2 ULB ይህም ቃል ከመጀመሪያው ከእግዚአብሔር ጋር ነበር፡፡ BSB BSB: He was with God in the beginning.
4 ULB በእርሱ ሕይወት ነበረ፤ያም ሕይወት የሰው ሁሉ ብርሃን ነበር፡፡ BSB BSB: In Him was life, and that life was the light of men.
5 ULB ብርሃኑ በጨለማ ይበራል፤ ጨለማም ሊያጠፋው አልቻለም፡፡ BSB BSB: The Light shines in the darkness, and the darkness has not overcome it.
7 ULB ሁሉም በእርሱ እንዲያምኑ እርሱ ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ። BSB BSB: He came as a witness to testify about the Light, so that through him everyone might believe.
8 ULB ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ ዮሐንስ ራሱ ብርሃን አልነበረም፡፡ BSB BSB: He himself was not the Light, but he came to testify about the Light.
9 ULB ወደ ዓለም የሚመጣውና ለሰው ሁሉ ብርሃን ሰጭ የሆነው እውነተኛ ብርሃን እየመጣ ነበር፡፡ BSB BSB: The true Light, who gives light to everyone, was coming into the world.
10 ULB እርሱ በዓለም ውስጥ ነበር፤ ዓለሙም የተሠራው በእርሱ ነው፤ ዓለም ግን አላወቀውም፤ BSB BSB: He was in the world, and though the world was made through Him, the world did not recognize Him.
11 ULB የራሱ ወደ ሆኑት መጣ፤ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም፡፡ BSB BSB: He came to His own, and His own did not receive Him.
12 ULB ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች የመሆንን መብት ሰጣቸው፡፡ BSB BSB: But to all who did receive Him, to those who believed in His name, He gave the right to become children of God—
13 ULB እነርሱም ከደምና ከሥጋ ወይም ከሰው ፈቃድ አልተወለዱም፤ ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ፡፡ BSB BSB: children born not of blood, nor of the desire or will of man, but born of God.
15 ULB ዮሐንስ ስለ እርሱ መሰከረ፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ፣ «ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ከእኔ ይበልጣል፤ 'ከእኔ በፊት ነበርና' ያልኋችሁ ይህ ነው» ይል ነበር፡፡ BSB BSB: John testified concerning Him. He cried out, saying, “This is He of whom I said, ‘He who comes after me has surpassed me because He was before me.’”
16 ULB ከእርሱ ሙላት ሁላችንም በጸጋ ላይ ጸጋ ተቀበልን፤ BSB BSB: From His fullness we have all received grace upon grace.
17 ULB ሕግ በሙሴ በኩል ተሰጥቶ ነበር፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ በኩል መጣ፡፡ BSB BSB: For the law was given through Moses; grace and truth came through Jesus Christ.
19 ULB አይሁድ ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን ልከው፣ «አንተ ማን ነህ?» ብለው በጠየቁት ጊዜ፣ የዮሐንስ ምስክርነት ይህ ነው፡፡ BSB BSB: And this was John’s testimony when the Jews of Jerusalem sent priests and Levites to ask him, “Who are you?”
20 ULB እርሱ በግልጽ ተናገረ አልካደምም፤ ነገር ግን፣ «እኔ ክርስቶስ አይደለሁም» ብሎ መለሰላቸው። BSB BSB: He did not refuse to confess, but openly declared, “I am not the Christ.”
22 ULB ከዚያም እነርሱ፣ «ለላኩን መልስ መስጠት እንድንችል፣ አንተ ማን ነህ? ስለ ራስህስ ምን ትላለህ?» አሉት፡፡ BSB BSB: So they said to him, “Who are you? We need an answer for those who sent us. What do you say about yourself?”
23 ULB እርሱ፣ «ልክ ነቢዩ ኢሳይያስ እንዳለው፡- 'የጌታን መንገድ አስተካክሉ' እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ እኔ ነኝ» አላቸው፡፡ BSB BSB: John replied in the words of Isaiah the prophet: “I am a voice of one calling in the wilderness, ‘Make straight the way for the Lord.’”
