1 ULB ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር መጀመሪያ ቀን በነቢዩ በሐጌ በኩል ወደ ይሁዳ ገዢ ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤልና ወደ ሊቀ ካህኑ ኢዮሴዴቅ ልጅ ወደ ኢያሱ የያህዌ ቃል መጣ። BSB BSB: In the second year of the reign of Darius, on the first day of the sixth month, the word of the LORD came through Haggai the prophet to Zerubbabel son of Shealtiel, governor of Judah, and to Joshua son of Jehozadak, the high priest, stating
2 ULB የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ይህ ሕዝብ “እኛ የምንመጣበት ወይ የያህዌን ቤት የምንሠራበት ጊዜ ገና ነው” ይላል። BSB BSB: that this is what the LORD of Hosts says: “These people say, ‘The time has not yet come to rebuild the house of the LORD.’”
3 ULB የያህዌ ቃል በነቢዩ በሐጌ በኩ መጣ፤ እንዲህም አሉ፣ BSB BSB: Then the word of the LORD came through Haggai the prophet, saying:
4 ULB “ይህ ቤት ፈራርሶ እያለ፣ እናንተ ራሳችሁ ባማሩ ቤቶቻችሁ ለመኖር ጊዜው ነውን? BSB BSB: “Is it a time for you yourselves to live in your paneled houses, while this house lies in ruins?”
5 ULB ስለዚህ የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ እስቲ፣ የሠራችሁትን ቤት አስቡ! BSB BSB: Now this is what the LORD of Hosts says: “Consider carefully your ways.
6 ULB ብዙ ዘራችሁ፤ ግን ጥቂት አጭዳችሁ፤ በላችሁ ግን አልጠገባችሁም፤ ጠጣችሁ ግን አልረካችሁም። ለበሳችሁ ግን አልሞቃችሁም፤ ደመወዝ ተቀበላችሁ ግን ብዙ ቀዳዶች በሞሉበት መያዣ የማስቀመጥ ያህል ሆነባችሁ! BSB BSB: You have planted much but harvested little. You eat but never have enough. You drink but never have your fill. You put on clothes but never get warm. You earn wages to put into a bag pierced through.”
7 ULB የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ እስቲ የሠራችሁትን አስቡ! BSB BSB: This is what the LORD of Hosts says: “Consider carefully your ways.
8 ULB ወደ ተራራ ውጡ፤ እንጨትን አምጡና ቤቴን ሥሩ፤ ያኔ እኔ በእርሱ ደስ ይለኛል፣ እከብርበታለሁ! ይላል ያህዌ። BSB BSB: Go up into the hills, bring down lumber, and build the house, so that I may take pleasure in it and be glorified, says the LORD.
9 ULB ብዙ ጠበቃችሁ፤ ግን እኔ እፍ ስላልሁበት ወደ ቤት ያመጣችሁት ግን ጥቂት ነው፤ እንዲህ ያደረግሁት ለምን ይመስላችኋል? የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል! ምክንያቱም የእኔ ቤት ፈርሶ እያለ፣ ሰው ሁሉ በገዛ ራሱ ቤት እጅግ ደስ በመሰኘቱ ነው። BSB BSB: You expected much, but behold, it amounted to little. And what you brought home, I blew away. Why? declares the LORD of Hosts. Because My house still lies in ruins, while each of you is busy with his own house.
10 ULB ከዚህ የተነሣ ሰማያት ጠል ከለከሉ፤ ምድርም ፍሬዋን ነሣች። BSB BSB: Therefore, on account of you the heavens have withheld their dew and the earth has withheld its crops.
11 ULB እኔ በምድሪቱና በተራሮች፤ በእህሉና በአዲሱ ወይን ጠጅ፤ በዘይቱና ምድር በምትሰጠው ሁሉ ላይ፣ በሰዎችና በእንስሳት፣ በእጆቻችሁ ሥራ ሁሉ ላይ ድርቅ አመጣለሁ! BSB BSB: I have summoned a drought on the fields and on the mountains, on the grain, new wine, and oil, and on whatever the ground yields, on man and beast, and on all the labor of your hands.”
12 ULB ከዚህ በኋላ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና ሊቀ ካህኑ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ፣ ከምርኮ ከተረፉት ሕዝብ ሁሉ ጋር የአምላካቸው የያህዌን ድምጽ ሰሙ፤ አምላካቸው ያህዌ ልኮታልና ለነቢዩ ሐጌ ቃል ታዘዙ። ሕዝቡም ያህዌን ፈሩ። BSB BSB: Then Zerubbabel son of Shealtiel and Joshua son of Jehozadak, the high priest, as well as all the remnant of the people, obeyed the voice of the LORD their God and the words of the prophet Haggai, because the LORD their God had sent him. So the people feared the LORD.
13 ULB ከዚያም የያህዌ መልእክተኛ ሐጌ ለሕዝቡ የያህዌን መልእክት እንዲህ በማለት ተናገረ፤ “እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ! ይህ የያህዌ ቃል ነው! BSB BSB: Haggai, the messenger of the LORD, delivered the message of the LORD to the people: “I am with you,” declares the LORD.
14 ULB ስለዚህ ሄደው የአምላካቸውን የሠራዊት ጌታ የያህዌን ቤት እንዲሠሩ የይሁዳን ገዢ የሰላትያል ልጅ የዘሩባቤልን መንፈስና የኢዮሴዴቅ ልጅ የካህኑ ኢያሱን መንፈስ፣ እንዲሁም ከምርኮ የተረፉትን ሰዎች ሁሉ መንፈስ ያህዌ አነሣሣ። BSB BSB: So the LORD stirred the spirit of Zerubbabel son of Shealtiel, governor of Judah, and the spirit of Joshua son of Jehozadak, the high priest, as well as the spirit of all the remnant of the people. And they came and began the work on the house of the LORD of Hosts, their God,
15 ULB ይህ የሆነው በንጉሥ ዳርዮስ ሁለተኛ ዓመት በስድስተኛው ወር ሃያ አራተኛ ቀን ነው። BSB BSB: on the twenty-fourth day of the sixth month, in the second year of King Darius.