትን ሶስት ወንዶች ልጆች ወለደ። BSB BSB: And Noah had three sons: Shem, Ham, and Japheth.
11 ULB በእግዚአብሔር ፊት በክፉ ሥራ ረከሰች በዓመፅም ተሞላች። BSB BSB: Now the earth was corrupt in the sight of God, and full of violence.
12 ULB እግዚአብሔር ምድርን ተመለከተ፣ የተበላሸች እንደሆነችና በምድር የሚኖሩትም ሰዎች ሁሉ በክፋት እንደሚኖሩ አየ። BSB BSB: And God looked upon the earth and saw that it was corrupt; for all living creatures on the earth had corrupted their ways.
13 ULB እግዚአብሔርም ኖኅን፦ “ሥጋን የለበሰ ሁሉ ፍጻሜ ደርሶአል፣ ከእነርሱ የተነሳ ምድር በግፍ ተሞልታለችና። እኔም በእርግጥ ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ። BSB BSB: Then God said to Noah, “The end of all living creatures has come before Me, because through them the earth is full of violence. Now behold, I will destroy both them and the earth.
14 ULB አንተ ግን ከጥሩ እንጨት መርከብ ሥራ፤ መርከቧም ክፍሎች እንዲኖራት አድርግ፤ ውስጧንና ውጭዋንም በቅጥራን ለቅልቀው። BSB BSB: Make for yourself an ark of gopher wood; make rooms in the ark and coat it with pitch inside and out.
15 ULB እንደዚህ አድርገህ ሥራት፦ ርዝመቷ 140 ሜትር፣ ወርዷ 23 ሜትር፣ ከፍታዋ 13. 5 ሜትር ይሁን። BSB BSB: And this is how you are to build it: The ark is to be 300 cubits long, 50 cubits wide, and 30 cubits high.
16 ULB ለመርከቧ ጣራ አብጅላት፣ ጣራና ግድግዳው በሚጋጠምበት ቦታ ግማሽ ሜትር ክፍተት ተው፤ ከጎኗ በር አውጣላት፤ ባለ ሦስት ፎቅ አድርገህ ሥራት። BSB BSB: You are to make a roof for the ark, finish its walls a cubit from the top, place a door in the side of the ark, and build lower, middle, and upper decks.
17 ULB እኔም ከሰማይ በታች የሕይወት እስትንፋስ ያለባችውን ፍጡራን ሁሉ ለማጥፋት እነሆ በምድር ላይ የጥፋት ውሃ አወርዳለሁ፤ በምድር ላይ ያለ ሁሉ ይጠፋል። BSB BSB: And behold, I will bring floodwaters upon the earth to destroy every creature under the heavens that has the breath of life. Everything on the earth will perish.
18 ULB ከአንተ ጋር ግን ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ አንተና ሚስትህ፣ ልጆችህና የልጆችህ ሚስቶች ከአንተ ጋር ወደ መርከቧ ትገባላችሁ። BSB BSB: But I will establish My covenant with you, and you will enter the ark—you and your sons and your wife and your sons’ wives with you.
19 ULB ከአንተ ጋር በሕይወት እንዲቆዩ ከሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ወንድና ሴት እያደረግህ ሁለት ሁለቱን ወደ መርከቧ ታስገባለህ። BSB BSB: And you are to bring two of every living creature into the ark—male and female—to keep them alive with you.
20 ULB ከእያንዳንዱ የወፍ ወገን፣ ከእያንዳንዱ የእንስሳ ወገን፣ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረት ሁሉ በየወገናቸው በሕይወት ይቆዩ ዘንድ ወደ አንተ ይምጡ። BSB BSB: Two of every kind of bird and animal and crawling creature will come to you to be kept alive.
21 ULB ለአንተና ለእነዚህ ፍጥረቶች ሁሉ የሚበቃ ልዩ ልዩ ዓይነት ምግብ በመርከቡ ውስጥ አከማች።” BSB BSB: You are also to take for yourself every kind of food that is eaten and gather it as food for yourselves and for the animals.”
22 ULB ኖኅም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አደረገ። BSB BSB: So Noah did everything precisely as God had commanded him.