1 ULB ከዚያም ጲላጦስ ኢየሱስን ወስዶ አስገረፈው። BSB BSB: Then Pilate took Jesus and had Him flogged.
2 ULB ወታደሮቹ የእሾኽ አክሊል ጐንጕነው በኢየሱስ ራስ ላይ አደረጉ። ሐምራዊ ልብስም አለበሱት። BSB BSB: The soldiers twisted together a crown of thorns, set it on His head, and dressed Him in a purple robe.
3 ULB ወደ እርሱ መጥተው፣ «የተከበሩ የአይሁድ ንጉሥ ሆይ!» አሉ በጥፊም መቱት። BSB BSB: And they went up to Him again and again, saying, “Hail, King of the Jews!” and slapping Him in the face.
4 ULB ከዚያም ጲላጦስ እንደ ገና ወደ ወጥቶ ሕዝቡን፣ «ምንም ጥፋት እንዳላገኘሁበት እንድታውቁ እነሆ፣ ሰውየውን ወደ ውጭ አወጣላችኋለሁ» አላቸው። BSB BSB: Once again Pilate came out and said to the Jews, “Look, I am bringing Him out to you to let you know that I find no basis for a charge against Him.”
5 ULB ስለዚህ ኢየሱስ የእሾኽ አክሊል ደፍቶና ሐምራዊ ልብስ ለብሶ ወደ ውጭ ወጣ። ጲላጦስም፣ «እነሆ፣ ሰውየው!» አላቸው። BSB BSB: When Jesus came out wearing the crown of thorns and the purple robe, Pilate said to them, “Here is the man!”
6 ULB የካህናት አለቆችና ጠባቂዎቹ ኢየሱስን ባዩ ጊዜ፣ «ስቀለው፣ ስቀለው» እያሉ ጮኹ። ጲላጦስ፣ «እናንተ ወስዳችሁ ስቀሉት፤ እኔ ምንም ወንጀል አላገኘሁበትም» አላቸው። BSB BSB: As soon as the chief priests and officers saw Him, they shouted, “Crucify Him! Crucify Him!” “You take Him and crucify Him,” Pilate replied, “for I find no basis for a charge against Him.”
7 ULB አይሁድ፣ «እኛ ሕግ አለን፣ በሕጋችን መሠረትም ይህ ሰው ራሱን የእግዚአብሔር ልጅ አድርጓልና ሞት ይገባዋል» ብለው መለሱ። BSB BSB: “We have a law,” answered the Jews, “and according to that law He must die, because He declared Himself to be the Son of God.”
8 ULB ጲላጦስ ይህን ሲሰማ የበለጠ ደነገጠ፤ BSB BSB: When Pilate heard this statement, he was even more afraid,
9 ULB ወደ ግቢውም ተመልሶ ኢየሱስን፣ «ከየት ነው የመጣኸው?» ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስ ግን ምንም አልመለሰለትም። BSB BSB: and he went back into the Praetorium. “Where are You from?” he asked. But Jesus gave no answer.
10 ULB ጲላጦስም ኢየሱስን፣ «አናግረኝ እንጂ፤ ልፈታህም ሆነ ልሰቅልህ ሥልጣን እንዳለኝ አታውቅም እንዴ?» አለው። BSB BSB: So Pilate said to Him, “Do You refuse to speak to me? Do You not know that I have authority to release You and authority to crucify You?”
11 ULB ኢየሱስ፣ «ከላይ ባይሰጥህ ኖሮ በእኔ ላይ ምንም ሥልጣን ባልኖረህ ነበር። ስለዚህም ለአንተ አሳልፎ የሰጠኝ ኀጢአቱ የከፋ ነው» አለው። BSB BSB: Jesus answered, “You would have no authority over Me if it were not given to you from above. Therefore the one who handed Me over to you is guilty of greater sin.”
12 ULB ከዚህ መልሱ የተነሣ ጲላጦስ ሊፈታው ፈለገ፣ ነገር ግን አይሁድ፣ «ራሱን ንጉሥ ብሎ የሚጠራ ቄሣርን የሚቃወም ስለ ሆነ፣ ይህን ሰው ብትለቀው አንተ የቄሣር ወዳጅ አይደለህም» እያሉ ይጮኹ ነበር። BSB BSB: From then on, Pilate tried to release Him, but the Jews kept shouting, “If you release this man, you are no friend of Caesar. Anyone who declares himself a king is defying Caesar.”
