1 ULB ጻድቅ ይጠፋል፣ በልቡም ነገሩን የሚያኖር የለም፤ ምሕረተኞችም ይወገዳሉ፣ ጽድቅም ከክፋት ፊት እንደ ተወገደ ማንም አያስተውልም። BSB BSB: The righteous perish, and no one takes it to heart; devout men are taken away, while no one considers that the righteous are taken away from the presence of evil.
2 ULB ወደ ሰላም ይገባል፤ በቅንነት የሄደ በአልጋው ላይ ያርፋል። BSB BSB: Those who walk uprightly enter into peace; they find rest, lying down in death.
3 ULB እናንተ የአስማተኛይቱ ልጆች፣ የአመንዝራውና የጋለሞታይቱ ዘር፣ ወደዚህ ቅረቡ። BSB BSB: “But come here, you sons of a sorceress, you offspring of adulterers and prostitutes!
4 ULB በማን ታላግጣላችሁ? በማንስ ላይ አፋችሁን ታላቅቃላችሁ? ምላሳችሁንስ በማን ላይ ታስረዝማላችሁ? BSB BSB: Whom are you mocking? At whom do you sneer and stick out your tongue? Are you not children of transgression, offspring of deceit,
5 ULB እናንተ በአድባር ዛፎች መካከል በለመለመም ዛፍ ሁሉ በታች በፍትወት የምትቃጠሉ፣ እናንተም በሸለቆች ውስጥ በዓለትም ስንጣቂዎች በታች ሕፃናትን የምታርዱ፣ የዓመፅ ልጆችና የሐሰት ዘር አይደላችሁምን? BSB BSB: who burn with lust among the oaks, under every luxuriant tree, who slaughter your children in the valleys, under the clefts of the rocks?
6 ULB በሸለቆው ውስጥ ያሉ የለዘቡ ድንጋዮች እድል ፈንታሽ ናቸው፣ እነርሱም ዕጣሽ ናቸው፤ ለእነርሱም የመጠጥ ቍርባን አፍስሰሻል፣ የእህልንም ቍርባን አቅርበሻል። እንግዲህ በዚህ ነገር አልቈጣምን? BSB BSB: Your portion is among the smooth stones of the valley; indeed, they are your lot. Even to them you have poured out a drink offering and offered a grain offering. Should I relent because of these?
7 ULB ከፍ ባለውም በረዘመውም ተራራ ላይ መኝታሽን አደረግሽ፣ መሥዋዕትንም ትሠዊ ዘንድ ወደዚያ ወጣሽ። BSB BSB: On a high and lofty hill you have made your bed, and there you went up to offer sacrifices.
8 ULB ከመዝጊያውና ከመቃኑ በኋላ መታሰቢያሽን አደረግሽ፤ እኔን ትተሽ ለሌላ ተገልጠሻል፣ ወጥተሽ መኝታሽን አስፍተሻል፤ ቃል ኪዳንም ተጋባሻቸው፣ ባየሽበትም ስፍራ ሁሉ መኝታቸውን ወደድሽ። BSB BSB: Behind the door and doorpost you have set up your memorial. Forsaking Me, you uncovered your bed; you climbed up and opened it wide. And you have made a pact with those whose bed you have loved; you have gazed upon their nakedness.
9 ULB ዘይትም ይዘሽ ወደ ንጉሡ ሄድሽ፣ ሽቱሽንም አበዛሽ፣ መልእክተኞችሽንም ወደ ሩቅ ላክሽ፣ እስከ ሲኦልም ድረስ ተዋረድሽ። BSB BSB: You went to Molech with oil and multiplied your perfumes. You have sent your envoys a great distance; you have descended even to Sheol itself.
10 ULB በመንገድሽም ብዛት ደከምሽ፣ ነገር ግን፣ "ተስፋ የለም" አላልሽም፤ የጕልበትን መታደስ አገኘሽ፣ ስለዚህም አልዛልሽም። BSB BSB: You are wearied by your many journeys, but you did not say, “There is no hope!” You found renewal of your strength; therefore you did not grow weak.
