2 ULB ስለዚህም ከያህዌ ዘንድ እሳት ወጥታ በላቻቸው፣ እነርሱም በያህዌ ፊት ሞቱ፡፡ BSB BSB: So fire came out from the presence of the LORD and consumed them, and they died in the presence of the LORD.
3 ULB ከዚያም ሙሴ አሮንን፣ “ያህዌ ‘ወደ እኔ በሚቀርቡ ላይ ቅድስናዬን እገልጻለሁ፡፡ በሰዎች ሁሉ ፊት እከብራለሁ’ ሲል ይህን ማለቱ ነው” አለው፡፡ አሮንም ምንም አልመለሰም፡፡ BSB BSB: Then Moses said to Aaron, “This is what the LORD meant when He said: ‘To those who come near Me I will show My holiness, and in the sight of all the people I will reveal My glory.’” But Aaron remained silent.
4 ULB ሙሴ የአሮን አጎት የሆነውን የዑዝኤልን ልጆች ሚሳኤልንና ኤልጻፋንን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፣ “ወደዚህ ኑና ከመቅደሱ ደጃፍ ወንድሞቻችሁን ተሸክማችሁ ከሰፈር አውጣቸው፡፡” BSB BSB: Moses summoned Mishael and Elzaphan, sons of Aaron’s uncle Uzziel, and said to them, “Come here; carry the bodies of your cousins outside the camp, away from the front of the sanctuary.”
5 ULB ስለዚህም ሙሴ እንዳዘዘው ቀርበው የክህነት ቀሚሳቸውን እንደለበሱ ተሸክመው ከሰፈር አወጧቸው፡፡ BSB BSB: So they came forward and carried them, still in their tunics, outside the camp, as Moses had directed.
6 ULB ከዚያም ሙሴ ለአሮንና ለልጆቹ ለአልአዛርና ለኢታምር እንዲህ አላቸው፣ “እንዳትቀሰፉ ፀጉራችሁን አትንጩ፣ ልብሳችሁንም አትቅደዱ፣ ያህዌ በህዝቡ ላይ ሁሉ እንዳይቆጣ ተጠንቀቁ፡፡ ነገር ግን ቤተዘመዶቻችሁና መላው የእስራኤል ቤት የያህዌ እሳት ለበላቻቸው ያልቅሱ፡፡ BSB BSB: Then Moses said to Aaron and his sons Eleazar and Ithamar, “Do not let your hair become disheveled and do not tear your garments, or else you will die, and the LORD will be angry with the whole congregation. But your brothers, the whole house of Israel, may mourn on account of the fire that the LORD has ignited.
7 ULB እናንተ ግን ከመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አትለፉ፣ የያህዌ የቅባት ዘይት በእናንተ ላይ ነውና ትሞታላችሁ፡፡ ስለዚህም ሙሴ እንዳዘዘው አደረጉ፡፡ BSB BSB: You shall not go outside the entrance to the Tent of Meeting, or you will die, for the LORD’s anointing oil is on you.” So they did as Moses instructed.
8 ULB ያህዌ አሮንን እንዲህ አለው፣ BSB BSB: Then the LORD said to Aaron,
9 ULB “አንተ፣ ወይም ከአንተ ጋር የሚሆኑ ልጆችህ ወደ መገናኛው ድንኳን ስትገቡ እንዳትሞቱ ወይን ጠጅ ወይም የሚያሰክር መጠጥ አትጠጡ፡፡ ይህ በትውልዳችሁ ሁሉ ቋሚ ስርዓት ይሆናል፣ BSB BSB: “You and your sons are not to drink wine or strong drink when you enter the Tent of Meeting, or else you will die; this is a permanent statute for the generations to come.
10 ULB ቅዱስ በሆነውና ተራ በሆነው መሃል ለመለየት፣ ንጹህ በሆነውና ንጹህ ባልሆነው መሃል ለመለየት፣ BSB BSB: You must distinguish between the holy and the common, between the clean and the unclean,
11 ULB ለእስራኤል ህዝብ ሁሉ በሙሴ በኩል ያህዌ ያዘዘውን ስርዓት ሁሉ አስተምሩ፡፡” BSB BSB: so that you may teach the Israelites all the statutes that the LORD has given them through Moses.”
12 ULB ሙሴ ለአሮንና ለተረፉት ልጆቹ ለአልአዛርና ለኢታምርን እንዲህ አላቸው፣ “በእሳት ለያህዌ ከቀረበው የእህል ቁርባን የተረፈውን መስዋዕት ውሰድ፣ እጅግ ቅዱስ ነውና እርሾ ሳይገባበት ከመሰዊያው አጠገብ ብሉት፡፡ BSB BSB: And Moses said to Aaron and his remaining sons, Eleazar and Ithamar, “Take the grain offering that remains from the food offerings to the LORD and eat it without leaven beside the altar, because it is most holy.