13 ULB ጲላጦስ እነዚህን ቃላት በሰማ ጊዜ ኢየሱስን ወደ ውጭ አውጥቶ የድንጋይ ንጣፍ፣ በዕብራይስጥ ግን ገበታ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ በፍርድ ወንበር ላይ ተቀመጠ። BSB BSB: When Pilate heard these words, he brought Jesus out and sat on the judgment seat at a place called the Stone Pavement, which in Hebrew is Gabbatha.
14 ULB ቀኑ ለፋሲካ በዓል ዝግጅት የሚደረግበትና ሰዓቱም ከቀኑ ስድስት ሰዓት አካባቢ ነበር። ጲላጦስ አይሁድን፣ «እነሆ፣ ንጉሣችሁ» አላቸው። BSB BSB: It was the day of Preparation for the Passover, about the sixth hour. And Pilate said to the Jews, “Here is your King!”
15 ULB እነርሱም፣ «አስወግደው፣ አስወግደው፣ ስቀለው!» እያሉ ጮኹ። እርሱ፣ «ንጉሣችሁን ልስቀለውን?» አላቸው። የካህናት አለቆችም፣ «እኛ ከቄሣር በቀር ሌላ ንጉሥ አናውቅም» ብለው መለሱለት። BSB BSB: At this, they shouted, “Away with Him! Away with Him! Crucify Him!” “Shall I crucify your King?” Pilate asked. “We have no king but Caesar,” replied the chief priests.
16 ULB ስለዚህ ጲላጦስ ኢየሱስን እንዲሰቅሉት ፈቀደላቸው። BSB BSB: Then Pilate handed Jesus over to be crucified, and the soldiers took Him away.
17 ULB ከዚያም ኢየሱስን፣ የሚሰቀልበትን መስቀል አሸክመው የራስ ቅል፣ በዕብራይስጥ ደግሞ ጎልጎልታ ወደሚባል ቦታ ወሰዱት። BSB BSB: Carrying His own cross, He went out to The Place of the Skull, which in Hebrew is called Golgotha.
19 ULB ጲላጦስም ጽሑፍ አዘጋጅቶ በኢየሱስ መስቀል ላይ አስቀመጠ። ጽሑፉም፣ «የናዝሬቱ ኢየሱስ፣ የአይሁድ ንጉሥ» የሚል ነበር። BSB BSB: Pilate also had a notice posted on the cross. It read: JESUS OF NAZARETH, THE KING OF THE JEWS.
21 ULB የአይሁድ የካህናት አለቆችም ጲላጦስን «እርሱ ራሱን 'የአይሁድ ንጉሥ ነኝ' ብሏል ብለህ ነው እንጂ፣ 'የአይሁድ ንጉሥ' ብለህ መጻፍ የለብህም» አሉት። BSB BSB: So the chief priests of the Jews said to Pilate, “Do not write, ‘The King of the Jews,’ but only that He said, ‘I am the King of the Jews.’”
22 ULB ጲላጦስም፣ «አንዴ የጻፍሁትን ጽፌአለሁ» አላቸው። BSB BSB: Pilate answered, “What I have written, I have written.”
23 ULB ወታደሮቹ ኢየሱስን ከሰቀሉት በኋላ ልብሱን ወስደው ለእያንዳንዳቸው እንዲዳረስ አድርገው አራት ቦታ ቈራረጡት፣ እጀ ጠባቡንም ወሰዱ። BSB BSB: When the soldiers had crucified Jesus, they divided His garments into four parts, one for each soldier, with the tunic remaining. It was seamless, woven in one piece from top to bottom.
24 ULB እጀ ጠባቡ ግን ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበረና እርስ በርሳቸው «ከምንቀደው ዕጣ እንጣጣልና የሚደርሰው ይውሰደው» ተባባሉ። ይህም የሆነው በቅዱስ መጽሐፍ፣ «ልብሴን ተከፋፈሉት በእጀ ጠባቤም ላይ ዕጣ ተጣጣሉበት» የተባለው ቃል እንዲፈጸም ነው። BSB BSB: So they said to one another, “Let us not tear it. Instead, let us cast lots to see who will get it.” This was to fulfill the Scripture: “They divided My garments among them, and cast lots for My clothing.” So that is what the soldiers did.
27 ULB ደቀ መዝሙሩንም፣ «እነኋት፣ በአጠገብህ ያለችው እንደ እናትህ ትሁንልህ» አለው። ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት። BSB BSB: Then He said to the disciple, “Here is your mother.” So from that hour, this disciple took her into his home.
