1 ULB እነዚህ ነገሮች ከተፈጸሙ በኋላ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንደ ገና በጥብርያዶስ ባሕር አጠገብ ተገለጠላቸው፤ ሁኔታውም እንደዚህ ነበር፦ BSB BSB: Later, by the Sea of Tiberias, Jesus again revealed Himself to the disciples. He made Himself known in this way:
2 ULB ስምዖን ጴጥሮስ ዲዲሞስ ከተባለው ከቶማስ፣ ከገሊላ አውራጃ ከቃና መንደር ከሆነው ከናትናኤል፣ ከዘብዴዎስ ልጆችና ከሌሎች ሁለት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ጋር ዐብረው ነበሩ። BSB BSB: Simon Peter, Thomas called Didymus, Nathanael from Cana in Galilee, the sons of Zebedee, and two other disciples were together.
3 ULB ስምዖን ጴጥሮስ፣ «ዓሣ ለማጥመድ መሄዴ ነው» አላቸው። እነርሱም፣ «እኛም ከአንተ ጋር እንሄዳለን» አሉት። በጀልባ ተሳፍረው ሄዱ፤ ነገር ግን በዚያች ሌሊት ምንም ዐሣ አላጠመዱም። BSB BSB: Simon Peter told them, “I am going fishing.” “We will go with you,” they said. So they went out and got into the boat, but caught nothing that night.
4 ULB ቀኑ እየነጋ ሳለ ኢየሱስ መጥቶ በባሕሩ ዳር ቆመ፤ እነርሱ ግን ኢየሱስ እንደ ሆነ አላወቁም ነበር። BSB BSB: Early in the morning, Jesus stood on the shore, but the disciples did not recognize that it was Jesus.
5 ULB ከዚያም ኢየሱስ «ልጆች ሆይ፣ የሚበላ ዐሣ አላችሁን?» አላቸው። «የለንም» ብለው መለሱለት። BSB BSB: So He called out to them, “Children, do you have any fish?” “No,” they answered.
6 ULB ኢየሱስ፣ «መረባችሁን ከጀልባው በቀኝ በኩል ጣሉት ታገኙማላችሁ» አላቸው። እነርሱም እንደተባሉት መረባቸውን ጣሉ፤ ነገር ግን ከዐሣው ብዛት የተነሣ መረቡን ወደ ጀልባው ውስጥ መጐተት አቃታቸው። BSB BSB: He told them, “Cast the net on the right side of the boat, and you will find some.” So they cast it there, and they were unable to haul it in because of the great number of fish.
7 ULB ከዚያም ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር ስምዖን ጴጥሮስን፣ «ጌታ እኮ ነው» አለው። ጴጥሮስ ጌታ እኮ ነው የሚለውን ቃል በሰማ ጊዜ፣ መደረቢያውን ልብስ ታጥቆ ወደ ውሃው ውስጥ ዘሎ ገባ። BSB BSB: Then the disciple whom Jesus loved said to Peter, “It is the Lord!” As soon as Simon Peter heard that it was the Lord, he put on his outer garment (for he had removed it) and jumped into the sea.
8 ULB ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት ግን ከምድር የነበራቸው ርቀት ሁለት መቶ ክንድ ያህል ብቻ ስለ ነበር ዐሣ የሞላውን መረብ እየጐተቱ በጀልባ ወደ ዳር መጡ። BSB BSB: The other disciples came ashore in the boat. They dragged in the net full of fish, for they were not far from land, only about a hundred yards.
9 ULB ወደ መሬትም በደረሱ ጊዜ፣ በላዩ ላይ ዐሣ የተቀመጠበት ፍምና እንጀራ ተዘጋጅቶ አዩ። BSB BSB: When they landed, they saw a charcoal fire there with fish on it, and some bread.
10 ULB ኢየሱስ፣ «እስኪ ካጠመዳችሁት ዐሣ ጥቂት ወደዚህ አምጡ» አላቸው። BSB BSB: Jesus told them, “Bring some of the fish you have just caught.”
11 ULB ስምዖን ጴጥሮስም ሄዶ 153 ዐሣ የሞላውን መረብ ወደ ምድር ጐተተ፤ ምንም እንኳ የዐሣው ብዛት ከፍተኛ ቢሆንም፣ መረቡ ግን አልተቀደደም ነበር። BSB BSB: So Simon Peter went aboard and dragged the net ashore. It was full of large fish, 153, but even with so many, the net was not torn.