24 ULB ከፈሪሳውያን የተላኩ ሰዎችም ነበሩ። BSB BSB: Then the Pharisees who had been sent
25 ULB እነርሱ፣ «ክርስቶስ፣ ኤልያስ ወይም ነቢዩ ካልሆንህ፣ ታዲያ ለምን ታጠምቃለህ?» ብለው ጠየቁት፡፡ BSB BSB: asked him, “Why then do you baptize, if you are not the Christ, nor Elijah, nor the Prophet?”
26 ULB ዮሐንስ፣ «እኔ በውሃ አጠምቃለሁ፤ ይሁን እንጂ እናንተ የማታውቁት በመካከላችሁ ቆሟል፤ BSB BSB: “I baptize with water,” John replied, “but among you stands One you do not know.
27 ULB ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ነው፤ እኔ የጫማውን ማሰሪያ ለመፍታት እንኳ የማልበቃ ነኝ» በማለት መለሰላቸው፤ BSB BSB: He is the One who comes after me, the straps of whose sandals I am not worthy to untie.”
28 ULB ይህ ሁሉ የሆንው ዮሐንስ ሲያጠምቅ በነበረበት በዮርዳኖስ ማዶ በምትገኘው በቢታንያ ነበር፡፡ BSB BSB: All this happened at Bethany beyond the Jordan, where John was baptizing.
29 ULB በማግስቱ ዮሐንስ ኢየሱስ ወደ እርሱ ሲመጣ ተመልክቶ እንዲህ አለ፤ «እነሆ፣ የዓለምን ኀጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ይኸውና! BSB BSB: The next day John saw Jesus coming toward him and said, “Look, the Lamb of God, who takes away the sin of the world!
30 ULB 'ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ በፊት ስለ ነበረ ከእኔ ይበልጣል' ብዬ ስለ እርሱ የነገርኋችሁ እርሱ ነው፡፡ BSB BSB: This is He of whom I said, ‘A man who comes after me has surpassed me because He was before me.’
31 ULB እኔ አላወቅሁትም ነበር፤ ነገር ግን እርሱ ለእስራኤል ይገለጥ ዘንድ እኔ በውሃ እያጠመቅሁ መጣሁ፡፡» BSB BSB: I myself did not know Him, but the reason I came baptizing with water was that He might be revealed to Israel.”
32 ULB ዮሐንስ እንዲህ ሲል መሰከረ፤ የእግዚአብሔር መንፈስ ከሰማይ እንደ ርግብ ሲወርድና በእርሱ ላይ ሲያርፍ አየሁ፡፡ BSB BSB: Then John testified, “I saw the Spirit descending from heaven like a dove and resting on Him.
33 ULB እኔ አላወቅሁትም ነበር፤ ነገር ግን በውሃ እንዳጠምቅ የላከኝ እርሱ፣ 'መንፈስ ሲወርድበትና ሲያርፍበት የምታየው፣ በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቀው እርሱ ነው' አለኝ፡፡ BSB BSB: I myself did not know Him, but the One who sent me to baptize with water told me, ‘The man on whom you see the Spirit descend and rest is He who will baptize with the Holy Spirit.’
34 ULB እኔ ይህን አይቻለሁ፤ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነም መስክሬአለሁ፡፡» BSB BSB: I have seen and testified that this is the Son of God.”
35 ULB ደግሞም በማግስቱ፣ ዮሐንስ ከሁለት ደቀ መዛሙርቱ ጋር ቆሞ ሳለ፣ BSB BSB: The next day John was there again with two of his disciples.
36 ULB ኢየሱስን በአጠገባቸው ሲያልፍ አዩት፤ ዮሐንስም፣ «እነሆ፣ የእግዚአብሔር በግ» አለ፡፡ BSB BSB: When he saw Jesus walking by, he said, “Look, the Lamb of God!”
37 ULB ሁለቱ ደቀ መዛሙርት፣ ዮሐንስ ይህን ሲናገር ሰምተው ኢየሱስን ተከተሉት፤ BSB BSB: And when the two disciples heard him say this, they followed Jesus.
38 ULB ከዚያም ኢየሱስ መለስ ብሎ ሲከተሉት አየና፣ «ምን ትፈልጋላችሁ?» አላቸው፡፡ እነርሱ፣ «ረቢ የት ነው የምትኖረው?» አሉት። ረቢ ማለት 'መምህር' ማለት ነው። BSB BSB: Jesus turned and saw them following. “What do you want?” He asked. They said to Him, “Rabbi” (which means Teacher), “where are You staying?”
