1 ULB ኢየሱስ ወደ ደብረ ዘይት ሄደ። BSB BSB: But Jesus went to the Mount of Olives.
2 ULB ጠዋት በማለዳ ተመልሶ ወደ ቤተ መቅደስ መጣ፤ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ መጡ፤ እርሱም ተቀምጦ አስተማራቸው። BSB BSB: Early in the morning He went back into the temple courts. All the people came to Him, and He sat down to teach them.
3 ULB የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያንም ስታመነዝር የተያዘችን ሴት አምጥተው፤ በመካከላቸው አቆሟት። BSB BSB: The scribes and Pharisees, however, brought to Him a woman caught in adultery. They made her stand before them
4 ULB ከዚያም ኢየሱስን እንዲህ አሉት፤ «መምህር ሆይ፣ ይህች ሴት ስታመነዝር እጅ ከፍንጅ የተያዘች ናት፤ BSB BSB: and said, “Teacher, this woman was caught in the act of adultery.
5 ULB ሙሴ በሕጉ እንዲህ ያሉትን በድንጋይ እንድንወግር አዞናል፤ አንተስ ስለ እርሷ ምን ትላለህ?» BSB BSB: In the Law Moses commanded us to stone such a woman. So what do You say?”
6 ULB ይህን ያሉት እርሱን ወጥመድ ውስጥ ለማስገባትና ለመክሰስ ፈልገው ነው፤ ኢየሱስ ግን ጎንበስ ብሎ በጣቱ መሬት ላይ ጻፈ። BSB BSB: They said this to test Him, in order to have a basis for accusing Him. But Jesus bent down and began to write on the ground with His finger.
7 ULB ጥያቄ ማቅረባቸውን በቀጠሉ ጊዜም፣ ተነሥቶ ቆመና፣ “ከእናንተ መካከል ኃጢአት የሌለበት ሰው በመጀመሪያ ይውገራት” አላቸው። BSB BSB: When they continued to question Him, He straightened up and said to them, “Let him who is without sin among you be the first to cast a stone at her.”
8 ULB ዳግመኛም ጐንበስ ብሎ፣ በጣቱ መሬት ላይ ጻፈ። BSB BSB: And again He bent down and wrote on the ground.
9 ULB ይህንም በሰሙ ጊዜ፣ ከታላቅ ጀምረው አንድ ባንድ ወጥተው ሄዱ። በመጨረሻ ኢየሱስ በመካከላቸው ቆማ ከነበረችው ሴት ጋር ለብቻው ቀረ። BSB BSB: When they heard this, they began to go away one by one, beginning with the older ones, until only Jesus was left, with the woman standing there.
10 ULB ኢየሱስ ተነሥቶ በመቆም፣ “አንቺ ሴት፤ የከሰሱሽ ሰዎች የት ናቸው? አንድም የፈረደብሽ የለም?” አላት። BSB BSB: Then Jesus straightened up and asked her, “Woman, where are your accusers? Has no one condemned you?”
11 ULB እርሷም፣ “ጌታ ሆይ፣ አንድም የለም” አለች። ኢየሱስ፣ “እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁን በኋላ ግን ደግመሽ ኀጢአት አትሥሪ” አላት። BSB BSB: “No one, Lord,” she answered. “Then neither do I condemn you,” Jesus declared. “Now go and sin no more.”
12 ULB ደግሞም ኢየሱስ ሕዝቡን፣ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ ቢኖር የሕይወት ብርሃን ያገኛል እንጂ፣ በጨለማ አይመላለስም” አላቸው። BSB BSB: Once again, Jesus spoke to the people and said, “I am the light of the world. Whoever follows Me will never walk in the darkness, but will have the light of life.”
13 ULB ፈሪሳውያንም፣ “አንተው ስለ ራስህ ስለምትመሰክር፤ ምስክርነትህ እውነት አይደለም” አሉት። BSB BSB: So the Pharisees said to Him, “You are testifying about Yourself; Your testimony is not valid.”
14 ULB ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር እንኳ ምስክርነቴ እውነት ነው። ከየት እንደ መጣሁ፣ ወዴትም እንደምሄድ ዐውቃለሁ፤ እናንተ ግን እኔ ከየት እንደ መጣሁ ወይም ወዴት እንደምሄድ አታውቁም። BSB BSB: Jesus replied, “Even if I testify about Myself, My testimony is valid, because I know where I came from and where I am going. But you do not know where I came from or where I am going.
