1 ULB ኢዮብም ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰ፥ BSB BSB: Then Job replied to the LORD:
2 ULB "ሁሉን ለማድረግ እንደምትችል፥ ዓላማህ ሊደናቀፍ እንደማይችል አውቃለሁ። BSB BSB: “I know that You can do all things and that no plan of Yours can be thwarted.
3 ULB 'ያለዕውቀት ዕቅዴን የሚያጨልም ይህ ማነው?' ብለህ ጠይቀኸኛል። ስለዚህ የማላውቀውን፥ ያልተረዳሁትን፥ ለማወቅም እጅግ አስቸጋሪ የሆነውን ነገር ተናግሬአለሁ። BSB BSB: You asked, ‘Who is this who conceals My counsel without knowledge?’ Surely I spoke of things I did not understand, things too wonderful for me to know.
4 ULB አንተም፥ 'አሁንም፥ አድምጥ፥ እኔ እናገራለሁ፤ አንዳንድ ነገሮችን እጠይቅሃለሁ፥ አንተም ትነግረኛለህ' አልከኝ። BSB BSB: You said, ‘Listen now, and I will speak. I will question you, and you shall inform Me.’
5 ULB ስለአንተ መስማትን በጆሮዬ ሰምቼ ነበር፥ አሁን ግን ዓይኖቼ አዩህ። BSB BSB: My ears had heard of You, but now my eyes have seen You.
6 ULB ስለዚህ ራሴን እንቃለሁ፤ በአመድና በትቢያ ላይ ተቀምጬ ንስሓ እገባለሁ"። BSB BSB: Therefore I despise myself, and I repent in dust and ashes.”
8 ULB አሁን እንግዲህ ሰባት ወይፈኖችንና ሰባት አውራ በጎችን ለራሳችሁ ይዛችሁ ወደ አገልጋዬ ኢዮብ ሂዱ፤ ለራሳችሁም የሚቃጠል ምስዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ። እኔም እንደ ስንፍናችሁ እንዳላደርግባችሁ አገልጋዬ ኢዮብ ይጸልይላችኋል፤ እኔም ጸሎቱን እቀበላለሁ። አገልጋዬ ኢዮብ እንዳደረገው ስለ እኔ ትክክለኛውን ነገር አልተናገራችሁምና።" BSB BSB: So now, take seven bulls and seven rams, go to My servant Job, and sacrifice a burnt offering for yourselves. Then My servant Job will pray for you, for I will accept his prayer and not deal with you according to your folly. For you have not spoken accurately about Me, as My servant Job has.”
9 ULB ስለዚህ ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው በልዳዶስና ናዕማታዊው ሶፋር እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው ሄደው አደረጉ፤ እግዚአብሔርም ኢዮብን ተቀበለው። BSB BSB: So Eliphaz the Temanite, Bildad the Shuhite, and Zophar the Naamathite went and did as the LORD had told them; and the LORD accepted Job’s prayer.
10 ULB ኢዮብ ስለ ጓደኞቹ በጸለየ ጊዜ እግዚአብሔር እንደገና አበለጸገው። ቀድሞ ከነበረው በላይ እግዚአብሔር ዕጥፍ አድርጎ ሰጠው። BSB BSB: After Job had prayed for his friends, the LORD restored his prosperity and doubled his former possessions.
11 ULB ከዚያም የኢዮብ ወንድሞቹና እህቶቹ ሁሉ፥ ቀድሞ ያውቁት የነበሩትም ሁሉ እርሱ ወደነበረበት መጡ፤ ከእርሱም ጋር ምግብ በሉ። እነርሱም ሐዘኑን ተጋሩት፤ እግዚአብሔር አምጥቶበት ስለነበረው መከራ ሁሉ አጽናኑት። እያንዳንዳቸውም ለኢዮብ ጥሬ ብርና የወርቅ ቀለበት ሰጡት። BSB BSB: All his brothers and sisters and prior acquaintances came and dined with him in his house. They consoled him and comforted him over all the adversity that the LORD had brought upon him. And each one gave him a piece of silver and a gold ring.
12 ULB እግዚአብሔር ከመጀመሪያው ይልቅ የኢዮብን የኋለኛውን ዘመን ባረከለት፤ እርሱም ዐሥራ አራት ሺህ በጎች፥ ስድስት ሺህ ግመሎች፥ አንድ ሺህ ጥማድ በሬዎች፥ አንድ ሺህም ሴት አህዮች ነበሩት። BSB BSB: So the LORD blessed Job’s latter days more than his first. He owned 14,000 sheep, 6,000 camels, 1,000 yoke of oxen, and 1,000 female donkeys.
13 ULB ደግሞም ሰባት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ልጆች ነበሩት። BSB BSB: And he also had seven sons and three daughters.
14 ULB የመጀመሪያ ሴት ልጁን ይሚማ፥ ሁለተኛዋን ቃሥያ፥ ሦስተኛዋን አማልቶያስ ቂራስ ብሎ ሰየማቸው። BSB BSB: He named his first daughter Jemimah, his second Keziah, and his third Keren-happuch.
15 ULB በሀገሩ ሁሉ እንደ ኢዮብ ሴቶች ልጆች የተዋቡ ሴቶች አልተገኙም። አባታቸውም ከወንድሞቻቸው እኩል ርስትን ሰጣቸው። BSB BSB: No women as beautiful as Job’s daughters could be found in all the land, and their father granted them an inheritance among their brothers.
16 ULB ከዚህ በኋላ ኢዮብ 140 አመት ኖረ፤ እርሱም ወንዶች ልጆችን፥ የወንዶች ልጆቹን ወንዶች ልጆች እስከ አራት ትውልድ ድረስ አየ። BSB BSB: After this, Job lived 140 years and saw his children and their children to the fourth generation.
17 ULB ከዚያም ኢዮብ አርጅቶ፥ ዕድሜንም ጠግቦ ሞተ። BSB BSB: And so Job died, old and full of years.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.