13 ULB በተቀደሰው ስፍራ ብሉት፣ ምክንያቱም በእሳት ለያህዌ ከቀረበው መስዋዕት ይህ የአንተና የልጆችህ ድርሻ ነው፣ እንድነግርህ የታዘዝኩት ይህንን ነው፡፡ BSB BSB: You shall eat it in a holy place, because it is your share and your sons’ share of the food offerings to the LORD; for this is what I have been commanded.
14 ULB ለመስዋዕት የተወዘወዘውን ፍርምባና ለያህዌ የቀረበውን ወርች እግዚአብሔር ደስ በሚሰኝበት በተቀደሰው ስፍራ ብሉት፡፡ እነዚህን ድርዎቻችሁን አንተ፣ እንዲሁም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ብሉት፣ እነዚህ የእስራኤል ህዝብ ከሚያቀርበው የህብረት መስዋዕት የአንተና የልጆችህ ድርሻ ሆነው ተሰጥተዋል፡፡ BSB BSB: And you and your sons and daughters may eat the breast of the wave offering and the thigh of the contribution in a ceremonially clean place, because these portions have been assigned to you and your children from the peace offerings of the sons of Israel.
15 ULB ለያህዌ መስዋዕት ሆኖ የቀረበውን ወርች እና መስዋዕት ሆኖ የተወዘወዘውን ፍርምባ በእሳት ከተዘጋጀው የስብ መስዋዕቶች ጋር ከፍ አድርገው ለመወዘወዝና ለያህዌ መስዋዕት ለማድረግ በአንድነት ያቅርቧቸው፡፡ ይህም ያህዌ እንዳዘዘው ለዘለዓለም የአንተና የልጆችህ ድርሻ ይሆናል፡፡” BSB BSB: They are to bring the thigh of the contribution and the breast of the wave offering, together with the fat portions of the food offerings, to wave as a wave offering before the LORD. It will belong permanently to you and your children, as the LORD has commanded.”
16 ULB ከዚያ ሙሴ ለኃጢአት መስዋዕት ስለሚሆነው ፍየል ጠየቀ፣እናም በእሳት እንደተቃጠለ አወቀ፡፡ ስለዚህም በአልአዛርና በኢታምር በተቀሩትም የአሮን ልጆች ላይ ተቆጣ፤ እንዲህም አላቸው፣ BSB BSB: Later, Moses searched carefully for the goat of the sin offering, and behold, it had been burned up. He was angry with Eleazar and Ithamar, Aaron’s remaining sons, and asked,
17 ULB “ይህ የኃጢአት መስዋዕት እጅግ የተቀደሰ ሆኖ ሳለና የጉባኤውን በደል በእረሱ ፊት እንድታስወግዱበትና ኃጢአታቸውንም እንድታስተረዩላቸው ሰጥቷችሁ ሳለ ስለምን በቤተ አምልኮው ስፍራ አልበላችሁትም? BSB BSB: “Why didn’t you eat the sin offering in the holy place? For it is most holy; it was given to you to take away the guilt of the congregation by making atonement for them before the LORD.
18 ULB ተመልከቱ፣ ደሙ ወደ ቤተመቅደስ ውስጥ አልመጣም፤ እንዳዘዝኳችሁ በቤተ መቅደሱ አካባቢ ለትበሉት ይገባ ነበር፡፡” BSB BSB: Since its blood was not brought inside the holy place, you should have eaten it in the sanctuary area, as I commanded.”
19 ULB ከዚያም አሮን ለሙሴ እንደህ ሲል መለሰለት፣ “እነሆ፣ ዛሬ የኃጢአት መስዋዕታቸውን እና የሚቃጠል መስዋዕታቸውን በያህዌ ፊት አቀርቡ፣ እናም ይህ ነገር በእኔ ላይ ደርሷል፡፡ ዛሬ እኔ የኃጢአት መስዋዕቱን ብበላ ኖሮ ይህ በያህዌ ፊት ደስ ያሰኝ ነበርን?” BSB BSB: But Aaron replied to Moses, “Behold, this very day they presented their sin offering and their burnt offering before the LORD. Since these things have happened to me, if I had eaten the sin offering today, would it have been acceptable in the sight of the LORD?”
20 ULB ሙሴ ያንን ሲሰማ መልሱ አረካው፡፡ BSB BSB: And when Moses heard this explanation, he was satisfied.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.