28 ULB ኢየሱስ ሁሉ እንደ ተፈጸመ ዐውቆ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፈው እንዲፈጸም፣ «ተጠማሁ» አለ። BSB BSB: After this, knowing that everything had now been accomplished, and to fulfill the Scripture, Jesus said, “I am thirsty.”
29 ULB በዚያም በሆምጣጤ የተሞላ ዕቃ ተቀምጦ ነበር፤ ወዲያውም በሆምጣጤ የተሞላ ሰፍነግ በሂሶጵ ወደ አፉ አስጠጉለት። BSB BSB: A jar of sour wine was sitting there. So they soaked a sponge in the wine, put it on a stalk of hyssop, and lifted it to His mouth.
30 ULB ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከጠጣ በኋላ «ተፈጸመ» አለ። ራሱንም አዘንብሎ ሞተ። BSB BSB: When Jesus had received the sour wine, He said, “It is finished.” And bowing His head, He yielded up His spirit.
31 ULB ቀኑ የመዘጋጀት ቀን በመሆኑና ሰንበትም በአይሁድ ዘንድ በጣም የሚከበር ስለነበረ በሰንበት ሥጋቸው በመስቀል ላይ መቆየት ስለሌለበት የሞት ፍርድ የተፈጸመባቸው ሰዎች እግሮቻቸው እየተሰበረ ሥጋቸው ከመስቀል እንዲወርድ አይሁድ ጲላጦስን ለመኑት። BSB BSB: It was the day of Preparation, and the next day was a High Sabbath. In order that the bodies would not remain on the cross during the Sabbath, the Jews asked Pilate to have the legs broken and the bodies removed.
33 ULB ወደ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን ሞቶ ስላገኙት እግሮቹን አልሰበሩም። BSB BSB: But when they came to Jesus and saw that He was already dead, they did not break His legs.
34 ULB ይሁን እንጂ፣ ከወታደሮቹ አንዱ ጐኑን በጦር ወጋው፣ ወዲያውም ከጐኑ ደምና ውሃ ወጣ። BSB BSB: Instead, one of the soldiers pierced His side with a spear, and immediately blood and water flowed out.
35 ULB ይህን ያየው ሰው ስለዚህ መስክሯል፣ ምስክርነቱም እውነት ነው። እናንተም እንድታምኑ የተናገረው እውነት እንደ ሆነ ያውቃል። BSB BSB: The one who saw it has testified to this, and his testimony is true. He knows that he is telling the truth, so that you also may believe.
36 ULB እነዚህ ነገሮች የሆኑት «ከዐጥንቱ አንድም አይሰበርም» የሚለው የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው። BSB BSB: Now these things happened so that the Scripture would be fulfilled: “Not one of His bones will be broken.”
37 ULB ደግሞም በሌላ መጽሐፍ፣ «የወጉትን ያዩታል» ተብሎ ተጽፎአል። BSB BSB: And, as another Scripture says: “They will look on the One they have pierced.”
38 ULB ከእነዚህ ነገሮች በኋላ አይሁድን ፈርቶ በድብቅ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረውና ከአርማትያስ ከተማ የሆነው ዮሴፍ የኢየሱስን አስከሬን ለመውሰድ ጲላጦስን ለመነ። ጲላጦስም ፈቀደለት። ዮሴፍም መጥቶ የኢየሱስን አስከሬን ወሰደ። BSB BSB: Afterward, Joseph of Arimathea, who was a disciple of Jesus (but secretly for fear of the Jews), asked Pilate to let him remove the body of Jesus. Pilate gave him permission, so he came and removed His body.
39 ULB በአንድ ወቅት በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረው ኒቆዲሞስም አንድ መቶ ነጥር ያህል የእሬትና የከርቤ ቅልቅል ይዞ መጣ። BSB BSB: Nicodemus, who had previously come to Jesus at night, also brought a mixture of myrrh and aloes, about seventy-five pounds.
40 ULB ስለዚህ የኢየሱስን አስከሬን ወስደው በአይሁድ ባህል አስከሬን ከመቀበሩ በፊት እንደሚደረገው ልማድ አስከሬኑን ሽቱ በተቀባ በበፍታ ጨርቅ ገነዙት። BSB BSB: So they took the body of Jesus and wrapped it in linen cloths with the spices, according to the Jewish burial custom.
42 ULB ቀኑ ለአይሁድ የመዘጋጀት ቀን በመሆኑና መቃብሩም ቅርብ ስለ ነበር፣ የኢየሱስን አስከሬን በዐዲሱ መቃብር አኖሩት። BSB BSB: And because it was the Jewish day of Preparation and the tomb was nearby, they placed Jesus there.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.