1 ULB ሕዝቡ ከበውት የእግዚአብሔርን ቃል እያዳመጡ ሳሉ፣ ኢየሱስ በጌንሳሬጥ ሐይቅ ዳር ቆሞ ነበር፡፡ BSB BSB: On one occasion, while Jesus was standing by the Lake of Gennesaret with the crowd pressing in on Him to hear the word of God,
2 ULB ሁለት ጀልባዎች በሐይቁ ጥግ በኩል ሲጎተቱ ተመለከተ፡፡ ዓሣ አጥማጆቹ ከጀልባዎቹ ወርደው መረቦቻቸውን እያጠቡ ነበር፡፡ BSB BSB: He saw two boats at the edge of the lake. The fishermen had left them and were washing their nets.
3 ULB ኢየሱስ የስምዖን ወደ ነበረችው ከጀልባዎቹ ወደ አንዲቱ ገባና ከምድር ጥቂት ፈቀቅ አድርጎ ወደ ውሃ ውስጥ እንዲያስገባት ጠየቀው፡፡ ከዚያ በኋላም በጀልባዋ ውስጥ ተቀምጦ ሕዝቡን ማስተማር ጀመረ፡፡ BSB BSB: Jesus got into the boat belonging to Simon and asked him to put out a little from shore. And sitting down, He taught the people from the boat.
4 ULB ንግግሩንም በጨረሰ ጊዜ ለስምዖን፣ “ጀልባይቱን ወደ ጥልቁ ውሃ ፈቀቅ አድርጋትና ዓሣ ለማጥመድ መረቦቻችሁን ጣሉ፡፡” አለው፡፡ BSB BSB: When Jesus had finished speaking, He said to Simon, “Put out into deep water and let down your nets for a catch.”
5 ULB ስምዖንም፣ “ጌታ ሆይ፣ ሌሊቱን ሁሉ ስንሠራ አደርን ምንም አላጠመድንም፣ ነገር ግን በቃልህ መረቡን እጥላለሁ፡፡” ብሎ መለሰለት፡፡ BSB BSB: “Master,” Simon replied, “we have worked hard all night without catching anything. But because You say so, I will let down the nets.”
6 ULB ይህንን ባደረጉ ጊዜ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ፣ መረቦቻቸውም ሊቀደዱ ደረሱ፡፡ BSB BSB: When they had done so, they caught such a large number of fish that their nets began to tear.
7 ULB ስለዚህ እንዲመጡና እንዲረዷቸው በሌላ ጀልባ የነበሩትን ጓደኞቻቸውን በጥቅሻ ጠሩ፡፡ እነርሱም መጥተው ሁለቱንም ጀልባዎች እስኪሰጥሙ ድረስ ሞሉአቸው፡፡ BSB BSB: So they signaled to their partners in the other boat to come and help them, and they came and filled both boats so full that they began to sink.
9 ULB እንደዚህም ያለው ስላጠመዷቸው ዓሣዎች እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሁሉ ተደንቀው ስለነበረ ነው፡፡ BSB BSB: For he and his companions were astonished at the catch of fish they had taken,
10 ULB በዚያም ከነበሩት መካከል የዘብዴዎስ ልጆች ዮሐንስና ያዕቆብ አብረውት ነበሩ፡፡ ኢየሱስም ለስምዖን፣ “ከእንግዲህ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህና፣ አትፍራ፡፡” አለው፡፡ BSB BSB: and so were his partners James and John, the sons of Zebedee. “Do not be afraid,” Jesus said to Simon. “From now on you will catch men.”
11 ULB ጀልባቸውን ወደ ምድር ባመጧት ጊዜ ሁሉንም ትተው ተከተሉት፡፡ BSB BSB: And when they had brought their boats ashore, they left everything and followed Him.
12 ULB ከከተማዎቹ በአንዲቱ በነበረ ጊዜ፣ መላ ሰውነቱ በለምጽ የተመታ ሰው በዚያ ነበረ፡፡ ኢየሱስንም ባየ ጊዜ በፊቱ ወድቆ፣ “ብትፈቅድስ፣ ልታነጻኝ ትችላለህ፡፡” ብሎ ለመነው፡፡ BSB BSB: While Jesus was in one of the towns, a man came along who was covered with leprosy. When he saw Jesus, he fell facedown and begged Him, “Lord, if You are willing, You can make me clean.”
13 ULB በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና፣ “እፈቅዳለሁ፣ ንጻ” አለው፡፡ ወዲያውኑም ለምጹ ከእርሱ ተወገደ፡፡ BSB BSB: Jesus reached out His hand and touched the man. “I am willing,” He said. “Be clean!” And immediately the leprosy left him.
14 ULB ለማንም እንዳይነግር አስጠነቀቀው፣ ነገር ግን፣ “ሂድና ራስህን ለካህን አሳይ፣ ሙሴ ባዘዘውም መሠረት ለእነርሱ ምስክር ይሆን ዘንድ ለመንጻትህ መሥዋዕት አቅርብ፡፡” አለው፡ BSB BSB: “Do not tell anyone,” Jesus instructed him. “But go, show yourself to the priest and present the offering Moses prescribed for your cleansing, as a testimony to them.”
