1 ULB በዚህ ጊዜ ኢየሱስ ከፋሲካ በዓል በፊት ከዚህ ዓለም ተለይቶ ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ ስላወቀ፣ ቀድሞውኑ የሚወዳቸውን በዓለም ይኖሩ የነበሩትን የራሱን ወገኖች እስከ መጨረሻው ወደዳቸው። BSB BSB: It was now just before the Passover Feast, and Jesus knew that His hour had come to leave this world and return to the Father. Having loved His own who were in the world, He loved them to the very end.
2 ULB ዲያብሎስም ኢየሱስን አሳልፎ እንዲሰጥ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ ይሁዳ ልብ ክፉ ዐሳብ አስገባ። BSB BSB: The evening meal was underway, and the devil had already put into the heart of Judas, the son of Simon Iscariot, to betray Jesus.
3 ULB ኢየሱስ አብ ሁሉን ነገር በእጁ አሳልፎ እንደ ሰጠው፣ ከእግዚአብሔር እንደ መጣ ወደ እግዚአብሔርም ተመልሶ እንደሚሄድ ዐወቀ፤ BSB BSB: Jesus knew that the Father had delivered all things into His hands, and that He had come from God and was returning to God.
4 ULB ከእራት ላይ ተነሣ፤ መጎናጸፊያውንም አስቀመጠ፤ ከዚያም ፎጣ ወስዶ ወገቡ ላይ ከታጠቀ በኋላ BSB BSB: So He got up from the supper, laid aside His outer garments, and wrapped a towel around His waist.
5 ULB በሳሕን ውስጥ ውሃ ጨምሮ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠብና በያዘውም ፎጣ ማበስ ጀመረ። BSB BSB: After that, He poured water into a basin and began to wash the disciples’ feet and dry them with the towel that was around Him.
6 ULB ወደ ስምዖን ጴጥሮስ መጣ፤ ጴጥሮስም «ጌታ ሆይ የእኔን እግር ልታጥብ ነውን?» አለው BSB BSB: He came to Simon Peter, who asked Him, “Lord, are You going to wash my feet?”
7 ULB ኢየሱስም «የማደርገውን አሁን አይገባህም፤ወደፊት ግን ትረዳዋለህ» በማለት መለሰለት BSB BSB: Jesus replied, “You do not realize now what I am doing, but later you will understand.”
8 ULB ጴጥሮስም «ፈጽሞ የእኔን እግር አታጥብም» አለው ኢየሱስም «እግርህን ካላጠብሁህ ከእኔ ጋር ዕድል ፈንታ አይኖርህም» ሲል መለሰለት BSB BSB: “Never shall You wash my feet!” Peter told Him. Jesus answered, “Unless I wash you, you have no part with Me.”
9 ULB ስምዖን ጴጥሮስም «ጌታ ሆይ እንግዲያስ እግሬን ብቻ ሳይሆን እጄንና ራሴንም እጠበኝ» አለው BSB BSB: “Then, Lord,” Simon Peter replied, “not only my feet, but my hands and my head as well!”
10 ULB ኢየሱስም «ገላውን የታጠበ እግሩን ብቻ ከመታጠብ በስተቀር ሌላ ሰውነቱ ንጹህ ነው፤ እናንተ ንጹሓን ናችሁ ነገር ግን ይህን ስል ሁላችሁንም ማለቴ አይደለም» BSB BSB: Jesus told him, “Whoever has already bathed needs only to wash his feet, and he will be completely clean. And you are clean, though not all of you.”
11 ULB ኢየሱስ «ሁላችሁም ንጹህ አይደላችሁም» ያለው ኣሳልፎ የሚሰጠው ማን እንደሆነ ያውቅ ስለነበረ ነው BSB BSB: For He knew who would betray Him. That is why He said, “Not all of you are clean.”
12 ULB ኢየሱስ እግራቸውን አጥቦ ከጨረሰ በኋላ ልብሱን ለብሶ ተቀመጠ፤ እነርሱንም፣ «ያደረግሁላችሁን ልብ ብላችኋል? BSB BSB: When Jesus had washed their feet and put on His outer garments, He reclined with them again and asked, “Do you know what I have done for you?
