2 ULB ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ "እነዚያ የገሊላ ሰዎች ይህ ሁሉ የደረሰባቸው በዙሪያቸው ካሉት ከሌሎች የገሊላ ሰዎች ይልቅ ኅጢአተኞች ስለ ነበሩ ነውን? BSB BSB: To this He replied, “Do you think that these Galileans were worse sinners than all the other Galileans, because they suffered this way?
3 ULB አይደለም፤ እናንተም ንስሓ ካልገባችሁ እንዲሁ ትጠፋላችሁ። BSB BSB: No, I tell you. But unless you repent, you too will all perish.
4 ULB ወይም በሰሊሆም ግንብ ተደርምሶባቸው የሞቱ ዐሥራ ስምንት ሰዎች በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካሉ ሰዎች ይልቅ ኃጢአተኞች ስለ ነበሩ ነውን? BSB BSB: Or those eighteen who were killed when the tower of Siloam collapsed on them: Do you think that they were more sinful than all the others living in Jerusalem?
5 ULB አይደለም፤ ሁላችሁም ንስሓ ባትገቡ ትጠፋላችሁ።" BSB BSB: No, I tell you. But unless you repent, you too will all perish.”
7 ULB እርሱም ለአትክልተኛው እንዲህ አለው፤ "ተመልከት! ሦስት ዓመት ሙሉ ፍሬ ፈልጌ ወደ በለሲቱ መጣሁ፤ ግን ምንም ፍሬ አላገኘሁባትም፡፡ ቊረጣት ስለምን መሬትን ታበላሻለች።" BSB BSB: So he said to the keeper of the vineyard, ‘Look, for the past three years I have come to search for fruit on this fig tree and haven’t found any. Therefore cut it down! Why should it use up the soil?’
8 ULB አትክልተኛውም መልሰና እንዲህ አለ፣ "ለዚህ ዓመት ተዋት ዙሪያዋን ኮትኩቼ ማዳበሪያ አደርግላትና BSB BSB: ‘Sir,’ the man replied, ‘leave it alone again this year, until I dig around it and fertilize it.
9 ULB በሚቀጥለው ዓመት ታፈራ ይሆናል፤ ባታፈራ ግን ቊረጣት።" BSB BSB: If it bears fruit next year, fine. But if not, you can cut it down.’”
10 ULB ኢየሱስም በሰንበት ቀን በአንዱ ምኲራብ እያስተማረ ነበር። BSB BSB: One Sabbath Jesus was teaching in one of the synagogues,
11 ULB ለዐሥራ ስምንት ዓመት ርኩስ መንፈስ ያጐበጣት አንዲት ሴት በዚያ ነበረች፡፡ እርስዋም ከመጒበጧ የተነሣ ቀና ብላ መቆም አትችልም ነበር፡፡ BSB BSB: and a woman there had been disabled by a spirit for eighteen years. She was hunched over and could not stand up straight.
12 ULB ኢየሱስም ባያት ጊዜ ጠራትና፣ "ተነሺና ከበሽታሽ ተፈወሺ" አላት። BSB BSB: When Jesus saw her, He called her over and said, “Woman, you are set free from your disability.”
13 ULB በእጁ ዳሰሳት፣ ወዲያውኑም ቀጥ ብላ ቆመች፤ እግዚአብሔርንም BSB BSB: Then He placed His hands on her, and immediately she straightened up and began to glorify God.
14 ULB አመሰገነች፡፡ የምኲራቡ አለቃ ግን በሰንበት በመፈወሷ ተቈጣና ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ "ከሳምንቱ ቀኖች ሥራ የሚሠራባቸው ስድስት ቀኖች አሉ፤ ሄዳችሁ በእነዚያ ቀኖች ተፈወሱ እንጂ በሰንበት ቀን አይሆንም አላቸው።" BSB BSB: But the synagogue leader was indignant that Jesus had healed on the Sabbath. “There are six days for work,” he told the crowd. “So come and be healed on those days and not on the Sabbath.”
