1 ULB ፈሪሳውያን ኢየሱስ ከዮሐንስ የበለጠ ብዙ ሰዎችን ደቀ መዛሙርት እንደሚያደርግና እንደሚያጠምቅ ሰሙ፤ ኢየሱስም ይህን ዐወቀ፤ BSB BSB: When Jesus realized that the Pharisees were aware He was gaining and baptizing more disciples than John
2 ULB (ያጠምቁ የነበሩት ደቀ መዛሙርቱ እንጂ እርሱ ባይሆንም)፣ ኢየሱስ መስማታቸውን ባወቀ ጊዜ BSB BSB: (although it was not Jesus who baptized, but His disciples),
3 ULB የይሁዳን ምድር ለቅቆ ወደ ገሊላ ሄደ። BSB BSB: He left Judea and returned to Galilee.
4 ULB በሰማርያም በኩል ማለፍ ነበረበት። BSB BSB: Now He had to pass through Samaria.
5 ULB ከዚያም በሰማርያ ከተማ፣ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ቦታ አጠገብ ወደምትገኝ፣ ሲካር ወደምትባል ቦታ መጣ። BSB BSB: So He came to a town of Samaria called Sychar, near the plot of ground that Jacob had given to his son Joseph.
6 ULB በዚያም የያዕቆብ የውሃ ጒድጓድ ነበረ፤ ኢየሱስ ከጒዞው ብዛት ደክሞት ስለ ነበር፣ በውሃው ጒድጓድ አጠገብ ተቀመጠ፤ ጊዜውም እኩለ ቀን አካባቢ ነበር። BSB BSB: Since Jacob’s well was there, Jesus, weary from His journey, sat down by the well. It was about the sixth hour.
7 ULB አንዲት ሳምራዊት ሴት ውሃ ልትቀዳ ስትመጣ፣ ኢየሱስ፣ «እባክሽ የምጠጣው ውሃ ስጪኝ» አላት። BSB BSB: When a Samaritan woman came to draw water, Jesus said to her, “Give Me a drink.”
8 ULB ደቀ መዛሙርቱ ምግብ ለመግዛት ወደ ከተማ ሄደው ነበር። BSB BSB: (His disciples had gone into the town to buy food.)
9 ULB ሳምራዊቷም ሴት፣ «አንተ አይሁዳዊ ሆነህ፣ እኔን ሳምራዊቷን ሴት እንዴት ውሃ አጠጪኝ ትለኛለህ?» አለችው። አይሁድ ከሳምራውያን ጋር አይተባበሩም ነበርና። BSB BSB: “You are a Jew,” said the woman. “How can You ask for a drink from me, a Samaritan woman?” (For Jews do not associate with Samaritans.)
10 ULB ኢየሱስ፣ «የእግዚአብሔርን ስጦታና ውሃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን እንደሆነ ዐውቀሽ ቢሆን ኖሮ፣ አንቺው በጠየቅሽው፣ እርሱም ሕያው ውሃ በሰጠሽ ነበር» ብሎ መለሰላት። BSB BSB: Jesus answered, “If you knew the gift of God and who is asking you for a drink, you would have asked Him, and He would have given you living water.”
11 ULB ሴትዮዋም እንዲህ አለችው፤ «ጌታ ሆይ፣ አንተ መቅጃ የለህም፤ ጒድጓዱም ጥልቅ ነው፤ ታዲያ ሕያዉን ውሃ ከየት ታገኛለህ? BSB BSB: “Sir,” the woman replied, “You have nothing to draw with and the well is deep. Where then will You get this living water?
12 ULB አንተ፣ ይህን ጒድጓድ ከሰጠን፣ ከአባታችን ከያዕቆብ ትበልጣለህን? እርሱ ራሱ፣ ልጆቹና ከብቶቹም ከዚሁ ጒድጓድ ጠጥተዋል። BSB BSB: Are You greater than our father Jacob, who gave us this well and drank from it himself, as did his sons and his livestock?”