11 ULB "ሐሰትን የተናገርሺው እኔንም ያላሰብሺው በልብሽም ነገሩን ያላኖርሺው ማንን ሰግተሽ ነው? ማንንስ ፈርተሽ ነው? እኔ ብዙ ጊዜ ዝም አልሁ፣ አንቺም አልፈራሽም። BSB BSB: Whom have you dreaded and feared, so that you lied and failed to remember Me or take this to heart? Is it not because I have long been silent that you do not fear Me?
12 ULB እኔ ጽድቅሽን እናገራለሁ፣ ሥራሽም አይረባሽም። BSB BSB: I will expose your righteousness and your works, and they will not profit you.
13 ULB ወደ አንቺ የሰበሰብሻቸው በጮኽሽ ጊዜ ይታደጉሽ፤ ንፋስ ግን ይወስዳቸዋል ሽውሽውታም ሁሉን ያስወግዳቸዋል። በእኔ የታመነ ግን ምድሪቱን ይገዛል፣ የተቀደሰውንም ተራራዬን ይወርሳል። BSB BSB: When you cry out, let your companies of idols deliver you! Yet the wind will carry off all of them, a breath will take them away. But he who seeks refuge in Me will inherit the land and possess My holy mountain.”
14 ULB እርሱም፣ 'ጥረጉ፣ መንገድን አዘጋጁ! ከሕዝቤም መንገድ ዕንቅፋትን አውጡ!" ይላል። BSB BSB: And it will be said, “Build it up, build it up, prepare the way, take every obstacle out of the way of My people.”
15 ULB ለዘላለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፣ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል፣ "የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፣ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፣ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ። BSB BSB: For thus says the One who is high and lifted up, who inhabits eternity, whose name is Holy: “I dwell in a high and holy place, and with the oppressed and humble in spirit, to restore the spirit of the lowly and revive the heart of the contrite.
16 ULB መንፈስም የፈጠርሁትም ነፍስ ከፊቴ እንዳይዝል ለዘላለም አልጣላም፣ ሁልጊዜም አልቈጣም። BSB BSB: For I will not accuse you forever, nor will I always be angry; for then the spirit of man would grow weak before Me—the breath of life I have made.
17 ULB ስለ ኃጢአቱ ጥቂት ጊዜ ተቈጥቼ ቀሠፍሁት፣ ፊቴን ሰውሬ ተቈጣሁ፤ እርሱም በልቡ መንገድ እያፈገፈገ ሄደ። BSB BSB: I was enraged by his sinful greed, so I struck him and hid My face in anger; yet he kept turning back to the desires of his heart.
18 ULB መንገዱን አይቻለሁ እፈውሰውማለሁ፣ እመራውማለሁ፣ ለእርሱና ስለ እርሱም ለሚያለቅሱ መጽናናትን እመልሳለሁ። BSB BSB: I have seen his ways, but I will heal him; I will guide him and restore comfort to him and his mourners,
19 ULB የከንፈሮችን ፍሬ እፈጥራለሁ። በሩቅም በቅርብም ላለው ሰላም ሰላም ይሁን፣ እፈውሰውማለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር። BSB BSB: bringing praise to their lips. Peace, peace to those far and near,” says the LORD, “and I will heal them.”
20 ULB ክፉዎች ግን እንደሚንቀሳቀስ ባሕር ናቸው፤ ጸጥ ይል ዘንድ አይችልምና፣ ውኆቹም ጭቃና ጕድፍ ያወጣሉና። BSB BSB: But the wicked are like the storm-tossed sea, for it cannot be still, and its waves churn up mire and muck.
21 ULB ለክፉዎች ሰላም የላቸውም" ይላል አምላኬ። BSB BSB: “There is no peace,” says my God, “for the wicked.”
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.