1 ULB ኢየሱስ ይህን ከተናገረ በኋላ ከቄድሮን ሸለቆ ማዶ የአትክልት ስፍራ ወደሚገኝበት ቦታ ሄደ፣ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደ አትክልት ስፍራው ገባ፡፡ BSB BSB: After Jesus had spoken these words, He went out with His disciples across the Kidron Valley, where they entered a garden.
2 ULB ኢየሱስ በተደጋጋሚ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደዚያ ስፍራ ይመጣ ስለ ነበር አሳልፎ ሊሰጠው ያለው ይሁዳ ቦታውን ያውቅ ነበር፡፡ BSB BSB: Now Judas His betrayer also knew the place, because Jesus had often met there with His disciples.
3 ULB ከዚያም ይሁዳ ከካህናት አለቆችና ከፈሪሳውያን ብዙ ወታደሮችንና ጠባቂዎችን ከተቀበለ በኋላ ፋኖስ፣ ችቦና የጦር መሣሪያ ይዞ ወደ አትክልት ስፍራው መጣ፡፡ BSB BSB: So Judas brought a band of soldiers and officers from the chief priests and Pharisees. They arrived at the garden carrying lanterns, torches, and weapons.
4 ULB ከዚያም እየደረሰበት ያለውን የተረዳው ኢየሱስ ወደ ፊት ወጥቶ፣ ‹‹ማንን ፈለጋችሁ?›› አላቸው፤ BSB BSB: Jesus, knowing all that was coming upon Him, stepped forward and asked them, “Whom are you seeking?”
5 ULB እነርሱ፣ ‹‹የናዝሬቱ ኢየሱስን›› ብለው መለሱለት፡፡ ኢየሱስ፣ ‹‹እኔ ነኝ›› አላቸው፡፡ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳም ከወታደሮቹ ጋር ቆሞ ነበር፡፡ BSB BSB: “Jesus of Nazareth,” they answered. Jesus said, “I am He.” And Judas His betrayer was standing there with them.
6 ULB ስለዚህ ‹‹እኔ ነኝ›› ባላቸው ጊዜ ወደ ኋላ አፈግፍገው በምድር ላይ ወደቁ፡፡ BSB BSB: When Jesus said, “I am He,” they drew back and fell to the ground.
7 ULB እንደ ገናም፣ ‹‹ማንን ፈለጋችሁ?›› አላቸው። እነርሱም፣ ‹‹የናዝሬቱ ኢየሱስን›› ብለው በድጋሚ መለሱለት፡፡ BSB BSB: So He asked them again, “Whom are you seeking?” “Jesus of Nazareth,” they answered.
8 ULB ኢየሱስ፣ ‹‹እኔ ነኝ አልኋችሁ፤ ስለዚህ እኔን የምትፈልጉ ከሆነ እነዚህን እንዲሄዱ ተዉአቸው›› አላቸው፡፡ BSB BSB: “I told you that I am He,” Jesus replied. “So if you are looking for Me, let these men go.”
9 ULB ይህም ‹‹ከሰጠኸኝ ከእነዚህ አንዱም አልጠፋብኝም›› ተብሎ የተነገረው ቃል እንዲፈጸም ነው፡፡ BSB BSB: This was to fulfill the word He had spoken: “I have not lost one of those You have given Me.”
10 ULB ከዚያም ስምዖን ጴጥሮስ የታጠቀውን ሰይፍ መዞ የሊቀ ካህናቱን አገልጋይ ቀኝ ጆሮውን ቈረጠ፡፡ የአገልጋዩም ስም ማልኮስ ነበረ፡፡ BSB BSB: Then Simon Peter drew his sword and struck the servant of the high priest, cutting off his right ear. The servant’s name was Malchus.
11 ULB ኢየሱስ ጴጥሮስን፣ ‹‹ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልስ፡፡ አብ የሰጠኝን ጽዋ መጠጣት የለብኝም እንዴ?›› አለው፡፡ BSB BSB: “Put your sword back in its sheath!” Jesus said to Peter. “Shall I not drink the cup the Father has given Me?”
12 ULB ስለዚህ ወታደሮቹና አዛዣቸው እንዲሁም የአይሁድ ጠባቂዎች ኢየሱስን ይዘው አሰሩት፡፡ BSB BSB: Then the band of soldiers, with its commander and the officers of the Jews, arrested Jesus and bound Him.
14 ULB ቀያፋ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ቢሞት ይሻላል ብሎ አይሁድን የመከረው ሰው ነው፡፡ BSB BSB: Caiaphas was the one who had advised the Jews that it would be better if one man died for the people.
