1 ULB ከዚህም በኋላ ኢዮብ አፉን ከፍቶ የተወለደበትን ቀን ረገመ። BSB BSB: After this, Job opened his mouth and cursed the day of his birth.
2 ULB እንዲህም አለ፦ BSB BSB: And this is what he said:
3 ULB “ያ የተወለድሁበት ቀን፤ 'ወንድ ልጅም ተፀነሰ' የተባለበት ሌሊት ይጥፋ” BSB BSB: “May the day of my birth perish, and the night it was said, ‘A boy is conceived.’
4 ULB ያ ቀን ጨለማ ይሁን እግዚአብሔርም ከላይ አያስበው፤ የጸሀይ ብርሀንም አያግኝው። BSB BSB: If only that day had turned to darkness! May God above disregard it; may no light shine upon it.
5 ULB ጨለማና የሞት ጥላ የራሳቸው እንደሆነ ይቁጠሩ፤ ዳመናም ይኑርበት፤ ቀኑን የሚያጨልሙ ነገሮች ሁሉ በርግጥ ያስደንግጡት። BSB BSB: May darkness and gloom reclaim it, and a cloud settle over it; may the blackness of the day overwhelm it.
6 ULB ያንን ሌሊት ድቅድቅ ጨለማ ይያዘው፤ በዓመቱ ካሉት ቀኖች ጋር ደስ አይበለው፤ በወራት ውስጥ ገብቶ አይቈጠር። BSB BSB: If only darkness had taken that night away! May it not appear among the days of the year; may it never be entered in any of the months.
7 ULB ያቺ ምሽት መካን ትሁን፤ ወደ እርሷም የደስታ ድምጽ አይግባበት። BSB BSB: Behold, may that night be barren; may no joyful voice come into it.
8 ULB ሌዋታንን እንዴት ማንቃት እንዳለባቸው የሚያውቁ ያንን ቀን ይርገሙት። BSB BSB: May it be cursed by those who curse the day—those prepared to rouse Leviathan.
9 ULB አጥቢያ ኮከቦች ይጨልሙ፤ ያ ቀን ብርሃንን ሲጠባበቅ አያግኝ፥ የንጋትንም ወገግታ አይመልከት፤ BSB BSB: May its morning stars grow dark; may it wait in vain for daylight; may it not see the breaking of dawn.
10 ULB ምክንያቱም የእናቴን ማኅፀን ደጅ አልዘጋምና፥ መከራንም ከዓይኔ አልሰወረምና። BSB BSB: For that night did not shut the doors of the womb to hide the sorrow from my eyes.
11 ULB ከማኅፀን ስወጣ ስለ ምን አልሞትሁም? እናቴ ስትወልደኝስ ስለምን አልጠፋሁም? BSB BSB: Why did I not perish at birth; why did I not die as I came from the womb?
12 ULB ጕልበቶቿ ስለ ምን ተቀበሉኝ? ጡቶቿስ እንድጠባ ስለ ምን ተቀበሉኝ? BSB BSB: Why were there knees to receive me, and breasts that I should be nursed?
13 ULB ይሄኔ በጸጥታ በተጋደምሁ፤ BSB BSB: For now I would be lying down in peace; I would be asleep and at rest
14 ULB አሁን ፈርሶ ያለውን መቃብር ለራሳቸው ከገነቡት የምድር ነገሥታትና አማካሪዎች ጋር፥ አንቀላፍቼም ባረፍሁ ነበር፤ BSB BSB: with kings and counselors of the earth, who built for themselves cities now in ruins,
15 ULB ወይም ባንድ ወቅት ቤታቸውን በብር ከሞሉ ወርቅም ከነበራቸው መኳንንት ጋር በተጋደምሁ ነበር፥ BSB BSB: or with princes who had gold, who filled their houses with silver.
16 ULB ወይም ያለጊዜያቸው እንደተወለዱ፥ ብርሃንንም አይተው እንደማያውቁ ሕፃናት በሆንሁ ነበር። BSB BSB: Or why was I not hidden like a stillborn child, like an infant who never sees daylight?
17 ULB በዚያ ክፉዎች ረብሻቸውን ያቆማሉ፤ የደከሙትም በዚያ ያርፋሉ። BSB BSB: There the wicked cease from raging, and there the weary find rest.
18 ULB በዚያ እስረኞች አርፈው በአንድነት ይቀመጣሉ፤ የአስጨናቂውን ጠባቂ ድምፅ አይሰሙም። BSB BSB: The captives enjoy their ease; they do not hear the voice of the oppressor.
19 ULB ታናናሽና ታላላቅ ሰዎች በዚያ አሉ፤ በዚያም ባሪያ ከጌታው ነጻ ወጥቶአል። BSB BSB: Both small and great are there, and the slave is freed from his master.
20 ULB በመከራ ላለ ሰው ብርሃን፤ ነፍሳቸው መራራ ለሆነችባቸውስ ህይወት፤ BSB BSB: Why is light given to the miserable, and life to the bitter of soul,
21 ULB የተሰወረን ሀብት ከሚፈልጉ ይልቅ ሞትን እየተመኙ ላልመጣላቸው ህይወት ለምን ተሰጠ? BSB BSB: who long for death that does not come, and search for it like hidden treasure,
22 ULB መቀበሪያቸውን ባገኙ ጊዜ እጅግ ደስ ለሚላቸው፥ ሐሤትንም ለሚያደርጉ ሕይወት ለምን ተሰጠ? BSB BSB: who rejoice and greatly exult when they reach the grave?
23 ULB መንገዱ ለጠፋበት ሰው፥ እግዚአብሔርም አጥር ላጠረበት ሰው ብርሃን ለምን ተሰጠ? BSB BSB: Why is life given to a man whose way is hidden, whom God has hedged in?
24 ULB በመመገብ ምትክ ሲቃዬ ፈጥኖ ይመጣልና፥ መቃተቴም እንደ ውኃ ፈስሶአል። BSB BSB: I sigh when food is put before me, and my groans pour out like water.
25 ULB የፈራሁት ነገር መጥቶብኛልና፥ የደነገጥሁበትም ደርሶብኛል። BSB BSB: For the thing I feared has overtaken me, and what I dreaded has befallen me.
26 ULB በእርጋታና በጸጥታ አልተቀመጥሁም፥ አላረፍሁም ይልቅ መከራና ችግር መጣብኝ። BSB BSB: I am not at ease or quiet; I have no rest, for trouble has come.”
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.