15 ULB እናንተ በሥጋዊ ዐይን ትፈርዳላችሁ፤ እኔ በማንም አልፈርድም። BSB BSB: You judge according to the flesh; I judge no one.
16 ULB ብፈርድም እንኳ፣ ብቻዬን አይደለሁም፤ ከላከኝ አብ ጋር ስለ ሆንሁ፣ ፍርዴ እውነት ነው። BSB BSB: But even if I do judge, My judgment is true, because I am not alone; I am with the Father who sent Me.
17 ULB አዎን፤ በሕጋችሁ የሁለት ሰዎች ምስክርነት እውነት እንደ ሆነ ተጽፎአል። BSB BSB: Even in your own Law it is written that the testimony of two men is valid.
18 ULB እኔ ስለ ራሴ እመሰክራለሁ፤ የላከኝም አብ ስለ እኔ ይመሰክራል።” BSB BSB: I am One who testifies about Myself, and the Father, who sent Me, also testifies about Me.”
19 ULB እነርሱም፣ “አባትህ የት ነው ያለው?” አሉት። ኢየሱስም፣ “እናንተ እኔንም ሆነ አባቴን አታውቁንም፤ እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም ባወቃችሁት ነበር” አላቸው። BSB BSB: “Where is Your Father?” they asked Him. “You do not know Me or My Father,” Jesus answered. “If you knew Me, you would know My Father as well.”
20 ULB ይህንም የተናገረው በቤተ መቅደሱ ግምጃ ቤት አጠገብ ሆኖ ሲያስተምር ነበር፤ ሆኖም ሰዓቱ ገና ስላልደረሰ፣ ማንም አልያዘውም። BSB BSB: He spoke these words while teaching in the temple courts, near the treasury. Yet no one seized Him, because His hour had not yet come.
21 ULB ደግሞም፣ “እኔ ተለይቻችሁ እሄዳለሁ፤ እናንተም ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ። እኔ ወደምሄድበት መምጣት አትችሉም” አላቸው። BSB BSB: Again He said to them, “I am going away, and you will look for Me, but you will die in your sin. Where I am going, you cannot come.”
22 ULB አይሁድም፣ “ይህ 'እኔ ወደምሄድበት መምጣት አትችሉም' የሚለው ራሱን ሊገድል ዐስቦ ይሆን?” አሉ። BSB BSB: So the Jews began to ask, “Will He kill Himself, since He says, ‘Where I am going, you cannot come’?”
23 ULB ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ ከታች ናችሁ፤ እኔ ግን ከላይ ነኝ። እናንተ ከዚህ ዓለም ናችሁ፤ እኔ ግን ከዚህ ዓለም አይደለሁም። BSB BSB: Then He told them, “You are from below; I am from above. You are of this world; I am not of this world.
24 ULB በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ ያልኋችሁ ለዚህ ነው። ምክንያቱም እኔ ነኝ ስላችሁ ካላመናችሁ፣ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ።” BSB BSB: That is why I told you that you would die in your sins. For unless you believe that I am He, you will die in your sins.”
25 ULB እነርሱም፣ “ለመሆኑ፣ አንተ ማን ነህ?” አሉት። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤”ከመጀመሪያው እንደ ነገርኋችሁ ነኝ። BSB BSB: “Who are You?” they asked. “Just what I have been telling you from the beginning,” Jesus replied.
26 ULB ብዙ የምናገረውና ስለ እናንተም የምፈርደው አለኝ። ይሁን እንጂ የላከኝ እርሱ እውነተኛ ነው፤ እኔም ከእርሱ የሰማሁትን፣ ያንኑ ለዓለም እናገራለሁ።” BSB BSB: “I have much to say about you and much to judge. But the One who sent Me is truthful, and what I have heard from Him, I tell the world.”