15 ULB ነገር ግን ስለ እርሱ ያለው ዝና ከዚያም ርቆ ወጣ፤ ብዙም የሕዝብ አጀብ ሲያስተምር ለመስማትና ከሕመሞቻቸው ለመፈወስ በአንድነት ወደ እርሱ መጡ፡፡ BSB BSB: But the news about Jesus spread all the more, and great crowds came to hear Him and to be healed of their sicknesses.
16 ULB እርሱ ግን ወደ ገለልተኛ ስፍራዎች ሄዶ በዚያ ይጸልይ ነበር፡፡ BSB BSB: Yet He frequently withdrew to the wilderness to pray.
17 ULB ያስተምር ከነበረባቸውም ከእነዚያ በአንዱ ቀን ከገሊላና ከይሁዳ መንደሮችና አውራጃዎች እንዲሁም ከኢየሩሳሌም ከተማ መጥተው በዚያ የተቀመጡ ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራን ነበሩ፡፡ ይፈውስም ዘንድ የእግዚአብሔር ኃይል በእርሱ ላይ ነበረ፡፡ BSB BSB: One day Jesus was teaching, and the Pharisees and teachers of the law were sitting there. People had come from Jerusalem and from every village of Galilee and Judea, and the power of the Lord was present for Him to heal the sick.
18 ULB በዚያን ጊዜ ጥቂት ሰዎች ሰውነቱ የደነዘዘ ሰው በቃሬዛ ይዘው መጡ፤ በኢየሱስ ፊትም ያደርጉት ዘንድ ወደ ውስጥ የሚያስገቡበትን መንገድ ይፈልጉ ነበር፡፡ BSB BSB: Just then some men came carrying a paralyzed man on a mat. They tried to bring him inside to set him before Jesus,
19 ULB ከሕዝቡም ብዛት የተነሣ ሊያስገቡ የሚችሉበትን መንገድ አላገኙም፤ ስለዚህ ወደ ቤቱ ጣሪያ ላይ ወጥተው፣ ሰውዬውን በቃሬዛው ላይ እንዳለ በጣሪያው አሳልፈው በሰዎቹ መካከል ከኢየሱስ ፊት አወረዱት፡፡ BSB BSB: but they could not find a way through the crowd. So they went up on the roof and lowered him on his mat through the tiles into the middle of the crowd, right in front of Jesus.
20 ULB ኢየሱስ እምነታቸውን ተመልክቶ፣ “አንተ ሰው፣ ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል” አለው፡፡ BSB BSB: When Jesus saw their faith, He said, “Friend, your sins are forgiven.”
21 ULB ፈሪሳውያንና ጸሐፍት፣ “የስድብ ቃል የሚናገር ይህ ማን ነው? እግዚአብሔር ብቻ ካልሆነ በስተቀር፣ ኃጢአትን ይቅር ማለት የሚችል ማን ነው?” በማለት መጠየቅ ጀመሩ፡፡ BSB BSB: But the scribes and Pharisees began thinking to themselves, “Who is this man who speaks blasphemy? Who can forgive sins but God alone?”
22 ULB ነገር ግን ኢየሱስ ምን እንዳሰቡ አውቆ፣ “በልባችሁ ይህንን ለምን ትጠይቃላችሁ? BSB BSB: Knowing what they were thinking, Jesus replied, “Why are you thinking these things in your hearts?
23 ULB የትኛውን ማለት ይቀላል፡- ‘ኃጢአትህ ተሰረየችልህ’ ማለት ወይስ ‘ተነሣና ሂድ’ ማለት? BSB BSB: Which is easier: to say, ‘Your sins are forgiven,’ or to say, ‘Get up and walk’?
24 ULB ነገር ግን ለሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ይቅር ለማለት ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፣ ለአንተ፣ ‘ተነሣና ቃሬዛህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ’ ብዬ እናገራለሁ፡፡" BSB BSB: But so that you may know that the Son of Man has authority on the earth to forgive sins…” He said to the paralytic, “I tell you, get up, pick up your mat, and go home.”
25 ULB ከዚያ በኋላ በእነርሱ ፊት ተነሣ፣ ተኝቶበት የነበረውንም ቃሬዛ ተሸክሞ እግዚአብሔርን እያከበረ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ BSB BSB: And immediately the man stood up before them, took what he had been lying on, and went home glorifying God.
26 ULB ሰዎች ሁሉ ተገረሙ፣ እግዚአብሔርንም አከበሩ፡፡ “በዛሬው ዕለት ያልተለመደ ነገር አየን” እያሉ በፍርሃት ተሞሉ፡፡ BSB BSB: Everyone was taken with amazement and glorified God. They were filled with awe and said, “We have seen remarkable things today.”