15 ULB ጴጥሮስና አንድ ሌላ ደቀ መዝሙር ኢየሱስን ተከትለው ሄዱ፡፡ ሌላኛው ደቀ መዝሙር ከሊቀ ካህናቱ ጋር ይተዋወቅ ስለ ነበረ፣ ከኢየሱስ ጋር ወደ ሊቀ ካህናቱ አደባባይ ገባ፡፡ BSB BSB: Now Simon Peter and another disciple were following Jesus. Since that disciple was known to the high priest, he also went with Jesus into the courtyard of the high priest.
16 ULB ጴጥሮስ ግን በውጭ በር ላይ ቆሞ ነበር፡፡ ከሊቀ ካህናቱ ጋር የሚተዋወቀው ያ ደቀ መዝሙር በር የምትጠብቀውን አገልጋይ አናግሮ ጴጥሮስን ወደ ውስጥ አስገባው፡፡ BSB BSB: But Peter stood outside at the door. Then the disciple who was known to the high priest went out and spoke to the doorkeeper, and brought Peter in.
17 ULB ከዚያም በር ትጠብቅ የነበረችው አገልጋይ ጴጥሮስን፣ ‹‹አንተ ከዚህ ሰው ደቀ መዛሙርት አንዱ አይደለህም እንዴ?›› አለችው፡፡ እርሱ፣ ‹‹አይደለሁም›› አለ፡፡ BSB BSB: At this, the servant girl watching the door said to Peter, “Aren’t you also one of this man’s disciples?” “I am not,” he answered.
18 ULB ጊዜው ብርድ ስለ ነበረ፣ አገልጋዮችና ጠባቂዎች እሳት አቀጣጥለው ዙሪያውን ከበው እየሞቁ ነበር፡፡ ጴጥሮስም በዚያ ከእነርሱ ጋር ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር፡፡ BSB BSB: Because it was cold, the servants and officers were standing around a charcoal fire they had made to keep warm. And Peter was also standing with them, warming himself.
19 ULB ከዚያም ሊቀ ካህናቱ ኢየሱስን ስለ ደቀ መዛሙርቱና ስለ አስተማረው ትምህርት ጠየቀው፡፡ BSB BSB: Meanwhile, the high priest questioned Jesus about His disciples and His teaching.
20 ULB ኢየሱስ፣ ‹‹ለዓለም ሁሉ በግልጽ ስናገር ነበር፤ ሁልጊዜ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኵራብና በቤተ መቅደስ ሳስተምር ነበር፤ በድብቅ የተናገርሁት ምንም ነገር የለም፣ BSB BSB: “I have spoken openly to the world,” Jesus answered. “I always taught in the synagogues and at the temple, where all the Jews come together. I said nothing in secret.
21 ULB ታዲያ ለምን ትጠይቀኛለህ? የተናገርኋቸውን ነገሮች ስለሚያውቁ ሲሰሙኝ የነበሩትን ሰዎች ስለተናገርኋቸው ነገሮች ጠይቅ›› ብሎ መለሰለት፡፡ BSB BSB: Why are you asking Me? Ask those who heard My message. Surely they know what I said.”
22 ULB ኢየሱስ ይህን በተናገረ ጊዜ፣ በዚያ ከቆሙት ጠባቂዎች መካከል አንዱ በጥፊ መታውና፣ ‹‹እንደዚህ ነው ለሊቀ ካህናቱ የምትመልሰው?›› አለው፡፡ BSB BSB: When Jesus had said this, one of the officers standing nearby slapped Him in the face and said, “Is this how You answer the high priest?”
23 ULB ኢየሱስ፣ ‹‹አንዳች ክፉ ነገር ተናግሬ ከሆነ መስክርብኝ፤ በትክክል መልሼ ከሆነ ግን ለምን ትመታኛለህ?›› አለው፡፡ BSB BSB: Jesus replied, “If I said something wrong, testify as to what was wrong. But if I spoke correctly, why did you strike Me?”
24 ULB ሐናም ኢየሱስን እንደ ታሰረ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ላከው፡፡ BSB BSB: Then Annas sent Him, still bound, to Caiaphas the high priest.
25 ULB ስምዖን ጴጥሮስም ቆሞ እሳት እየሞቀ ነበር። ሰዎቹ፣ ‹‹አንተ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ አይደለህም እንዴ?›› አሉት። ጴጥሮስ፣ ‹‹አይደለሁም›› ብሎ ካደ፡፡ BSB BSB: Simon Peter was still standing and warming himself. So they asked him, “Aren’t you also one of His disciples?” He denied it and said, “I am not.”