13 ULB 'መምህር' እና 'ጌታ' ትሉኛላችሁ። እንደዚያም ስለሆንሁ አባባላችሁ ትክክል ነው። BSB BSB: You call Me Teacher and Lord, and rightly so, because I am.
14 ULB እኔ ጌታና መምህር ሆኜ እግራችሁን ካጠብሁ፣ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ልትተጣጠቡ ይገባል። BSB BSB: So if I, your Lord and Teacher, have washed your feet, you also should wash one another’s feet.
15 ULB እኔ እንዳደረግሁላችሁ እንደዚያው ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ትቼላችኋለሁ። BSB BSB: I have set you an example so that you should do as I have done for you.
16 ULB እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ አገልጋይ ከጌታው አይበልጥም ወይም የተላከ ሰው ከላኪው አይበልጥም። BSB BSB: Truly, truly, I tell you, no servant is greater than his master, nor is a messenger greater than the one who sent him.
17 ULB እነዚህን ነገሮች ብታውቁና ብታደርጓቸው የተባረካችሁ ናችሁ። BSB BSB: If you know these things, you will be blessed if you do them.
18 ULB የምናገረው ሁላችሁን በሚመለከት አይደለም፤ የመረጥኋቸውን አውቃለሁና፣ ነገር ግን እንደዚህ የምናገረው እንጀራዬን የበላ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣ የሚለው የመጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም ነው። BSB BSB: I am not speaking about all of you; I know whom I have chosen. But this is to fulfill the Scripture: ‘The one who shares My bread has lifted up his heel against Me.’
19 ULB ከመሆኑ በፊት አስቀድሜ የምነግራችሁ በሚፈጸምበት ጊዜ እኔ እንደሆንሁ እንድታምኑ ነው። BSB BSB: I am telling you now before it happens, so that when it comes to pass, you will believe that I am He.
20 ULB እውነት እውነት እላችኋለሁ እኔን የሚቀበል የላክሁትን ይቀበላል፤ እኔን የተቀበለ ደግሞ የላክኝን ይቀባላል» BSB BSB: Truly, truly, I tell you, whoever receives the one I send receives Me, and whoever receives Me receives the One who sent Me.”
21 ULB ኢየሱስ ይህን በሚናገርበት ጊዜ በመንፈሱ ታወከ፤ «እውነት እውነት እላችኋለሁ ከእናንተ መካከል አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል» ብሎ በግልጽ ነገራቸው BSB BSB: After Jesus had said this, He became troubled in spirit and testified, “Truly, truly, I tell you, one of you will betray Me.”
22 ULB ደቀ መዛሙርቱም ስለማን እየተናገረ እንደሆነ ስላልገባቸው እርስ በርስ ተያዩ። BSB BSB: The disciples looked at one another, perplexed as to which of them He meant.
23 ULB ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የሆነው ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር ወደ ደረቱ ተጠግቶ ተቀምጦ ነበር። BSB BSB: One of His disciples, the one whom Jesus loved, was reclining at His side.
24 ULB ስለዚህ ስምዖን ጴጥሮስ ወደዚህ ደቀ መዝሙር ጠጋ ብሎ «ንገረን ለመሆኑ ስለ ማን ነው እየተናገረ ያለው?» በማለት ጠየቀው። BSB BSB: So Simon Peter motioned to him to ask Jesus which one He was talking about.
25 ULB ወደ ኢየሱስ ደረት ተጠግቶ የተቀመጠው ደቀ መዝሙርም፣ «ጌታ ሆይ፣ ይህ የምትለው ሰው ማን ነው?» ብሎ ጠየቀው። BSB BSB: Leaning back against Jesus, he asked, “Lord, who is it?”
26 ULB ከዚያም ኢየሱስ፣ «ይህን ቍራሽ እንጀራ ከወጭቱ አጥቅሼ የምሰጠው ያ ሰው እርሱ ነው» በማለት መለሰለት። ስለዚህ ቍራሹን እንጀራ አጥቅሶ ለአስቆሮቱ ይሁዳ ሰጠው። BSB BSB: Jesus answered, “It is the one to whom I give this morsel after I have dipped it.” Then He dipped the morsel and gave it to Judas son of Simon Iscariot.