15 ULB ጌታ እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ "እናንት ግብዞች! በሰንበት ቀን ከእናንተ መካከል በሬውን ወይም አህያውን ከታሰረበት በረት አወጥቶ ውኅ የማያጠጣው ማን ነው? BSB BSB: “You hypocrites!” the Lord replied. “Does not each of you on the Sabbath untie his ox or donkey from the stall and lead it to water?
16 ULB ይህች የአብርሃም ዘር የሆነች ለዐሥራ ስምንት ዓመት በሰይጣን ታስራ የኖረች ሴት በሰንበት ቀን ከበሽታዋ መፈታት አይገባትምን?" BSB BSB: Then should not this daughter of Abraham, whom Satan has kept bound for eighteen long years, be released from her bondage on the Sabbath day?”
17 ULB ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች በተናገረ ጊዜ፣ ይቃወሙት የነበሩ ሁሉ አፈሩ፣ ሕዝቡ ግን በተደረገው ድንቅ ነገር ሁሉ ደስ አላቸው። BSB BSB: When Jesus said this, all His adversaries were humiliated. And the whole crowd rejoiced at all the glorious things He was doing.
18 ULB ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ "የእግዚአብሔር መንግሥት በምን ትመሰላለች? ከምንስ ጋር አነጸጽራታለሁ? BSB BSB: Then Jesus asked, “What is the kingdom of God like? To what can I compare it?
19 ULB አንድ ሰው የሰናፍጭ ዘር በአትክልት ቦታው እንደተከላት ዛፍዋም አድጋ፣ ወፎች በቅርንጫፎችዋ ላይ ጎጆአቸውን ሠርተው ማረፊያ ያደረጉባት ዛፍ ትመሰላለች።" BSB BSB: It is like a mustard seed that a man tossed into his garden. It grew and became a tree, and the birds of the air nested in its branches.”
20 ULB እንደ ገናም እንዲህ አለ፤ "የእግዚአብሔርን መንግሥት በምን ላነጻጽራት እችላለሁ? BSB BSB: Again He asked, “To what can I compare the kingdom of God?
21 ULB የእግዚአብሔር መንግሥት አንዲት ሴት ሊጡን ሁሉ እስኪያቦካ ድረስ በሶሦስት መስፈሪያ ዱቄት ውስጥ የሰወረችውን እርሾ ትመስላለች።" BSB BSB: It is like leaven that a woman took and mixed into three measures of flour, until all of it was leavened.”
22 ULB ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ ሳለ በየከተማውና በየገጠሩ እያስተማረ ያልፍ ነበር፡፡ BSB BSB: Then Jesus traveled throughout the towns and villages, teaching as He made His way toward Jerusalem.
23 ULB አንድ ሰው፣ "ጌታ ሆይ፤ የሚድኑት ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸውን?" ብሎ ጠየቀው፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ BSB BSB: “Lord,” someone asked Him, “will only a few people be saved?” Jesus answered,
24 ULB "በጠባብዋ በር ለመግባት ታገሉ፣ ብዙዎች በዚህች በር ሊገቡ ይሞክራሉ ነገር ግን ሊገቡባት አይችሉም። BSB BSB: “Make every effort to enter through the narrow door. For many, I tell you, will try to enter and will not be able.
25 ULB የቤቱ ጌታ በሩን ይዘጋል፤ እናንተም በደጅ ቆማችሁ፤ አንኳኩታችሁ፣ 'ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤ እንድንገባ ክፈትልን' ትላላችሁ፡፡ እርሱ መልሶ 'ከየት ነው የመጣችሁት? እኔ አላውቃችሁም' ይላችኋል፡፡ BSB BSB: After the master of the house gets up and shuts the door, you will stand outside knocking and saying, ‘Lord, open the door for us.’ But he will reply, ‘I do not know where you are from.’
