1 ULB እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ማዳኔ ሊመጣ፣ ጽድቄም ሊገለጥ ቀርቦአልና ፍርድን ጠብቁ ጽድቅንም አድርጉ። BSB BSB: This is what the LORD says: “Maintain justice and do what is right, for My salvation is coming soon, and My righteousness will be revealed.
2 ULB ይህን የሚያደርግ ሰው ይህንንም የሚይዝ የሰው ልጅ፣ እንዳያረክሰው ሰንበትንም የሚጠብቅ እጁንም ክፋት ከማድረግ የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።" BSB BSB: Blessed is the man who does this, and the son of man who holds it fast, who keeps the Sabbath without profaning it and keeps his hand from doing any evil.”
3 ULB ወደ እግዚአብሔርም የተጠጋ መጻተኛ፣ "በእውነት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ይለየኛል" አይበል፤ ጃንደረባም፣ "ተመልከቱ፣ እኔ ደረቅ ዛፍ ነኝ አይበል።" BSB BSB: Let no foreigner who has joined himself to the LORD say, “The LORD will utterly exclude me from His people.” And let the eunuch not say, “I am but a dry tree.”
4 ULB እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና፣ BSB BSB: For this is what the LORD says: “To the eunuchs who keep My Sabbaths, who choose what pleases Me and hold fast to My covenant—
5 ULB "በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።" BSB BSB: I will give them, in My house and within My walls, a memorial and a name better than that of sons and daughters. I will give them an everlasting name that will not be cut off.
6 ULB ያገለግሉት ዘንድ የእግዚአብሔርንም ስም ይወድዱ ዘንድ ባሪያዎቹም ይሆኑ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር የሚጠጉትንም መጻተኞች፣ እንዳያረክሱት ሰንበትን የሚጠብቁትን ቃል ኪዳኔንም የሚይዙትን ሁሉ፣ BSB BSB: And the foreigners who join themselves to the LORD to minister to Him, to love the name of the LORD, and to be His servants—all who keep the Sabbath without profaning it and who hold fast to My covenant—
7 ULB "ወደ ተቀደሰ ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፣ በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ፤ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት ይባላልና የሚቃጠለውን መሥዋዕታቸውንና ሌላ መሥዋዕታቸውን በመሠዊያዬ ላይ እቀበላለሁ። BSB BSB: I will bring them to My holy mountain and make them joyful in My house of prayer. Their burnt offerings and sacrifices will be accepted on My altar, for My house will be called a house of prayer for all the nations.”
8 ULB ከእስራኤል የተበተኑትን የሚሰበስብ ጌታ እግዚአብሔር፣ ወደ ተሰበሰቡት ዘንድ ሌሎችን እሰበስብለታለሁ" ይላል። BSB BSB: Thus declares the Lord GOD, who gathers the dispersed of Israel: “I will gather to them still others besides those already gathered.”
9 ULB እናንተ የምድረ በዳ አራዊት ሁሉ፣ እናንተም የዱር አራዊት ሁሉ፣ ትበሉ ዘንድ ቅረቡ! BSB BSB: Come, all you beasts of the field; eat greedily, all you beasts of the forest.
10 ULB ጕበኞቹ ዕውሮች ናቸው፣ ሁሉ ያለ እውቀት ናቸው፤ ሁሉም ዲዳ የሆኑ ውሾች ናቸው ይጮኹም ዘንድ አይችሉም፤ ሕልምን ያልማሉ፤ ይተኛሉ፤ ማንቀላፋትንም ይወድዳሉ። BSB BSB: Israel’s watchmen are blind, they are all oblivious; they are all mute dogs, they cannot bark; they are dreamers lying around, loving to slumber.
11 ULB መብል ወዳጆች ከቶ የማይጠግቡ ውሾች ናቸው፤ እነርሱም ያስተውሉ ዘንድ የማይችሉ እረኞች ናቸው፤ ሁሉ ወደ መንገዳቸው፣ ከፊተኛው እስከ ኋለኛው ድረስ ሁሉ፣ እያንዳንዳቸው ወደ ጥቅማቸው ዘወር ብለዋል። BSB BSB: Like ravenous dogs, they are never satisfied. They are shepherds with no discernment; they all turn to their own way, each one seeking his own gain:
12 ULB "ኑ፣ የወይን ጠጅ እንውሰድ፣ በሚያሰክርም መጠጥ እንርካ፤ ዛሬም እንደ ሆነ እንዲሁ ነገ ይሆናል፣ ከዛሬም ይልቅ እጅግ ይበልጣል" ይላሉ። BSB BSB: “Come, let me get the wine, let us imbibe the strong drink, and tomorrow will be like today, only far better!”
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.