26 ULB ጴጥሮስ ጆሮውን የቈረጠው ሰው ዘመድ የሆነ ከሊቀ ካህናቱ አገልጋዮች አንዱ፣ ጴጥሮስን፣ ‹‹አንተን በአትክልት ስፍራው ከእርሱ ጋር አላየሁህም እንዴ?›› አለው፡፡ BSB BSB: One of the high priest’s servants, a relative of the man whose ear Peter had cut off, asked, “Didn’t I see you with Him in the garden?”
27 ULB ጴጥሮስ እንደ ገና ካደ፣ ወዲያውም ዶሮ ጮኸ፡፡ BSB BSB: Peter denied it once more, and immediately a rooster crowed.
28 ULB ከዚያም ኢየሱስን ከቀያፋ ወደ ገዢው ግቢ ወሰዱት። ጊዜው ማለዳ ነበረ፣ ይዘውት የመጡት አይሁድ እንዳይረክሱና ፋሲካን መብላት እንዲችሉ ወደ ገዢው ግቢ መግባት አልፈለጉም። BSB BSB: Then they led Jesus away from Caiaphas into the Praetorium. By now it was early morning, and the Jews did not enter the Praetorium, to avoid being defiled and unable to eat the Passover.
29 ULB ስለዚህ ጲላጦስ ወደ ውጭ ወጥቶ፣ «በዚህ ሰው ላይ ያላችሁ ክስ ምንድን ነው?» ብሎ ጠየቃቸው። BSB BSB: So Pilate went out to them and asked, “What accusation are you bringing against this man?”
30 ULB እነርሱም፣ «ይህ ሰው ክፉ ባያደርግ ኖሮ ወደ አንተ አናመጣውም ነበር» አሉት። BSB BSB: “If He were not a criminal,” they replied, “we would not have handed Him over to you.”
31 ULB ስለዚህ ጲላጦስ፣ «እናንተ ወስዳችሁ በሕጋችሁ መሠረት ፍረዱበት» አላቸው። አይሁድ፣ «እኛ ማንንም ሰው ለመግደል አልተፈቀደልንም» ብለው መለሱለት። BSB BSB: “You take Him and judge Him by your own law,” Pilate told them. “We are not permitted to execute anyone,” the Jews replied.
32 ULB ይህንም ያሉት ኢየሱስ በእንዴት ዓይነት ሞት እንደሚሞት የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው። BSB BSB: This was to fulfill the word that Jesus had spoken to indicate the kind of death He was going to die.
34 ULB ኢየሱስ፣ «ይህን የምትጠይቀኝ ከራስህ ነው ወይስ ሌሎች እንድትጠይቀኝ ስለ ነገሩህ ነው?» አለው። BSB BSB: “Are you saying this on your own,” Jesus asked, “or did others tell you about Me?”
35 ULB ጲላጦስ፣ «እኔ አይሁዳዊ አይደለሁም፤ ነኝ እንዴ? ለእኔ አሳልፈው የሰጡህ የገዛ አገርህ ሰዎችና የካህናት አለቆች ናቸው፣ ምን አድርገህ ነው?» አለው። BSB BSB: “Am I a Jew?” Pilate replied. “Your own people and chief priests handed You over to me. What have You done?”
37 ULB ጲላጦስ፣ «ታዲያ አንተ ንጉሥ ነህ?» አለው፤ ኢየሱስ፣ «እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ተናገርህ፤ የተወለድሁት ወደ ዓለምም የመጣሁት ስለ እውነት ለመመስከር ነው፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል» ብሎ መለሰለት። BSB BSB: “Then You are a king!” Pilate said. “You say that I am a king,” Jesus answered. “For this reason I was born and have come into the world, to testify to the truth. Everyone who belongs to the truth listens to My voice.”
38 ULB ጲላጦስ፣ «እውነት ምንድን ነው?» ካለ በኋላ፣ እንደ ገና ወደ አይሁድ ወጣና፣ «በዚህ ሰው ላይ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም። BSB BSB: “What is truth?” Pilate asked. And having said this, he went out again to the Jews and told them, “I find no basis for a charge against Him.
39 ULB እንደ ተለመደው በየዓመቱ በፋሲካ በዓል አንድ እስረኛ እለቅላችኋለሁ፣ ታዲያ የአይሁድን ንጉሥ ልፍታላችሁን?» አላቸው። BSB BSB: But it is your custom that I release to you one prisoner at the Passover. So then, do you want me to release to you the King of the Jews?”
40 ULB ከዚያም፣ እነርሱ፣ እንደ ገና ጮኸው «ይህን ሰው አይደለም፣ በርባንን ፍታልን» አሉ። በርባን ግን ወንበዴ ነበር። BSB BSB: “Not this man,” they shouted, “but Barabbas!” (Now Barabbas was an insurrectionist.)
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.