2 ULB ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ተጠርተው ነበር፡፡ BSB BSB: and Jesus and His disciples had also been invited to the wedding.
3 ULB የወይን ጠጁ ባለቀ ጊዜ፣ የኢየሱስ እናት ኢየሱስን፣ «የወይን ጠጅ እኮ ዐልቆባቸዋል» አለችው፡፡ BSB BSB: When the wine ran out, Jesus’ mother said to Him, “They have no more wine.”
4 ULB ኢየሱስ መልሶ፣ «አንቺ ሴት፣ ከዚህ ጋር እኔ ምን ጉዳይ አለኝ? ጊዜዬ እኮ ገና አልደረሰም» አላት፡፡ BSB BSB: “Woman, what is that to you and to Me?” Jesus replied. “My hour has not yet come.”
6 ULB በዚያ፣ ለአይሁድ የመንጻት ሥርዐት የሚያገለግሉ እያንዳንዳቸው ሁለት ወይም ሦስት እንስራ የሚይዙ ስድስት የድንጋይ ጋኖች ነበሩ፡፡ BSB BSB: Now six stone water jars had been set there for the Jewish rites of purification. Each could hold from twenty to thirty gallons.
7 ULB ኢየሱስ፣ «ጋኖቹን ውሃ ሙሉአቸው» አላቸው፡፡ እነርሱም እስከ አፋቸው ሞሉአቸው፡፡ BSB BSB: Jesus told the servants, “Fill the jars with water.” So they filled them to the brim.
8 ULB ከዚያም ኢየሱስ አሳላፊዎቹን፣ «ጥቂት ቅዱና ለመስተንግዶው ኀላፊ ስጡት» አላቸው፤ እነርሱም እንዳላቸው አደረጉ፡፡ BSB BSB: “Now draw some out,” He said, “and take it to the master of the banquet.” They did so,
9 ULB የመስተንግዶው ኀላፊ፣ ወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ ቀመሰው፤ ከየት እንደ መጣ ግን አላወቀም፤ ውሃውን የቀዱት አሳላፊዎች ግን ያውቁ ነበር፡፡ እርሱም ሙሽራውን ጠርቶ BSB BSB: and the master of the banquet tasted the water that had been turned into wine. He did not know where it was from, but the servants who had drawn the water knew. Then he called the bridegroom aside
10 ULB «ሰው ሁሉ መልካሙን ወይን ጠጅ በመጀመሪያ ያቀርባል፤ መናኛውን ሰዎች ከሰከሩ በኋላ ነው የሚያቀርበው፤ አንተ ግን መልካሙን የወይን ጠጅ እስካሁን ድረስ አቈይተሃል» አለው፡፡ BSB BSB: and said, “Everyone serves the fine wine first, and then the cheap wine after the guests are drunk. But you have saved the fine wine until now!”
11 ULB ይህ በገሊላ ቃና የተደረገው ተአምር ኢየሱስ ካደረጋቸው ተአምራዊ ምልክቶች የመጀመሪያ ነው፤ ክብሩንም ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ። BSB BSB: Jesus performed this, the first of His signs, at Cana in Galilee. He thus revealed His glory, and His disciples believed in Him.
12 ULB ከዚህ በኋላ ከእናቱ፣ ከወንድሞቹና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፤ በዚያም ጥቂት ቀናት ቈዩ፡፡ BSB BSB: After this, He went down to Capernaum with His mother and brothers and His disciples, and they stayed there a few days.
13 ULB የአይሁድ ፋሲካ ቀርቦ ስለ ነበረ፣ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ፡፡ BSB BSB: When the Jewish Passover was near, Jesus went up to Jerusalem.
14 ULB በቤተ መቅደስ ውስጥ በሬዎችን፣ በጎችንና ርግቦችን ሲሸጡ የነበሩ ሰዎችን አገኘ፡፡ ገንዘብ ለዋጮችም ደግሞ በዚያ ተቀምጠው ነበር፡፡ BSB BSB: In the temple courts He found men selling cattle, sheep, and doves, and money changers seated at their tables.
15 ULB እርሱም የገመድ ጅራፍ አበጅቶ በጎችንና ከብቶችን ጭምር ሁሉንም ከቤተ መቅደስ አስወጣቸው፤ የገንዘብ ለዋጮችንም ገንዘብ በተነ፤ ጠረጴዛዎቻቸውንም ገለባበጠ። BSB BSB: So He made a whip out of cords and drove all from the temple courts, both sheep and cattle. He poured out the coins of the money changers and overturned their tables.
16 ULB ርግብ ሻጮችንም፣ «እነዚህን ከዚህ አስወጧቸው፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት ማድረጋችሁን አቁሙ!» አላቸው። BSB BSB: To those selling doves He said, “Get these out of here! How dare you turn My Father’s house into a marketplace!”
17 ULB ደቀ መዛሙርቱ፣ «ለቤትህ ያለኝ ቅናት ይበላኛል» ተብሎ የተጻፈውን አስታወሱ፡፡ BSB BSB: His disciples remembered that it is written: “Zeal for Your house will consume Me.”
18 ULB ከዚያም የአይሁድ ባለ ሥልጣኖች፣ «እነዚህን ነገሮች ለማድረግ መብት እንዳለህ ምን ምልክት ታሳየናለህ?» በማለት መለሱለት፡፡ BSB BSB: On account of this, the Jews demanded, “What sign can You show us to prove Your authority to do these things?”
19 ULB ኢየሱስ፣ «ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፤ እኔ በሦስት ቀን አስነሣዋለሁ» ብሎ መለሰ፡፡ BSB BSB: Jesus answered, “Destroy this temple, and in three days I will raise it up again.”
20 ULB ከዚያም አይሁድ፣ «ይህን ቤተ መቅደስ ለመገንባት ዐርባ ስድስት ዓመት ፈጅቶአል፤ አንተ በሦስት ቀን መልሰህ ታስነሣዋለህ?» አሉት። BSB BSB: “This temple took forty-six years to build,” the Jews replied, “and You are going to raise it up in three days?”
21 ULB ይሁን እንጂ፣ እርሱ ቤተ መቅደስ ብሎ የተናገረው፣ ስለ ራሱ ሰውነት ነበር። BSB BSB: But Jesus was speaking about the temple of His body.
22 ULB ከሙታን ከተነሣም በኋላ፣ ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ ይህን እንደ ተናገረ አስታወሱ፤ መጻሕፍትንና ኢየሱስ የተናገረውንም ቃል አመኑ። BSB BSB: After He was raised from the dead, His disciples remembered that He had said this. Then they believed the Scripture and the word that Jesus had spoken.
23 ULB በፋሲካ በዓል በኢየሩሳሌም ሳለ፣ ያደረጋቸውን ተአምራት አይተው ብዙዎች በስሙ አመኑ። BSB BSB: While He was in Jerusalem at the Passover Feast, many people saw the signs He was doing and believed in His name.
24 ULB ሆኖም፣ ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ያውቅ ስለ ነበር፣ እነርሱን አላመናቸውም፤ BSB BSB: But Jesus did not entrust Himself to them, for He knew them all.
25 ULB ደግሞም በሰው ውስጥ ያለውን ያውቅ ስለ ነበር፣ ማንም ስለ ሰው እንዲመሰክርለት አያስፈልገውም ነበር። BSB BSB: He did not need any testimony about man, for He knew what was in a man.