12 ULB ኢየሱስ፣ «ኑ ቍርስ ብሉ» አላቸው። ኢየሱስ እንደ ሆነ አውቀው ነበርና ከደቀ መዛሙርቱ ማንም፣ «አንተ ማነህ?» ብሎ ሊጠይቀው የደፈረ አልነበረም። BSB BSB: “Come, have breakfast,” Jesus said to them. None of the disciples dared to ask Him, “Who are You?” They knew it was the Lord.
13 ULB ኢየሱስ እንጀራውን አንሥቶ ሰጣቸው፤ ዐሣውንም እንደዚያው አደረገ። BSB BSB: Jesus came and took the bread and gave it to them, and He did the same with the fish.
14 ULB ከሞት ከተነሣ በኋላ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ሲገለጥላቸው ይህ ለሦስተኛ ጊዜ ነበር። BSB BSB: This was now the third time that Jesus appeared to the disciples after He was raised from the dead.
15 ULB ቍርስ ከበሉ በኋላ፣ ኢየሱስ ስምዖን ጴጥሮስን፣ «የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፣ ከእነዚህ የበለጠ ትወደኛለህን?» አለው። ጴጥሮስ፣ «አዎን፣ ጌታ ሆይ፣ እንደምወድህማ አንተም ታውቃለህ» አለው። ኢየሱ፣ «ጠቦቶቼን መግብ» አለው። BSB BSB: When they had finished eating, Jesus asked Simon Peter, “Simon son of John, do you love Me more than these?” “Yes, Lord,” he answered, “You know I love You.” Jesus replied, “Feed My lambs.”
16 ULB እንደ ገና ለሁለተኛ ጊዜ፣ «የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ ትወደኛለህን?» አለው። ጴጥሮስ፣ «አዎን፣ ጌታ ሆይ፣ እንደምወድህማ አንተም ታውቃለህ» አለው። ኢየሱስ፣ «በጎቼን ጠብቅ» አለው። BSB BSB: Jesus asked a second time, “Simon son of John, do you love Me?” “Yes, Lord,” he answered, “You know I love You.” Jesus told him, “Shepherd My sheep.”
17 ULB ለሦስተኛ ጊዜ፣ «የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፣ ትወደኛለህ?» አለው። ለሦስተኛ ጊዜ «ትወደኛለህ ወይ?» ብሎ ስለ ጠየቀው ጴጥሮስ በጣም ዐዘነ። ቀጥሎም፣ «ጌታ ሆይ፣ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንደምወድህም ታውቃለህ» አለው። ኢየሱስም «በጎቼን መግብ። BSB BSB: Jesus asked a third time, “Simon son of John, do you love Me?” Peter was deeply hurt that Jesus had asked him a third time, “Do you love Me?” “Lord, You know all things,” he replied. “You know I love You.” Jesus said to him, “Feed My sheep.
19 ULB ኢየሱስ ይህን የተናገረው ጴጥሮስ በምን ዓይነት አሟሟት እግዚአብሔርን እንደሚያከብር ለማመልከት ነው። ከዚያም ኢየሱስ ጴጥሮስን፣ «ተከተለኝ» አለው። BSB BSB: Jesus said this to indicate the kind of death by which Peter would glorify God. And after He had said this, He told him, “Follow Me.”
21 ULB ጴጥሮስ ኢየሱስን፣ «ጌታ ሆይ፣ ይህ ሰውስ ምን ይሆናል?» አለው። BSB BSB: When Peter saw him, he asked, “Lord, what about him?”
22 ULB ኢየሱስ፣ «እኔ እስክመጣ እንዲቆይ ብፈልግስ አንተን ምን ይመለከትሃል? ዝም ብለህ ተከተለኝ» አለው። BSB BSB: Jesus answered, “If I want him to remain until I return, what is that to you? You follow Me!”
23 ULB በዚህ ምክንያት «ያ ደቀ መዝሙር አይሞትም» የሚል ወሬ በየ ስፍራው ተሠራጨ። ኢየሱስ ግን ለጴጥሮስ፣ «እኔ እስክመጣ እንዲቆይ ብፈልግስ አንተን ምን ይመለከትሃል?» አለው እንጂ ያ ደቀ መዝሙር አይሞትም አላለውም። BSB BSB: Because of this, the rumor spread among the brothers that this disciple would not die. However, Jesus did not say that he would not die, but only, “If I want him to remain until I return, what is that to you?”
25 ULB ከእነዚህ ሌላ ኢየሱስ ያደረጋቸው ብዙ ነገሮች አሉ። እያንዳንዱ ነገር ቢጻፍ ኖሮ ለሚጻፉት መጻሕፍት ማስቀመጫ ዓለም እንኳ የሚበቃ አይመስለኝም። BSB BSB: There are many more things that Jesus did. If all of them were written down, I suppose that not even the world itself would have space for the books that would be written.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.