13 ULB ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላት፤ «ከዚህ ውሃ የሚጠጣ ሁሉ እንደ ገና ይጠማል፤ BSB BSB: Jesus said to her, “Everyone who drinks this water will be thirsty again.
14 ULB እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ግን ፈጽሞ ዳግመኛ አይጠማም፤ ይልቁንም፣ እኔ የምሰጠው ውሃ፣ ከውስጡ የሚፈልቅ የዘላለም ሕይወት ውሃ ምንጭ ይሆናል።» BSB BSB: But whoever drinks the water I give him will never thirst. Indeed, the water I give him will become in him a fount of water springing up to eternal life.”
15 ULB ሴትዮዋም፣ «ጌታዬ፤ ከእንግዲህ እንዳልጠማና ውሃ ለመቅዳት ወደዚህ እንዳልመጣ፣ ይህን ውሃ ስጠኝ» አለችው። BSB BSB: The woman said to Him, “Sir, give me this water so that I will not get thirsty and have to keep coming here to draw water.”
16 ULB ኢየሱስም፣ «ሂጂ፣ ባልሽን ጥሪና ወደዚህ ተመልሰሽ ነይ» አላት። BSB BSB: Jesus told her, “Go, call your husband and come back.”
17 ULB ሴትዮዋ፣ «ባል የለኝም» በማለት መለሰች፤ ኢየሱስ፣ 'ባል የለኝም' በማለትሽ ልክ ነሽ፤ BSB BSB: “I have no husband,” the woman replied. Jesus said to her, “You are correct to say that you have no husband.
18 ULB አምስት ባሎች ነበሩሽና፤ አሁን ከአንቺ ጋር ያለው ሰው ባልሽ አይደለም፤ ስለዚህ እውነቱን ተናግረሻል» ብሎ መለሰ። BSB BSB: In fact, you have had five husbands, and the man you now have is not your husband. You have spoken truthfully.”
19 ULB ሴትዮዋ፣ «ጌታ ሆይ፣ አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ ይገባኛል፤ BSB BSB: “Sir,” the woman said, “I see that You are a prophet.
21 ULB ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላት፤ «አንቺ ሴት፣ በዚህ ተራራም ሆነ በኢየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ እየመጣ መሆኑን እመኚኝ። BSB BSB: “Believe Me, woman,” Jesus replied, “a time is coming when you will worship the Father neither on this mountain nor in Jerusalem.
23 ULB ይሁን እንጂ፣ በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ አሁንም መጥቶአል፤ አብ እንደዚህ በእውነት የሚሰግዱለትን ሰዎች ይፈልጋልና። BSB BSB: But a time is coming and has now come when the true worshipers will worship the Father in spirit and in truth, for the Father is seeking such as these to worship Him.
24 ULB እግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ይገባል።» BSB BSB: God is Spirit, and His worshipers must worship Him in spirit and in truth.”
25 ULB ሴትዮዋ፣ «ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንደሚመጣ ዐውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉንም ነገር ይነግረናል» አለችው። BSB BSB: The woman said, “I know that Messiah” (called Christ) “is coming. When He comes, He will explain everything to us.”
26 ULB ኢየሱስ፣ «አሁን እያነጋገርሁሽ ያለሁት እኔ እርሱ ነኝ» አላት። BSB BSB: Jesus answered, “I who speak to you am He.”
27 ULB ልክ በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ተመልሰው መጡ፤ ኢየሱስ ከሴት ጋር በመነጋገሩ ተገረሙ፤ ይሁን እንጂ፣ ማንም፣ «ምን ትፈልጋለህ? ወይም ከእርስዋ ጋር ለምን ትነጋገራለህ?» ያለው የለም። BSB BSB: Just then His disciples returned and were surprised that He was speaking with a woman. But no one asked Him, “What do You want from her?” or “Why are You talking with her?”