27 ULB ቍራሹንም እንጀራ ከተቀበለ በኋላ፣ ሰይጣን ገባበት። ከዚያም ኢየሱስ፣ «ለማድረግ ያሰብኸውን ፈጥነህ አድርግ» አለው። BSB BSB: And when Judas had taken the morsel, Satan entered into him. Then Jesus said to Judas, “What you are about to do, do quickly.”
28 ULB ኢየሱስ ለይሁዳ እንደዚያ ለምን እንዳለው በማዕድ ላይ ከተቀመጡት ማንም ያወቀ የለም። BSB BSB: But no one at the table knew why Jesus had said this to him.
29 ULB አንዳንዶቹ ይሁዳ ገንዝብ ያዥ ስለ ነበር፣ ኢየሱስ «ለበዓሉ የሚያስፈልጉንን ነገሮች ግዛ» ወይም ለድኾች ገንዘብ ስጥ ብሎ ነግሮታል ብለው ዐሰቡ። BSB BSB: Since Judas kept the money bag, some thought that Jesus was telling him to buy what was needed for the feast, or to give something to the poor.
30 ULB ይሁዳ ቍራሹን እንጀራ ከተቀበለ በኋላ፣ ፈጥኖ ወጣ ምሽትም ነበረ። BSB BSB: As soon as he had received the morsel, Judas went out into the night.
31 ULB ይሁዳ በሄደ ጊዜ፣ ኢየሱስ እንዲህ በማለት ተናገረ፤ «አሁን የሰው ልጅ ከብሯል፣ እግዚአብሔርም በእርሱ ከብሯል። BSB BSB: When Judas had gone out, Jesus said, “Now the Son of Man is glorified, and God is glorified in Him.
32 ULB እግዚአብሔር በራሱ ያከብረዋል፣ ደግሞም ፈጥኖ ያከብረዋል። BSB BSB: If God is glorified in Him, God will also glorify the Son in Himself—and will glorify Him at once.
33 ULB ልጆች ሆይ፣ ከእንግዲህ ከእናንተ ጋር የምቆየው ለጥቂት ጊዜ ነው። እናንተ ትፈልጉኛላችሁ፣ ይሁን እንጂ፣ ለአይሁድ፣ 'እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም' እንዳልኋቸው፣ ለእናንተም የምናገረው እንደዚያ ነው። BSB BSB: Little children, I am with you only a little while longer. You will look for Me, and as I said to the Jews, so now I say to you: ‘Where I am going, you cannot come.’
35 ULB እርስ በርሳችሁም ብትዋደዱ የእኔ ደቀ መዛሙርት እንደ ሆናችሁ ሰዎች በዚህ ያውቃሉ።» BSB BSB: By this everyone will know that you are My disciples, if you love one another.”
36 ULB ስምዖን ጴጥሮስ «ጌታ ሆይ፣ ወዴት ልትሄድ ነው?» ሲል ጠየቀው። ኢየሱስ፣ «ወደምሄድበት አሁን ልትከተለኝ አትችልም፣ በኋላ ግን ትከተለኛለህ» በማለት መለሰለት። BSB BSB: “Lord, where are You going?” Simon Peter asked. Jesus answered, “Where I am going, you cannot follow Me now, but you will follow later.”
37 ULB ጴጥሮስ፣ «ጌታ ሆይ፣ አሁን ልከተልህ የማልችለው ለምንድን ነው? ስላንተ ሕይወቴን እንኳ አሳልፌ ለመስጠት ቈርጫለሁ» አለው። BSB BSB: “Lord,” said Peter, “why can’t I follow You now? I will lay down my life for You.”
38 ULB ኢየሱስ፣ «ስለ እኔ ሕይወትህን አሳልፈህ ትሰጣለህን? እውነት፣ እውነት እልሃለሁ፣ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ» ብሎ መለሰለት። BSB BSB: “Will you lay down your life for Me?” Jesus replied. “Truly, truly, I tell you, before the rooster crows, you will deny Me three times.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.