1 ULB "በኃይልህ ጩኽ፣ አትቈጥብ፣ ድምፅህን እንደ መለከት አንሣ፣ ለሕዝቤ መተላለፋቸውን ለያዕቆብ ቤትም ኃጢአታቸውን ንገር። BSB BSB: “Cry aloud, do not hold back! Raise your voice like a ram’s horn. Declare to My people their transgression and to the house of Jacob their sins.
2 ULB ነገር ግን ዕለት ዕለት ይሹኛል መንገዴንም ያውቁ ዘንድ ይወድዳሉ፤ ጽድቅን እንዳደረጉ የአምላካቸውንም ፍርድ እንዳልተዉ ሕዝብ እውነተኛውን ፍርድ ይለምኑኛል። ወደ እግዚአብሔርም ለመቅረብ ይወድዳሉ። BSB BSB: For day after day they seek Me and delight to know My ways, like a nation that does what is right and does not forsake the justice of their God. They ask Me for righteous judgments; they delight in the nearness of God.”
3 ULB 'ስለ ምን ጾምን፣' አንተም 'አልተመለከትኸንም? ሰውነታችንንስ ስለ ምን አዋረድን፣ አንተም አላወቅህም?' ይላሉ። ተመልከቱ፣ በጾማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ፣ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ። BSB BSB: “Why have we fasted, and You have not seen? Why have we humbled ourselves, and You have not noticed?” “Behold, on the day of your fast, you do as you please, and you oppress all your workers.
4 ULB ተመልከቱ፣ ለጥልና ለክርክር ትጾማላችሁ በግፍ ጡጫም ትማታላችሁ፤ ድምፃችሁንም ወደ ላይ ታሰሙ ዘንድ ዛሬ እንደምትጾሙት አትጾሙም። BSB BSB: You fast with contention and strife to strike viciously with your fist. You cannot fast as you do today and have your voice be heard on high.
5 ULB እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ ነውን? ሰውስ ነፍሱን የሚያዋርደው እንደዚህ ባለ ቀን ነውን? በውኑ ራሱን እንደ እንግጫ ዝቅ ያደርግ ዘንድ ማቅንና አመድንም በበታቹ ያነጥፍ ዘንድ ነውን? በውኑ ይህን ጾም፣ በእግዚአብሔርም ዘንድ የተወደደ ቀን ትለዋለህን? BSB BSB: Is this the fast I have chosen: a day for a man to deny himself, to bow his head like a reed, and to spread out sackcloth and ashes? Will you call this a fast and a day acceptable to the LORD?
6 ULB እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? የክፋት በደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፣ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፣ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፣ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን? BSB BSB: Isn’t this the fast that I have chosen: to break the chains of wickedness, to untie the cords of the yoke, to set the oppressed free and tear off every yoke?
7 ULB እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድ፣ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፣ የተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፣ ከሥጋ ዘምድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን? BSB BSB: Isn’t it to share your bread with the hungry, to bring the poor and homeless into your home, to clothe the naked when you see him, and not to turn away from your own flesh and blood?
8 ULB የዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፣ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል፣ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፣ የእግዚአብሔርም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል። BSB BSB: Then your light will break forth like the dawn, and your healing will come quickly. Your righteousness will go before you, and the glory of the LORD will be your rear guard.
9 ULB የዚያን ጊዜ ትጠራለህ፣ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም፣ "እነሆኝ" ይላል። ከመካከልህ ቀንበርን ብታርቅ፣ ጣትህንም መጥቀስ ብትተው፣ BSB BSB: Then you will call, and the LORD will answer; you will cry out, and He will say, ‘Here I am.’ If you remove the yoke from your midst, the pointing of the finger and malicious talk,
10 ULB ባታንጐራጕርም፣ ነፍስህንም ለተራበ ብታፈስስ፣ የተጨነቀውንም ነፍስ ብታጠግብ፣ ብርሃንህ በጨለማ ይወጣል ጨለማህም እንደ ቀትር ይሆናል። BSB BSB: and if you give yourself to the hungry and satisfy the afflicted soul, then your light will go forth in the darkness, and your night will be like noonday.
11 ULB እግዚአብሔርም ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል። አንተም እንደሚጠጣ ገነት፣ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ። BSB BSB: The LORD will always guide you; He will satisfy you in a sun-scorched land and strengthen your frame. You will be like a well-watered garden, like a spring whose waters never fail.
12 ULB ከዱሮ ዘመን የፈረሱት ስፍራዎች ይሠራሉ፣ የብዙ ትውልድም መሠረት ይታነጻል፤ አንተም፣ "ቅጥሩን ጠጋኝ፣" "የመኖሪያ መንገድን አዳሽ" ትባላለህ። BSB BSB: Your people will rebuild the ancient ruins; you will restore the age-old foundations; you will be called Repairer of the Breach, Restorer of the Streets of Dwelling.
13 ULB ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ እግርህን ከሰንበት ብትመልስ፣ ሰንበትንም ደስታ፣ እግዚአብሔርም የቀደሰውን ክቡር ብትለው፣ የገዛ መንገድህንም ከማድረግ ፈቃድህንም ከማግኘት ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው። BSB BSB: If you turn your foot from breaking the Sabbath, from doing as you please on My holy day, if you call the Sabbath a delight, and the LORD’s holy day honorable, if you honor it by not going your own way or seeking your own pleasure or speaking idle words,
14 ULB "በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፤ በምድርም ከፍታዎች ላይ አወጣሃለሁ፤ የአባትህንም የያዕቆብን ርስት አበላሃለሁ፤ የእግዚአብሔር አፍ ተናግሮአልና።" BSB BSB: then you will delight yourself in the LORD, and I will make you ride on the heights of the land and feed you with the heritage of your father Jacob.” For the mouth of the LORD has spoken.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.