3 ULB ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ እንዲገለጥ ነው እንጂ፣ እርሱ ወይም ወላጆቹ ኀጢአት አልሠሩም። BSB BSB: Jesus answered, “Neither this man nor his parents sinned, but this happened so that the works of God would be displayed in him.
4 ULB የላከኝን ሥራ ቀን ሳለ መሥራት ይገባናል። ማንም ሊሠራ የማይችልበት ሌሊት እየመጣ ነው። BSB BSB: While it is daytime, we must do the works of Him who sent Me. Night is coming, when no one can work.
5 ULB በዓለም እስካለሁ፣ የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ።” BSB BSB: While I am in the world, I am the light of the world.”
6 ULB ኢየሱስ ይህን ካለ በኋላ፣ መሬት ላይ እንትፍ ብሎ፣ በምራቁ ጭቃ ሠራ፤ በጭቃውም የሰውየውን ዐይን ቀባ። BSB BSB: When Jesus had said this, He spit on the ground, made some mud, and applied it to the man’s eyes.
8 ULB የሰውየው ጐረቤቶችና ቀድሞ ለማኝ ሆኖ ያዩት ሰዎችም፣ “ይህ ሰው ተቀምጦ ሲለምን የነበረው ሰው አይደለምን?” አሉ። BSB BSB: At this, his neighbors and those who had formerly seen him begging began to ask, “Isn’t this the man who used to sit and beg?”
9 ULB አንዳንዶቹ፣ “እርሱ ነው” አሉ፤ ሌሎችም፣ “ይመስለዋል እንጂ እርሱ አይደለም” አሉ። እርሱ ግን፣ “እኔው ነኝ” አለ። BSB BSB: Some claimed that he was, but others said, “No, he just looks like him.” But the man kept saying, “I am the one.”
10 ULB እነርሱም፣ “ታዲያ፣ ዐይኖችህ እንዴት ተከፈቱልህ?” አሉት። BSB BSB: “How then were your eyes opened?” they asked.
11 ULB እርሱም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ “ኢየሱስ የሚባለው ሰው ጭቃ ሠርቶ ዐይኔን ቀባ፤ ከዚያም፣ ‘ወደ ሰሊሆም ሄደህ ታጠብ’ አለኝ። እኔም ሄጄ ታጠብሁ፤ ዐይኖቼም በሩ።” BSB BSB: He answered, “The man they call Jesus made some mud and anointed my eyes, and He told me to go to Siloam and wash. So I went and washed and received my sight.”
12 ULB እነርሱም፣ “ታዲያ፣ እርሱ የት ነው?” አሉ። እርሱም፣ “እኔ አላውቅም” ብሎ መለሰላቸው። BSB BSB: “Where is He?” they asked. “I do not know,” he answered.
13 ULB እነርሱም ዐይነ ስውር የነበረውን ሰው ወደ ፈሪሳውያን ወሰዱት። BSB BSB: They brought to the Pharisees the man who had been blind.
14 ULB ኢየሱስ ጭቃ ሠርቶ የሰውየውን ዐይን የከፈተው በሰንበት ቀን ነበረ። BSB BSB: Now the day on which Jesus had made the mud and opened his eyes was a Sabbath.
15 ULB ፈሪሳውያንም ዐይኑ እንዴት እንደ ተከፈተለት እንደ ገና ሰውየውን ጠየቁት። እርሱም፣ “ዐይኖቼን ጭቃ ቀባ፤ ታጠብሁና ማየት ቻልሁ” አላቸው። BSB BSB: So the Pharisees also asked him how he had received his sight. The man answered, “He put mud on my eyes, and I washed, and now I can see.”
16 ULB ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ፣ “ይህ ሰው ሰንበትን ስለማያከብር፣ ከእግዚአብሔር አይደለም” አሉ። ሌሎቹም፣ “ኀጢአተኛ የሆነ ሰው እንዴት እንደዚህ ያለ ተአምር ይሠራል?” አሉ። ስለዚህ በመካከላቸው መከፋፈል ተፈጠረ። BSB BSB: Because of this, some of the Pharisees said, “This man is not from God, for He does not keep the Sabbath.” But others said, “How can a sinful man perform such signs?” And there was division among them.