26 ULB ከዚያም እናንተ፣ 'ጌታ ሆይ፣ ከአንተ ጋር አብረን በልተናል፤ አብረንም ጠጥተናል፤ በአደባባዮቻችንም አስተምረሃል' ትላላችሁ፡፡ BSB BSB: Then you will say, ‘We ate and drank with you, and you taught in our streets.’
27 ULB እርሱ ግን እንዲህ ይመልሳል፤ 'ከየት እንደ መጣችሁ አላውቅም፤ እናንተ ዐመፀኞች ከእኔ ራቁ እላችኋለሁ፡፡' BSB BSB: And he will answer, ‘I tell you, I do not know where you are from. Depart from me, all you evildoers.’
28 ULB በእግዚአብሔር መንግሥት አብርሃምን፤ይስሐቅን፤ ያዕቆብን፤ ነቢያትንም በምታዩበት ጊዜ፤ እናንተ ግን በውጪ ትጣላላችሁ ከዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል፡፡ BSB BSB: There will be weeping and gnashing of teeth when you see Abraham, Isaac, Jacob, and all the prophets in the kingdom of God, but you yourselves are thrown out.
29 ULB ብዙ ሰዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ፤ ከሰሜንና ከደቡብ መጥተው በእግዚአብሔር መንግሥት በማዕድ ተቀምጠው ይደሰታሉ፡፡ BSB BSB: People will come from east and west and north and south, and will recline at the table in the kingdom of God.
30 ULB ይህንም እወቁ ኋለኞች ፊተኞች፤ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፡፡" BSB BSB: And indeed, some who are last will be first, and some who are first will be last.”
31 ULB ከዚያ በኋላ፣ አንዳንድ ፈሪሳውያን ወደ እርሱ ቀርበው፣ "ሄሮድስ ሊገድልህ ይፈልጋልና ከዚህ ወጥተህ ወደ ሌላ ስፍራ ሂድ" አሉት፡፡ BSB BSB: At that very hour, some Pharisees came to Jesus and told Him, “Leave this place and get away, because Herod wants to kill You.”
32 ULB ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ "ሂዱና ለዚያ ቀበሮ፣ 'ዛሬና ነገ አጋንንትን አወጣለሁ፤ በሽታኞችን እፈውሳለሁ፤ በሦስተኛም ቀን ሥራዬን እፈጽማለሁ' ይላል በሉት" BSB BSB: But Jesus replied, “Go tell that fox, ‘Look, I will keep driving out demons and healing people today and tomorrow, and on the third day I will reach My goal.’
33 ULB ይሁን እንጂ ዛሬና ነገ ከዚያም በኋላ ነቢይ ከኢየሩሳሌም በቀር በሌላ ስፍራ መሞት ስለሌበት ወደ ኢየሩሳሌም መንገዴን መቀጠል አለብኝ" አለ። BSB BSB: Nevertheless, I must keep going today and tomorrow and the next day, for it is not admissible for a prophet to perish outside of Jerusalem.
34 ULB አንቺ ኢየሩሳሌም! ኢየሩሳሌም ሆይ! ነቢያትን የምትገድዪ፤ መልእክተኞችሽንም የምትወግሪ ነሽ፡፡ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ ሥር እንደምትሰበስብ እኔም ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ፡፡ እናንተ ግን አልፈለጋችሁም፡፡ BSB BSB: O Jerusalem, Jerusalem, who kills the prophets and stones those sent to her, how often I have longed to gather your children together as a hen gathers her chicks under her wings, but you were unwilling!
35 ULB እነሆ፣ ቤታችሁ ባዶ ሆኖ ቀርቶአል፡፡ እላችኋለሁ፣ እናንተ 'በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነው' እስከምትሉ ድረስ አታዩኝም፡፡" BSB BSB: Look, your house is left to you desolate. And I tell you that you will not see Me again until you say, ‘Blessed is He who comes in the name of the Lord.’”