27 ULB እነዚህ ነገሮች ከሆኑ በኋላ፣ ኢየሱስ ከዚያ ወጥቶ በቀረጥ መሰብሰቢያው ስፍራ ተቀምጦ የነበረውን ሌዊ የተባለውን ቀረጥ ሰብሳቢ ተመለከተ፡፡ እርሱንም፣ “ተከተለኝ” አለው፡፡ BSB BSB: After this, Jesus went out and saw a tax collector named Levi sitting at the tax booth. “Follow Me,” He told him,
28 ULB ስለዚህ ሌዊ ሁሉንም ትቶ ተነሥቶ ተከተለው፡፡ BSB BSB: and Levi got up, left everything, and followed Him.
29 ULB ከዚያ በኋላ፣ ሌዊ በቤቱ ለኢየሱስ ታላቅ ግብዣ አደረገለት፣ በዚያም ብዙ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና በማዕድ ቀርበው ከእነርሱ ጋር የሚመገቡ ሌሎች ሰዎችም ነበሩ፡፡ BSB BSB: Then Levi hosted a great banquet for Jesus at his house. A large crowd of tax collectors was there, along with others who were eating with them.
30 ULB ነገር ግን ፈሪሳውያንና ጻሐፍት በደቀመዛሙርቱ ላይ፣ “ከቀረጥ ሰብሳቢዎችና ከሌሎች ኃጢአተኛ ሰዎች ጋር ለምን ትበላላችሁ ትጠጣላችሁም?” እያሉ ያጉረመርሙባቸው ነበር፡፡ BSB BSB: But the Pharisees and their scribes complained to Jesus’ disciples, “Why do you eat and drink with tax collectors and sinners?”
31 ULB ኢየሱስም እንደዚህ በማለት መለሰላቸው፣ “በመልካም ጤንነት ላይ ያሉ ሐኪም አያስፈልጋቸውም፣ ሐኪም የሚያስፈልጋቸው የታመሙ ብቻ ናቸው፡፡ BSB BSB: Jesus answered, “It is not the healthy who need a doctor, but the sick.
32 ULB እኔ የመጣሁት ጻድቃንን ለንስሐ ለመጥራት ሳይሆን ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ ለመጥራት ነው፡፡” BSB BSB: I have not come to call the righteous, but sinners, to repentance.”
33 ULB እነርሱም፣ “የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ይጾማሉ ይጸልያሉም፣ የፈሪሳውያን ደቀመዛሙርትም እንደዚሁ ያደርጋሉ፡፡ የአንተ ደቀመዛሙርት ግን ይበላሉ፣ ይጠጣሉም፡፡” አሉት፡፡ BSB BSB: Then they said to Him, “John’s disciples and those of the Pharisees frequently fast and pray, but Yours keep on eating and drinking.”
34 ULB ኢየሱስም፣ “ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሚዜዎቹን እንዲጾሙ ሊያደርጋቸው የሚችል አለን? BSB BSB: Jesus replied, “Can you make the guests of the bridegroom fast while He is with them?
35 ULB ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወቅት ይመጣል በእነዚያ ቀናት ይጾማሉ፡፡” BSB BSB: But the time will come when the bridegroom will be taken from them; then they will fast.”
36 ULB ከዚያ በኋላ ኢየሱስ በምሳሌ ተናገራቸው፣ “ማንም ሰው ከአዲስ ልብስ ላይ እራፊ ቀዶ አሮጌ ልብስ አይጥፍም፡፡ እንደዚህ የሚያደርግ ከሆነ፣ ከአዲሱ ልብስ ላይ እራፊ ይቀዳል፣ ነገር ግን ከአዲሱ ልብስ ላይ የተቀደደው እራፊ ከአሮጌው ልብስ ጋር አብሮ አይሄድም፡፡ BSB BSB: He also told them a parable: “No one tears a piece of cloth from a new garment and sews it on an old one. If he does, he will tear the new garment as well, and the patch from the new will not match the old.
37 ULB እንደዚሁም፣ ማንም ሰው በአሮጌው አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ አያስቀምጥም፡፡ እንደዚህ ቢያደርግ፣ አዲሱ ወይን ጠጅ አቁማዳውን ያፈነዳዋል፣ ወይን ጠጁም ይፈሳል፣ አቁማዳውም ይበላሻል፡፡ BSB BSB: And no one pours new wine into old wineskins. If he does, the new wine will burst the skins, the wine will spill, and the wineskins will be ruined.
38 ULB ነገር ግን አዲስ ወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ይቀመጣል፡፡ BSB BSB: Instead, new wine is poured into new wineskins.
39 ULB ማንም ሰው አሮጌውን ወይን ጠጅ ከጠጣ በኋላ አዲሱን የወይን ጠጅ አይፈልግም፣ ‘አሮጌው ይሻላል’ ይላልና፡፡” BSB BSB: And no one after drinking old wine wants new, for he says, ‘The old is better.’”