2 ULB በእምነታችን ጀማሪና ፍጹም አድራጊ ኢየሱስ ላይ ዓይኖቻችን እንትከል። እርሱ ከፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉንና መስቀሉ የሚያስከትለውን ውርደት ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል። BSB BSB: Let us fix our eyes on Jesus, the author and perfecter of our faith, who for the joy set before Him endured the cross, scorning its shame, and sat down at the right hand of the throne of God.
3 ULB እንዳትደክሙ ወይም ልባችሁ እንዳይዝል፣ ከኃጢአተኞች የተሰነዘረበትን እንዲህ ያለውን የጥላቻ ንግግር የታገሠውን እርሱን አስቡ። BSB BSB: Consider Him who endured such hostility from sinners, so that you will not grow weary and lose heart.
4 ULB ደም እስከማፍሰስ ድረስ ኃጢአትን አልተቃወማችሁም፣ አልታገላችሁትምም። BSB BSB: In your struggle against sin, you have not yet resisted to the point of shedding your blood.
5 ULB ደግሞም እንደ ልጆች፡ “ልጄ ሆይ የጌታን ቅጣት አታቅልል፣ በሚቀጣህም ጊዜ ልብህ አይዛል። BSB BSB: And you have forgotten the exhortation that addresses you as sons: “My son, do not take lightly the discipline of the Lord, and do not lose heart when He rebukes you.
6 ULB ጌታ የሚወደውን ይገሥጻል፣ የሚቀበለውን ማንኛውንም ልጅ ይቀጣል" በማለት የተናገራችሁን ማበረታቻ ምክር ረስታችኋል። BSB BSB: For the Lord disciplines the one He loves, and He chastises every son He receives.”
7 ULB አባት በልጆቹ እንደሚደረግ እግዚአብሔርም በእናንተ ላይ ስለሚያደርግ፣ መከራን እንደ ተግሣጽ በመቁጠር ታገሡ። ለመሆኑ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው? BSB BSB: Endure suffering as discipline; God is treating you as sons. For what son is not disciplined by his father?
8 ULB ነገር ግን እኛ ሁላችን ከምንካፈለው ተግሣጽ ውጭ ከሆናችሁ፣ ዲቃሎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም። BSB BSB: If you do not experience discipline like everyone else, then you are illegitimate children and not true sons.
9 ULB ከዚህም በላይ የሚቀጡን ምድራዊ አባቶች ነበሩን፤ እኛም እናከብራቸው ነበር። ይልቁንስ መንፈስ ለሆነው አባት እየታዘዝን መኖር የቱን ያህል ይገባናል? BSB BSB: Furthermore, we have all had earthly fathers who disciplined us, and we respected them. Should we not much more submit to the Father of our spirits and live?
10 ULB በእርግጥ አባቶቻችን ለእነርሱ መልካም መስሎ እንደታያቸው ለጥቂት ጊዜ ይቀጡን ነበር፣ እግዚአብሔር ግን የእርሱን የቅድስናው ተካፋዮች እንድንሆን ለጥቅማችን ያቀጣናል። BSB BSB: Our fathers disciplined us for a short time as they thought best, but God disciplines us for our good, so that we may share in His holiness.
11 ULB ቅጣት በወቅቱ የሚያም እንጂ አስደሳች አይደለም። ይሁን እንጂ፣ ለለመዱት በመጨረሻ ሰላማዊ የጽድቅ ፍሬን ያፈራል። BSB BSB: No discipline seems enjoyable at the time, but painful. Later on, however, it yields a harvest of righteousness and peace to those who have been trained by it.
12 ULB ስለዚህ የዛሉ እጆቻችሁን ወደ ላይ አንሡ፣ የደከሙ ጉልበቶቻችሁንም እንደገና አበርቱ፤ BSB BSB: Therefore strengthen your limp hands and weak knees.
13 ULB የሚያነክስ ማንም ቢኖር እንዲፈወስ እንጂ እንዳይናጋ እግሮቻችሁ የሚራመዱባቸውን መንገዶች ቀና አድርጉ። BSB BSB: Make straight paths for your feet, so that the lame may not be disabled, but rather healed.
14 ULB ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ተከታተሉ፣ ቅድስናንም ተከታተሉ፣ ያለ ቅድስና ማንም ጌታን ሊያይ አይችልም። BSB BSB: Pursue peace with everyone, as well as holiness, without which no one will see the Lord.
15 ULB ማንም ከእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጎድል፣ መራራ ሥርም አድጎ እንዳያስጨንቅና ብዙዎችን እንዳይመርዝ ተጠንቀቁ። BSB BSB: See to it that no one falls short of the grace of God, and that no root of bitterness springs up to cause trouble and defile many.