17 ULB እንደ ገናም ዐይነ ስውሩን ሰው፣ “ዐይንህን ስለ ከፈተው ሰው ምን ትላለህ?” አሉት። ዐይነ ስውሩም፣ “ነቢይ ነው” አለ። BSB BSB: So once again they asked the man who had been blind, “What do you say about Him, since it was your eyes He opened?” “He is a prophet,” the man replied.
18 ULB ፈሪሳውያንም ዐይነ ስውር የነበረው ሰው ዐይኖች መከፈታቸውን አሁንም ስላላመኑ፣ ዐይኑ የበራለትን ሰው ወላጆች አስጠሩ። BSB BSB: The Jews still did not believe that the man had been blind and had received his sight until they summoned his parents
19 ULB ወላጆቹንም፣ “ይህ ዐይነ ስውር ሆኖ የተወለደ ነው የምትሉት ሰው ልጃችሁ ነውን? ከሆነስ፣ አሁን እንዴት ማየት ቻለ?” ብለው ጠየቋቸው። BSB BSB: and asked, “Is this your son, the one you say was born blind? So how is it that he can now see?”
20 ULB ወላጆቹም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤ “ይህ ልጃችን መሆኑንና ዐይነ ስውር ሆኖ መወለዱን እናውቃለን። BSB BSB: His parents answered, “We know he is our son, and we know he was born blind.
21 ULB አሁን እንዴት ማየት እንደ ቻለ ግን አናውቅም፤ ዐይኑን የከፈተለት ማን እንደ ሆነም አናውቅም። እርሱን ጠይቁት፤ ጕልማሳ ነው፤ ስለ ራሱ መናገር ይችላል።” BSB BSB: But how he can now see or who opened his eyes, we do not know. Ask him. He is old enough to speak for himself.”
22 ULB ወላጆቹ እንዲህ ያሉት አይሁድን ስለ ፈሩ ነበር። ምክንያቱም አይሁድ፣ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው የሚል ሰው ካገኙ፣ ከምኵራብ ሊያስወግዱት ቀደም ብለው ተስማምተው ነበር። BSB BSB: His parents said this because they were afraid of the Jews. For the Jews had already determined that anyone who confessed Jesus as the Christ would be put out of the synagogue.
23 ULB ወላጆቹ፣ “እርሱ ጕልማሳ ነው፤ ራሱን ጠይቁት” ያሉትም በዚህ ምክንያት ነበር። BSB BSB: That was why his parents said, “He is old enough. Ask him.”
24 ULB ዐይነ ስውር የነበረውን ሰው እንደ ገና አስጠርተው፣ “ለእግዚአብሔር ክብር ስጥ፤ እኛ ይህ ሰው ኀጢአተኛ እንደ ሆነ እናውቃለን” አሉት። BSB BSB: So a second time they called for the man who had been blind and said, “Give glory to God! We know that this man is a sinner.”
25 ULB ሰውየውም፣ “እኔ እርሱ ኀጢአተኛ መሆኑን አላውቅም። ነገር ግን አንድ ነገር ዐውቃለሁ፤ ዐይነ ስውር ነበርሁ፤ አሁን ግን እያየሁ ነው” አላቸው። BSB BSB: He answered, “Whether He is a sinner I do not know. There is one thing I do know: I was blind, but now I see!”
26 ULB እነርሱም፣ “ያደረገልህ ምንድን ነው? ዐይኖችህንስ የከፈተው እንዴት ነው?” አሉት። BSB BSB: “What did He do to you?” they asked. “How did He open your eyes?”
27 ULB እርሱም፣ “አስቀድሜ ነግሬአችሁ ነበር! እናንተ ግን አትሰሙም። እንደ ገና መስማትስ ለምን ፈለጋችሁ? እናንተም የእርሱ ደቀ መዛሙርት ለመሆን ትፈልጋላችሁን?” ብሎ መለሰ። BSB BSB: He replied, “I already told you, and you did not listen. Why do you want to hear it again? Do you also want to become His disciples?”
