1 ULB “እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ ወደ በጎች በረት በበር ሳይሆን፣ በሌላ መንገድ ተንጠላጥሎ የሚገባ እርሱ ሌባና ወንበዴ ነው። BSB BSB: “Truly, truly, I tell you, whoever does not enter the sheepfold by the gate, but climbs in some other way, is a thief and a robber.
2 ULB በበር የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው። BSB BSB: But the one who enters by the gate is the shepherd of the sheep.
3 ULB በር ጠባቂውም ለእርሱ ይከፍትለታል። በጎቹም ድምፁን ይሰማሉ፤ እርሱም የራሱን በጎች በስማቸው ጠርቶ፣ ወደ ውጭ ይመራቸዋል። BSB BSB: The gatekeeper opens the gate for him, and the sheep listen for his voice. He calls his own sheep by name and leads them out.
4 ULB የራሱን ሁሉ ካወጣቸው በኋላ፣ ፊት ፊታቸው ይሄዳል፤ በጎቹም ድምፁን ስለሚያውቁ ይከተሉታል። BSB BSB: When he has brought out all his own, he goes on ahead of them, and his sheep follow him because they know his voice.
5 ULB ባዕድ የሆነውን አይከተሉትም፤ ይልቁንም የባዕዱን ድምፅ ስለማያውቁት ይሸሹታል።” BSB BSB: But they will never follow a stranger; in fact, they will flee from him because they do not recognize his voice.”
6 ULB ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ እነርሱ ግን የነገራቸው ስለ ምን እንደ ሆነ አልገባቸውም። BSB BSB: Jesus spoke to them using this illustration, but they did not understand what He was telling them.
7 ULB ኢየሱስም እንደ ገና እንዲህ አላቸው፤ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ የበጎች በር እኔ ነኝ። BSB BSB: So He said to them again, “Truly, truly, I tell you, I am the gate for the sheep.
8 ULB ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው፤ በጎቹ ግን አላዳመጡአቸውም። BSB BSB: All who came before Me were thieves and robbers, but the sheep did not listen to them.
9 ULB በሩ እኔ ነኝ። ማንም በእኔ በኩል ቢገባ፣ ይድናል፤ ይገባል፣ ይወጣልም፤ መሰማሪያም ያገኛል። BSB BSB: I am the gate. If anyone enters through Me, he will be saved. He will come in and go out and find pasture.
10 ULB ሌባው የሚመጣው ሊሰርቅ፣ ሊገድልና ሊያጠፋ ብቻ ነው። እኔ ግን ሕይወት እንዲኖራቸውና እንዲትረፈረፍላቸው መጥቻለሁ። BSB BSB: The thief comes only to steal and kill and destroy. I have come that they may have life, and have it in all its fullness.
12 ULB እረኛ ያልሆነው ተቀጣሪ በጎቹም የእርሱ ያልሆኑት፣ ቀበሮ መምጣቱን ሲያይ በጎቹን ጥሎ ይሸሻል። ቀበሮም ነጥቆአቸው ይሄዳል፤ ይበታትናቸውማል። BSB BSB: The hired hand is not the shepherd, and the sheep are not his own. When he sees the wolf coming, he abandons the sheep and runs away. Then the wolf pounces on them and scatters the flock.
13 ULB የሚሸሸውም ተቀጣሪ ስለ ሆነና ለበጎቹ ደንታ ስለሌለው ነው። BSB BSB: The man runs away because he is a hired servant and is unconcerned for the sheep.
14 ULB መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ የእኔ የሆኑትን ዐውቃቸዋለው፤ የእኔ የሆኑትም ያውቁኛል። BSB BSB: I am the good shepherd. I know My sheep and My sheep know Me,
15 ULB አብ እንደሚያውቀኝ፤ እኔም አብን ዐውቀዋለው፤ ነፍሴንም ስለ በጎች እሰጣለሁ። BSB BSB: just as the Father knows Me and I know the Father. And I lay down My life for the sheep.
19 ULB ከዚህ አባባል የተነሣም በአይሁድ መካከል እንደ ገና መከፋፈል ተፈጠረ። BSB BSB: Again there was division among the Jews because of Jesus’ message.
20 ULB ብዙዎች፣ “ጋኔን ስላለበት ዐብዶአል፤ ለምን ታዳምጡታላችሁ?” አሉ። BSB BSB: Many of them said, “He is demon-possessed and insane. Why would you listen to Him?”
21 ULB ሌሎችም፣ “ንግግሩ ጋኔን ያለበት ሰው ንግግር አይደለም። ጋኔን ያለበት ሰው የዐይነ ስውርን ዐይን መክፈት ይችላልን?” አሉ። BSB BSB: But others replied, “These are not the words of a man possessed by a demon. Can a demon open the eyes of the blind?”
23 ULB ጊዜው ክረምት ነበረ፤ ኢየሱስም በቤተ መቅደስ በሰሎሞን መተላለፊያ ይመላለስ ነበር። BSB BSB: and Jesus was walking in the temple courts in Solomon’s Colonnade.