16 ULB ለአንድ መብል ብሎ ብኩርናውን እንደሸጠ እንደ ኤሳው እግዚአብሔርን የማይፈራ፣ ወይም ሴሰኛ የሆነ ማንም እንዳይኖር ተጠንቀቁ። BSB BSB: See to it that no one is sexually immoral, or is godless like Esau, who for a single meal sold his birthright.
17 ULB ከዚያ በኋላ በረከትን ለመውረስ እያለቀሰ በትጋት ቢፈልግም፣ ከአባቱ ዘንድ የይቅርታ እድል እንዳጣና እንደተጣለ ታውቃላችሁ። BSB BSB: For you know that afterward, when he wanted to inherit the blessing, he was rejected. He could find no ground for repentance, though he sought the blessing with tears.
18 ULB የሚቃጠል እሳት፣ ጨለማ፣ ጭጋግና ማዕበል ወዳለበት በእጅ ሊነካ ወደሚችል ተራራ ገና አልመጣችሁም። BSB BSB: For you have not come to a mountain that can be touched and that is burning with fire; to darkness, gloom, and storm;
19 ULB የሰሙትም ሌላ ቃል እንዳይነገራቸው እስከሚለምኑ ወዳደረሳቸው ቃልን ወደሚያሰማ ድምጽ ወይም የመለከት ጩኹት ገና አልመጣችሁም። BSB BSB: to a trumpet blast or to a voice that made its hearers beg that no further word be spoken.
20 ULB ይህም፣ “እንስሳም እንኳ ቢሆን ተራራውን ከነካ በድንጋይ ይወገር” ተብሎ የተሰጠውን ትእዛዝ ሊሸከሙት አልቻሉም። BSB BSB: For they could not bear what was commanded: “If even an animal touches the mountain, it must be stoned.”
21 ULB ሙሴ፣ “እጅግ ስለፈራሁ እየተንቀጠቀጥሁ ነኝ” እስከሚል ድረስ ይህ ስፍራ አስፈሪ ነበር። BSB BSB: The sight was so terrifying that even Moses said, “I am trembling with fear.”
22 ULB አሁን ግን፣ የሕያው እግዚአብሔር ከተማ ወደሆነችው ወደ ጽዮን ተራራ፣ አእላፋት መላእክት በደስታ ወደሚያመልኩባት ሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም መጥታችኋል፤ BSB BSB: Instead, you have come to Mount Zion, to the city of the living God, the heavenly Jerusalem. You have come to myriads of angels
23 ULB በሰማይ ወደሚገኙት የበኩራን ሁሉ ጉባኤ፣ የሁሉም ፈራጅ ወደሆነው እግዚአብሔርና ፍጹም የተደረጉ የጻድቃን መንፈሶች ወዳሉበት መጥታችኋል፤ BSB BSB: in joyful assembly, to the congregation of the firstborn, enrolled in heaven. You have come to God the Judge of all, to the spirits of the righteous made perfect,
24 ULB የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ወደሆነው ኢየሱስና ከአቤል ደም የተሻለውን ወደሚናገር ወደተረጨው ደም ደርሳችኋል። BSB BSB: to Jesus the mediator of a new covenant, and to the sprinkled blood that speaks a better word than the blood of Abel.
25 ULB የሚናገራችሁን እምቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ። እነርሱ በምድር ላይ ሆኖ ያስጠነቀቃቸውን እምቢ በማለታቸው ካላመለጡ፣ በሰማይ ሆኖ ከሚያስጠነቅቀን በእርግጥ አናመልጥም። BSB BSB: See to it that you do not refuse Him who speaks. For if the people did not escape when they refused Him who warned them on earth, how much less will we escape if we reject Him who warns us from heaven?
26 ULB በዚያን ጊዜ ድምጹ ምድርን አናወጠ። ነገር ግን፣ “አንድ ጊዜ ደግሜ ምድርን ብቻ ሳይሆን ሰማያትንም አናውጣለሁ” በማለት አሁን ተስፋ ሰጥቷል። BSB BSB: At that time His voice shook the earth, but now He has promised, “Once more I will shake not only the earth, but heaven as well.”
27 ULB “አንድ ጊዜ ደግሜ” የሚል ቃል፣ ያልተናወጡ ነገሮች መጽናታቸውን፣ የተናወጡት ማለትም የተፈጠሩት ነገሮች መወገዳቸውን ያመላክታል። BSB BSB: The words “Once more” signify the removal of what can be shaken—that is, created things—so that the unshakable may remain.
28 ULB ስለዚህ፣ ሊናወጥ የማይችል መንግሥት ስለተቀብልን አምላካችንን እናመስግነው፣ ደግሞም እግዚአብሔርን ተቀባይነት ባለው በአክብሮትና በፍርሃት እናምልከው፣ BSB BSB: Therefore, since we are receiving an unshakable kingdom, let us be filled with gratitude, and so worship God acceptably with reverence and awe.
29 ULB ምክንያቱም አምላካችን የሚባላ እሳት ነው። BSB BSB: “For our God is a consuming fire.”
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.