28 ULB ሰደቡትና እንዲህ አሉ፤ “አንተ የእርሱ ደቀ መዝሙር ነህ፣ እኛ ግን የሙሴ ደቀ መዛሙርት ነን። BSB BSB: Then they heaped insults on him and said, “You are His disciple; we are disciples of Moses.
29 ULB እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ተናገረው እናውቃለን፤ ይህ ሰው ግን ከየት እንደ መጣ አናውቅም።” BSB BSB: We know that God spoke to Moses, but we do not know where this man is from.”
30 ULB ሰውየውም፣ “ይህ ሰው ከየት እንደ መጣ አለማወቃችሁ የሚገርም ነው፤ ይሁን እንጂ፣ ዐይኔን የከፈተው እርሱ ነው። BSB BSB: “That is remarkable indeed!” the man said. “You do not know where He is from, and yet He opened my eyes.
31 ULB እግዚአብሔር ኀጢአተኞችን እንደማይሰማ እናውቃለን፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን የሚያመልክና ፈቃዱን የሚያደርግ ሰው ሁሉ እግዚአብሔር ይሰማዋል። BSB BSB: We know that God does not listen to sinners, but He does listen to the one who worships Him and does His will.
32 ULB ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ፣ ዐይነ ስውር ሆኖ የተወለደን ሰው ዐይን የከፈተ ሰው ከቶ አልተሰማም። BSB BSB: Never before has anyone heard of opening the eyes of a man born blind.
33 ULB ይህ ሰው ከእግዚአብሔር ባይሆን ኖሮ፣ አንድም ነገር ማድረግ ባልቻለ ነበር።” BSB BSB: If this man were not from God, He could do no such thing.”
34 ULB እነርሱም፣ መልሰው “አንተ ሁለንተናህ በኀጢአት የተወለደ፣ አሁን አንተ እኛን ታስተምረናለህን?” አሉት። ከዚያም ከምኵራብ አስወጡት። BSB BSB: They replied, “You were born in utter sin, and you are instructing us?” And they threw him out.
35 ULB ኢየሱስም ሰውየውን ከምኵራብ እንዳስወጡት ሰማ። ሰውየውንም አግኝቶ፣ “በሰው ልጅ ታምናለህን?” አለው። BSB BSB: When Jesus heard that they had thrown him out, He found the man and said, “Do you believe in the Son of Man?”
36 ULB እርሱም፣ “ጌታ ሆይ፣ አምንበት ዘንድ እርሱ ማን ነው?” አለው። BSB BSB: “Who is He, Sir?” he replied. “Tell me so that I may believe in Him.”
37 ULB ኢየሱስም፣ “አይተኸዋል፤ አሁን እንኳ ከአንተ ጋር እየተነጋገረ ያለው እርሱ ነው” አለው። BSB BSB: “You have already seen Him,” Jesus answered. “He is the One speaking with you.”
38 ULB ሰውየውም፣ “ጌታ ሆይ፣ አምናለሁ” አለ። ከዚያም ሰገደለት። BSB BSB: “Lord, I believe,” he said. And he worshiped Jesus.
39 ULB ኢየሱስም፣ “የማያዩ እንዲያዩ፣ የሚያዩም እንዳያዩ፣ ለፍርድ ወደዚህ ዓለም መጣሁ” አለ። BSB BSB: Then Jesus declared, “For judgment I have come into this world, so that the blind may see and those who see may become blind.”
40 ULB ከእነርሱም ጋር ከነበሩት አንዳንድ ፈሪሳውያን ይህን ሰምተው፣ “እኛም ደግሞ ዐይነ ስውራን ነን ወይ?” አሉት። BSB BSB: Some of the Pharisees who were with Him heard this, and they asked Him, “Are we blind too?”
41 ULB ኢየሱስም፣ “ዐይነ ስውራን ብትሆኑማ፣ ኀጢአት ባልሆነባችሁ ነበር። ነገር ግን፣ ‘እናያለን’ ስለምትሉ፣ ኀጢአታችሁ እንዳለ ይኖራል።” BSB BSB: “If you were blind,” Jesus replied, “you would not be guilty of sin. But since you claim you can see, your guilt remains.”
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.