28 ULB ሴትዮዋ እንስራዋን ትታ ወደ ከተማ ተመለሰች፤ ለሕዝቡም፣ BSB BSB: Then the woman left her water jar, went back into the town, and said to the people,
29 ULB «ያደረግሁትን ነገር ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ፤ እርሱ ክርስቶስ ይሆንን?» አለች፤ BSB BSB: “Come, see a man who told me everything I ever did. Could this be the Christ?”
30 ULB ሕዝቡ ከከተማ ወጥተው እርሱ ወዳለበት መጡ። BSB BSB: So they left the town and made their way toward Jesus.
31 ULB በዚህም መሐል ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን፣ «መምህር ሆይ፣ ምግብ ብላ» አሉት። BSB BSB: Meanwhile the disciples urged Him, “Rabbi, eat something.”
32 ULB እርሱ ግን፣ «እናንተ የማታውቁት፣ የምበላው ምግብ አለኝ» አላቸው። BSB BSB: But He told them, “I have food to eat that you know nothing about.”
33 ULB ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ እርስ በርስ፣ «ምግብ ያመጣለት ሰው ይኖር ይሆን?» ተባባሉ። BSB BSB: So the disciples asked one another, “Could someone have brought Him food?”
34 ULB ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ «የእኔ ምግብ የላከኝን ፈቃድ ማድረግና ሥራውንም መፈጸም ነው። BSB BSB: Jesus explained, “My food is to do the will of Him who sent Me and to finish His work.
35 ULB እናንተ 'መከር ገና አራት ወር ቀርቶታል፤ ከዚያም መከሩ ይመጣል' ትሉ የለምን? ቀና በሉና ዕርሻዎቹን ተመልከቱ፣ መከሩ ደርሷልና እያልኋችሁ ነው፤ BSB BSB: Do you not say, ‘There are still four months until the harvest’? I tell you, lift up your eyes and look at the fields, for they are ripe for harvest.
36 ULB የሚያጭድ ደመወዙን ይቀበላል፤ ለዘላለም ሕይወት የሚሆን ፍሬም ይሰበስባል፤ ስለዚህ የሚዘራውም፣ የሚያጭደውም አብረው ይደሰታሉ። BSB BSB: Already the reaper draws his wages and gathers a crop for eternal life, so that the sower and the reaper may rejoice together.
37 ULB 'አንዱ ይዘራል፣ ሌላውም ያጭዳል' የሚለው አባባል እውነት የሚሆነው በዚህ ምክንያት ነው። BSB BSB: For in this case the saying ‘One sows and another reaps’ is true.
38 ULB እኔ ያልደከማችሁበትን እንድታጭዱ ላክኋችሁ፤ ሌሎች በሥራ ደከሙ፤ እናንተም በእነርሱ ሥራ ገባችሁ።» BSB BSB: I sent you to reap what you have not worked for; others have done the hard work, and now you have taken up their labor.”
39 ULB ሴትዮዋ፣ «ያደረግሁትን ሁሉ ነገረኝ» ብላ ስለ እርሱ በሰጠችው ምስክርነት የተነሣ፣ በዚያች ከተማ ከሚኖሩ ሳምራውያን ብዙዎቹ በእርሱ አመኑ። BSB BSB: Many of the Samaritans from that town believed in Jesus because of the woman’s testimony, “He told me everything I ever did.”
40 ULB ስለዚህ፣ ሳምራውያኑ ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ፣ ከእነርሱ ጋር እንዲቈይ ለመኑት፤ እዚያም ሁለት ቀን ቈየ። BSB BSB: So when the Samaritans came to Him, they asked Him to stay with them, and He stayed two days.
41 ULB ከቃሉም የተነሣ ሌሎች ብዙ ሰዎች አመኑ። BSB BSB: And many more believed because of His message.
42 ULB ሴትዮዋንም፣ «የምናምነው አንቺ ስለ ነገርሽን ቃል ብቻ አይደለም፤ እኛ ራሳችን ሰምተነዋል፤ ይህ ሰው በእውነት የዓለም አዳኝ እንደ ሆነ እናውቃለን» ይሏት ነበር። BSB BSB: They said to the woman, “We now believe not only because of your words; we have heard for ourselves, and we know that this man truly is the Savior of the world.”