39 ULB እርሱ፣ «ኑና እዩ» አላቸው፡፡ ከዚያም እነርሱ መጥተው የሚኖርበትን አዩ፤ በዚያም ቀን ዐብረውት ዋሉ፤ ሰዓቱም ዐሥረኛው ሰዓት ያህል ሆኖ ነበርና፡፡ BSB BSB: “Come and see,” He replied. So they went and saw where He was staying, and spent that day with Him. It was about the tenth hour.
40 ULB ዮሐንስ ሲናገር ሰምተው ኢየሱስን ከተከተሉት ከሁለቱ አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ ነበረ፡፡ BSB BSB: Andrew, Simon Peter’s brother, was one of the two who heard John’s testimony and followed Jesus.
41 ULB እርሱ በመጀመሪያ የራሱን ወንድም ጴጥሮስን አገኘውና፣ «መሲሑን አግኝተነዋል» አለው። መሲሕ 'ክርስቶስ ማለት ነው'፡፡ BSB BSB: He first found his brother Simon and told him, “We have found the Messiah” (which is translated as Christ).
42 ULB ወደ ኢየሱስም አመጣው፡፡ ኢየሱስ ጴጥሮስን ተመለከተውና፣ «አንተ የዮና ልጅ ስምዖን ነህ፤ ኬፋ ትባላለህ» አለው። ኬፋ 'ጴጥሮስ ማለት ነው'፡፡ BSB BSB: Andrew brought him to Jesus, who looked at him and said, “You are Simon son of John. You will be called Cephas” (which is translated as Peter).
43 ULB በማግስቱ፣ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ሊሄድ በፈለገ ጊዜ፣ ፊልጶስን አግኝቶ፣ «ተከተለኝ» አለው፡፡ BSB BSB: The next day Jesus decided to set out for Galilee. Finding Philip, He told him, “Follow Me.”
45 ULB ፊልጶስ ናትናኤልን አገኘውና፣ «ሙሴ በሕግ፣ ነቢያትም በትንቢት የጻፉለትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስ አግኝተነዋል» አለው፡፡ BSB BSB: Philip found Nathanael and told him, “We have found the One Moses wrote about in the Law, the One the prophets foretold—Jesus of Nazareth, the son of Joseph.”
46 ULB ናትናኤል፣ «ከናዝሬት መልካም ነገር ይወጣልን?» አለው፡፡ ፊልጶስም መጥተህ እይ አለው፡፡ BSB BSB: “Can anything good come from Nazareth?” Nathanael asked. “Come and see,” said Philip.
47 ULB ኢየሱስ፣ ናትናኤል ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ፣ «እነሆ፣ ተንኰል የሌለበት እውነተኛ እስራኤላዊ!» አለ። BSB BSB: When Jesus saw Nathanael approaching, He said of him, “Here is a true Israelite, in whom there is no deceit.”
48 ULB ናትናኤል፣ «እንዴት ታውቀኛለህ?» አለው፡፡ኢየሱስም፣ «ገና ፊልጶስ ሳይጠራህ ከበለስ ዛፍ ሥር ሳለህ አየሁህ» ብሎ መለሰለት፡፡ BSB BSB: “How do You know me?” Nathanael asked. Jesus replied, “Before Philip called you, I saw you under the fig tree.”
49 ULB ናትናኤል፣ «አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ!» ብሎ መለሰለት፡፡ BSB BSB: “Rabbi,” Nathanael answered, “You are the Son of God! You are the King of Israel!”
50 ULB ኢየሱስ፣ «ከበለስ ዛፍ ሥር ሳለህ አየሁህ ስላልሁህ አመንህን? ገና ከዚህ የሚበልጡ ነገሮችን ታያለህ» ብሎ መለሰለት፡፡ BSB BSB: Jesus said to him, “Do you believe just because I told you I saw you under the fig tree? You will see greater things than these.”
51 ULB ኢየሱስ፣ «እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ሰማያት ሲከፈቱ መላእክትም በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ» አለ፡፡ BSB BSB: Then He declared, “Truly, truly, I tell you, you will all see heaven open and the angels of God ascending and descending on the Son of Man.”