24 ULB ከዚያም አይሁድ ወደ እርሱ ተሰብስበው፣ «እስከ መቼ ድረስ ልባችንን ታንጠለጥላለህ? አንተ ክርስቶስ ከሆንህ፣ በግልጽ ንገረን» አሉት። BSB BSB: So the Jews gathered around Him and demanded, “How long will You keep us in suspense? If You are the Christ, tell us plainly.”
25 ULB ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “ነገርኋችሁኮ፤ እናንተ ግን አታምኑም፤ በአባቴ ስም የማደርጋቸው ሥራዎች እነዚህ ስለ እኔ ይመሰክራሉ። BSB BSB: “I already told you,” Jesus replied, “but you did not believe. The works I do in My Father’s name testify on My behalf.
26 ULB እናንተ ግን በጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም። BSB BSB: But because you are not My sheep, you refuse to believe.
28 ULB የዘላለም ሕይወት እሰጣቸዋለው፤ ፈጽሞም አይጠፉም፤ ነጥቆ ከእጄ የሚያወጣቸው ማንም የለም። BSB BSB: I give them eternal life, and they will never perish. No one can snatch them out of My hand.
29 ULB እነርሱን ለእኔ የሰጠ አባቴ ከሌሎች ሁሉ ይበልጣል፤ ስለዚህ ከአብ እጅ ነጥቆ ሊያወጣቸው የሚችል ማንም የለም። BSB BSB: My Father who has given them to Me is greater than all. No one can snatch them out of My Father’s hand.
31 ULB አይሁድ ሊወግሩት እንደ ገና ድንጋይ አነሡ። BSB BSB: At this, the Jews again picked up stones to stone Him.
32 ULB ኢየሱስም መልሶ፣ «ከአብ የሆነ ብዙ መልካም ሥራ አሳይቻችኋለሁ፤ ከእነዚህ ሥራዎች ውስጥ በየትኛው ምክንያት ትወግሩኛላችሁ?” አላቸው። BSB BSB: But Jesus responded, “I have shown you many good works from the Father. For which of these do you stone Me?”
33 ULB አይሁድም መልሰው፣ «የምንወግርህ በየትኛውም መልካም ሥራ ምክንያት አይደለም፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ በምትሰነዝረው የስድብ ቃል ምክንያት ነው፤ አንተ ሰው ሆነህ ሳለህ፣ ራስህን አምላክ እያደረግህ ስለ ሆነ ነው» አሉት። BSB BSB: “We are not stoning You for any good work,” said the Jews, “but for blasphemy, because You, who are a man, make Yourself out to be God.”
34 ULB ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ «በሕጋችሁ፣ ‘አማልክት ናችሁ አልሁ’ ተብሎ አልተጻፈምን? BSB BSB: Jesus replied, “Is it not written in your Law: ‘I have said you are gods’?
35 ULB የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት ናችሁ ካላቸው፣ የመጻሕፍት ቃል አይሻርምና፣ BSB BSB: If he called them gods to whom the word of God came—and the Scripture cannot be broken—
36 ULB እኔ ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ስላልሁ፣ አብ ቀድሶ ወደ ዓለም የላከውን እንዴት የስድብ ቃል ሰነዘረ ትሉታላችሁ? BSB BSB: then what about the One whom the Father sanctified and sent into the world? How then can you accuse Me of blasphemy for stating that I am the Son of God?
37 ULB እኔ የአባቴን ሥራዎች የማላደርግ ከሆንሁ አትመኑኝ። BSB BSB: If I am not doing the works of My Father, then do not believe Me.
38 ULB ነገር ግን የማደርጋቸው ከሆንሁ፣ በእኔ ባታምኑ እንኳ፣ አብ በእኔ እንዳለ፣ እኔም በአብ እንዳለሁ እንድታውቁና እንድትረዱ፣ በሥራዎቹ እመኑ።» BSB BSB: But if I am doing them, even though you do not believe Me, believe the works themselves, so that you may know and understand that the Father is in Me, and I am in the Father.”
39 ULB እነርሱም ኢያሱስን እንደ ገና ለመያዝ ሞከሩ፣ እርሱ ግን ከእጃቸው አምልጦ ሄደ። BSB BSB: At this, they tried again to seize Him, but He escaped their grasp.
40 ULB ኢየሱስ ዮርዳኖስን ተሻግሮ፣ ዮሐንስ በመጀመሪያ ሲያጠምቅበት ወደ ነበረው ቦታ እንደ ገና ሄደ፤ በዚያም ቆየ። BSB BSB: Then Jesus went back across the Jordan to the place where John had first been baptizing, and He stayed there.
41 ULB ብዙ ሰዎች ወደ ኢየሱስ መጡ። እነርሱም፣ «በርግጥ ዮሐንስ ምንም ተአምር አልሠራም፤ ነገር ግን ዮሐንስ ስለዚህ ሰው የተናገረው ሁሉ እውነት ነው» ይሉ ነበር። BSB BSB: Many came to Him and said, “Although John never performed a sign, everything he said about this man was true.”
42 ULB በዚያም ብዙ ሰዎች በኢያሱስ አመኑ። BSB BSB: And many in that place believed in Jesus.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.