43 ULB ከእነዚያ ሁለት ቀናት በኋላም ከዚያ ተነሥቶ ወደ ገሊላ ሄደ። BSB BSB: After two days, Jesus left for Galilee.
44 ULB ነቢይ በገዛ አገሩ እንደማይከበር ኢየሱስ ራሱ ተናግሮ ነበርና። BSB BSB: Now He Himself had testified that a prophet has no honor in his own hometown.
45 ULB ወደ ገሊላ በደረሰ ጊዜ፣ የገሊላ ሰዎች በደስታ ተቀበሉት፤ እነርሱ በፋሲካ በዓል ወደዚያ ሄደው ስለ ነበር፣ በኢየሩሳሌም ያደረጋቸውን ነገሮች ሁሉ አይተው ነበር። እነርሱ ደግሞ ወደ በዓሉ ሄደው ነበርና። BSB BSB: Yet when He arrived, the Galileans welcomed Him. They had seen all the great things He had done in Jerusalem at the feast, for they had gone there as well.
46 ULB ኢየሱስም ውሃውን የወይን ጠጅ ወዳደረገባት፣ በገሊላ ወደምትገኘው ወደ ቃና ከተማ ዳግመኛ መጣ፤ በቅፍርናሆምም ልጁ የታመመበት አንድ ከንጉሣዊ ቤተ ሰብ የሆነ ሹም ነበር፤ BSB BSB: So once again He came to Cana in Galilee, where He had turned the water into wine. And there was a royal official whose son lay sick at Capernaum.
47 ULB እርሱም ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ መምጣቱን በሰማ ጊዜ፣ ወደ እርሱ ሄደና በሞት አፋፍ ላይ የሚገኘውን ልጁን መጥቶ እንዲፈውስለት ለመነው። BSB BSB: When he heard that Jesus had come from Judea to Galilee, he went and begged Him to come down and heal his son, who was about to die.
48 ULB ከዚያም ኢየሱስ፣ «እናንተ ሰዎች ምልክቶችንና ድንቆችን ካላያችሁ አታምኑም» አለው። BSB BSB: Jesus said to him, “Unless you people see signs and wonders, you will never believe.”
49 ULB ሹሙ፣ «ጌታ ሆይ፤ ልጄ ከመሞቱ በፊት እባክህ ውረድ» አለው። BSB BSB: “Sir,” the official said, “come down before my child dies.”
50 ULB ኢየሱስ፣ «ሂድ፤ ልጅህ በሕይወት ይኖራል» አለው። ሰውየው ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አምኖ ሄደ። BSB BSB: “Go,” said Jesus. “Your son will live.” The man took Jesus at His word and departed.
51 ULB በመንገድ ላይ ሳለም፣ አገልጋዮቹ አገኙትና ልጁ ተሽሎት በሕይወት እንዳለ ነገሩት። BSB BSB: And while he was still on the way, his servants met him with the news that his boy was alive.
52 ULB እርሱም ልጁ የተሻለው በስንት ሰዓት ላይ እንደ ነበረ ጠየቃቸው። እነርሱም፣ «ትኵሳቱ የለቀቀው ትናንት በሰባተኛው ሰዓት ላይ ነበር» አሉት። BSB BSB: So he inquired as to the hour when his son had recovered, and they told him, “The fever left him yesterday at the seventh hour.”
53 ULB አባትየውም፣ ኢየሱስ «ልጅህ በሕይወት ይኖራል» ብሎት የነበረው በዚያ ሰዓት እንደ ነበረ ተገነዘበ፤ ስለዚህ እርሱ ራሱና ቤተ ሰቡ በሙሉ በኢየሱስ አመኑ። BSB BSB: Then the father realized that this was the very hour in which Jesus had told him, “Your son will live.” And he and all his household believed.
54 ULB ይህም ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ በመጣ ጊዜ ያደረገው ሁለተኛው ምልክት ነው። BSB BSB: This was now the second sign that Jesus performed after coming from Judea into Galilee.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.