27 ULB እነርሱ ግን ስለ አብ እየነገራቸው እንደ ነበር አልተረዱም። BSB BSB: They did not understand that He was telling them about the Father.
28 ULB ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “የሰውን ልጅ ወደ ላይ ከፍ ስታደርጉት፣ በዚያን ጊዜ እኔው እንደ ሆንሁና ከራሴ አንድም ነገር እንደማላደርግ ታውቃላችሁ። አብ እንዳስተማረኝ ይህን እናገራለሁ። BSB BSB: So Jesus said, “When you have lifted up the Son of Man, then you will know that I am He, and that I do nothing on My own, but speak exactly what the Father has taught Me.
29 ULB የላከኝ እርሱ ከእኔ ጋር ነው፤ ብቻዬንም አልተወኝም፤ እኔ ሁልጊዜ እርሱን ደስ የሚያሰኘውን ነገር አደርጋለሁና።” BSB BSB: He who sent Me is with Me. He has not left Me alone, because I always do what pleases Him.”
30 ULB ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች በተናገረ ጊዜ ብዙ ሰዎች በእርሱ አመኑ። BSB BSB: As Jesus spoke these things, many believed in Him.
31 ULB ኢየሱስ በእርሱ ያመኑትን አይሁድ፣ “እናንተ በቃሌ ብትኖሩ፣ በርግጥ ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤ BSB BSB: So He said to the Jews who had believed Him, “If you continue in My word, you are truly My disciples.
32 ULB እውነትን ታውቃላችሁ፤ እውነትም ነጻ ያወጣችኋል” አላቸው። BSB BSB: Then you will know the truth, and the truth will set you free.”
33 ULB እነርሱም፣ “እኛ የአብርሃም ዘሮች ነን፤ የማንም ባሪያ ሆነን አናውቅም፤ ታዲያ እንዴት ‘ነጻ ትወጣላችሁ’ ትለናለህ?” አሉት። BSB BSB: “We are Abraham’s descendants,” they answered. “We have never been slaves to anyone. How can You say we will be set free?”
34 ULB ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ ኃጢአት የሚሠራ ሁሉ የኃጢአት ባሪያ ነው። BSB BSB: Jesus replied, “Truly, truly, I tell you, everyone who sins is a slave to sin.
35 ULB ባሪያ ለዘለቄታ በቤት አይኖርም፤ ልጅ ግን ለዘለቄታ ይኖራል። BSB BSB: A slave does not remain in the house forever, but a son remains forever.
36 ULB ስለዚህ ልጁ ነጻ ካወጣችሁ፣ በርግጥ ነጻ ትወጣላችሁ። BSB BSB: So if the Son sets you free, you will be free indeed.
37 ULB የአብርሃም ዘር መሆናችሁን ዐውቃለሁ፤ ቃሌን ስላልተቀበላችሁ፣ ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ። BSB BSB: I know you are Abraham’s descendants, but you are trying to kill Me because My word has no place within you.
38 ULB አባቴ ጋ ያየሁትን እናገራለሁ፤ እናንተም ደግሞ ከአባታችሁ የሰማችሁትን ታደርጋላችሁ።” BSB BSB: I speak of what I have seen in the presence of the Father, and you do what you have heard from your father.”
39 ULB እነርሱም መልሰው፣ “አባታችንስ አብርሃም ነው” አሉት። ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “የአብርሃም ልጆችስ ብትሆኑ ኖሮ፣ የአብርሃምን ሥራ በሠራችሁ ነበር። BSB BSB: “Abraham is our father,” they replied. “If you were children of Abraham,” said Jesus, “you would do the works of Abraham.
40 ULB አሁን ግን ከእግዚአብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው ለመግደል ትፈልጋላችሁ። አብርሃምኮ ይህን አላደረገም። BSB BSB: But now you are trying to kill Me, a man who has told you the truth that I heard from God. Abraham never did such a thing.
41 ULB እናንተ ግን የአባታችሁን ሥራ ትሠራላችሁ።” እነርሱም፣ “እኛ በዝሙት የተወለድን አይደለንም፤ አንድ አባት እግዚአብሔር አለን” አሉት። BSB BSB: You are doing the works of your father.” “We are not illegitimate children,” they declared. “Our only Father is God Himself.”
42 ULB ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እግዚአብሔር አባታችሁ ቢሆን ኖሮ፣ እኔ ከእግዚአብሔር ወጥቼ ስለ መጣሁ፣ በወደዳችሁኝ ነበር፤ በራሴም ፈቃድ አልመጣሁም፤ ነገር ግን እርሱ ላከኝ። BSB BSB: Jesus said to them, “If God were your Father, you would love Me, for I have come here from God. I have not come on My own, but He sent Me.
43 ULB ቃሌን የማትረዱት ለምንድን ነው? ምክንያቱም ቃሌን መስማት ስለማትችሉ ነው። BSB BSB: Why do you not understand what I am saying? It is because you are unable to accept My message.
45 ULB እኔ ግን እውነትን ስለምናገር አታምኑኝም። BSB BSB: But because I speak the truth, you do not believe Me!
46 ULB ከእናንተ ስለ ኃጢአት የሚወቅሰኝ ሰው ማን ነው? እውነትን የምናገር ከሆነስ፣ ታዲያ ለምን አታምኑኝም? BSB BSB: Which of you can prove Me guilty of sin? If I speak the truth, why do you not believe Me?
47 ULB ከእግዚአብሔር ስላልሆናችሁ፣ ቃሉን አትሰሙም።” BSB BSB: Whoever belongs to God hears the words of God. The reason you do not hear is that you do not belong to God.”
48 ULB አይሁድም፣ “እንግዲህ ጋኔን ያደረብህ ሳምራዊ ነህ በማለታችን እውነት አልተናገርንምን?” በማለት መለሱለት። BSB BSB: The Jews answered Him, “Are we not right to say that You are a Samaritan and You have a demon?”
49 ULB ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ “እኔ ጋኔን የለብኝም፤ እኔ አባቴን አከብረዋለሁ እንጂ፣ እናንተ ግን ታዋርዱኛላችሁ። BSB BSB: “I do not have a demon,” Jesus replied, “but I honor My Father, and you dishonor Me.
50 ULB እኔ የራሴን ክብር አልሻም፤ የሚሻና የሚፈርድ አንድ አለ። BSB BSB: I do not seek My own glory. There is One who seeks it, and He is the Judge.
51 ULB እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚጠብቅ ማንም ቢኖር፣ እርሱ ሞትን በፍጹም አያይም።” BSB BSB: Truly, truly, I tell you, if anyone keeps My word, he will never see death.”
52 ULB አይሁድም፣ “አሁን ጋኔን እንዳለብህ ዐወቅን። አብርሃምም ነቢያትም ሞተዋል፤ አንተ ግን 'ማንም ቃሌን ቢጠብቅ ሞትን አይቀምስም' ትላለህ። BSB BSB: “Now we know that You have a demon!” declared the Jews. “Abraham died, and so did the prophets, yet You say that anyone who keeps Your word will never taste death.
53 ULB አንተ ከሞተው ከአባታችን፣ ከአብርሃም ትበልጣለህን? ነቢያትም ሞተዋል። ለመሆኑ፣ አንተ ማን ነኝ ልትል ነው?” አሉት። BSB BSB: Are You greater than our father Abraham? He died, as did the prophets. Who do You claim to be?”
54 ULB ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እኔ ራሴን ባከብር፣ ክብሬ ከንቱ ነው፤ እኔን የሚያከብረኝ እናንተ አምላካችን ነው የምትሉት አባቴ ነው። BSB BSB: Jesus answered, “If I glorify Myself, My glory means nothing. The One who glorifies Me is My Father, of whom you say, ‘He is our God.’
55 ULB እናንተ እርሱን አላወቃችሁትም፤ እኔ ግን ዐውቀዋለሁ። እኔ ‘አላውቀውም’ ብል እንደ እናንተው ሐሰተኛ እሆናለሁ። ነገር ግን እኔ ዐውቀዋለሁ፤ ቃሉንም እጠብቃለሁ። BSB BSB: You do not know Him, but I know Him. If I said I did not know Him, I would be a liar like you. But I do know Him, and I keep His word.
57 ULB አይሁድም፣ “ገና ዐምሳ ዓመት ያልሞላህ፣ አንተ አብርሃምን አይተሃልን?” አሉት። BSB BSB: Then the Jews said to Him, “You are not yet fifty years old, and You have seen Abraham?”
59 ULB እነርሱም፣ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ራሱን ሰውሮ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ሄደ። BSB BSB: At this, they picked up stones to throw at Him. But Jesus was hidden and went out of the temple area.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.