1 ULB በሰንበት ቀን በእህል እርሻ መካከል በሚያልፍበት ጊዜ ደቀመዛሙርቱ እሸት እየቀጠፉና በእጆቻቸው እያሹ እህሉን ይቅሙ ነበር፡፡ BSB BSB: One Sabbath Jesus was passing through the grainfields, and His disciples began to pick the heads of grain, rub them in their hands, and eat them.
2 ULB ገር ግን ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ፣ “በሰንበት ቀን ማድረግ ያልተፈቀደውን የምታደርጉት ለምንድን ነው?” አሏቸው፡፡ BSB BSB: But some of the Pharisees asked, “Why are you doing what is unlawful on the Sabbath?”
4 ULB ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ ከተቀደሰው ኅብስት ጥቂት ወሰደ፤ ካህናትም ብቻ ይበሉ ዘንድ የተፈቀደላቸውን ለራሱ በላ። አብረውት ከነበሩትም ለአንዳንዶቸ ይበሉ ዘንድ ሰጣቸው” አላቸው፡፡ BSB BSB: He entered the house of God, took the consecrated bread and gave it to his companions, and ate what is lawful only for the priests to eat.”
5 ULB ከዚያ በኋላም፣ “የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነው” አላቸው፡፡ BSB BSB: Then Jesus declared, “The Son of Man is Lord of the Sabbath.”
6 ULB በሌላም ሰንበት ቀን ወደ ምኩራብ ገብቶ በዚያ የነበሩትን ሰዎች አስተማራቸው፡፡ በዚያም የቀኝ እጁ የሰለለች አንድ ሰው ነበረ፡፡ BSB BSB: On another Sabbath Jesus entered the synagogue and was teaching, and a man was there whose right hand was withered.
7 ULB አንድ የተሳሳተ ነገር ሲያደርግ ተመልክተው ለመክሰስ ምክንያት ያገኙ ዘንድ በሰንበት ቀን አንድን ሰው ይፈውስ እንደሆነ ፈሪሳውያንና ጸሐፍት በትኩረት ይመለከቱት ነበር፡፡ BSB BSB: Looking for a reason to accuse Jesus, the scribes and Pharisees were watching Him closely to see if He would heal on the Sabbath.
8 ULB እርሱ ግን ምን እንደሚያስቡ አውቆ፣ እጁ የሰለለችበትን ሰውዬ፣ “ተነሣና በሰዎች ሁሉ መካከል ቁም” አለው፡፡ ስለዚህም ሰውዬው ተነሣና በዚያ ስፍራ ቆመ፡፡ BSB BSB: But Jesus knew their thoughts and said to the man with the withered hand, “Get up and stand among us.” So he got up and stood there.
9 ULB ኢየሱስም፣“እኔም እናንተን እጠይቃችኋለሁ፡- በሰንበት ሕጋዊ የሚሆነው መልካም ማድረግ ነው ክፉ፣ ሕይወት ማድን ነው ወይስ ማጥፋት?” BSB BSB: Then Jesus said to them, “I ask you, which is lawful on the Sabbath: to do good or to do evil, to save life or to destroy it?”
10 ULB ከዚያም ዞር ብሎ ሁሉንም ተመለከታቸውና ለሰውዬው፣ “እጅህን ዘርጋ” አለው፤ ዘረጋውም፣ እጁም ዳነለት፡፡ BSB BSB: And after looking around at all of them, He said to the man, “Stretch out your hand.” He did so, and it was restored.
11 ULB ከዚያ በኋላም በቁጣ ተሞልተው፣ በኢየሱስ ላይ ምን እንደሚያደርጉበት እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ፡፡ BSB BSB: But the scribes and Pharisees were filled with rage and began to discuss with one another what they might do to Jesus.
12 ULB በዚያም ወቅት ኢየሱስ ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ፣ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር መጸለዩን ቀጠለ፡፡ BSB BSB: In those days Jesus went out to the mountain to pray, and He spent the night in prayer to God.
13 ULB በነጋም ጊዜ ደቀመዛሙርቱን ወደ እርሱ ጠራ፣ ከእነርሱም ‘ሐዋርያት’ ብሎ የሰየማቸውን አሥራ ሁለቱን መረጠ፡፡ BSB BSB: When daylight came, He called His disciples to Him and chose twelve of them, whom He also designated as apostles:
14 ULB የሐዋርያቱም ስም፣ ስምዖን (ጴጥሮስ ብሎ የሰየመው) ወንድሙ እንድርያስ፣ ያዕቆብ፣ ዮሐንስ፣ ፊልጶስ፣ በርተሎሚዎስ፣ BSB BSB: Simon, whom He named Peter, and his brother Andrew; James and John; Philip and Bartholomew;
15 ULB ማቴዎስ፣ ቶማስ፣ ያዕቆብ የእልፍዮስ ልጅ፣ ቀናተኛ የተባለው ስምዖን፣ BSB BSB: Matthew and Thomas; James son of Alphaeus and Simon called the Zealot;
16 ULB የያዕቆብ ልጅ ይሁዳና ከዳተኛ የሆነው ይሁዳ አስቆሮቱ ናቸው፡፡ BSB BSB: Judas son of James, and Judas Iscariot, who became a traitor.
17 ULB ከዚያ በኋላም ኢየሱስ ከተራራው ወረደና በደልዳላ ቦታ ላይ ቆመ፡፡ ከደቀመዛሙርቱ በርከት ያሉት፣ ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም እንዲሁም ከጢሮስና ከሲዶና ባሕር ዳርቻ ብዙ ሰዎች በዚያ ነበሩ፡፡ BSB BSB: Then Jesus came down with them and stood on a level place. A large crowd of His disciples was there, along with a great number of people from all over Judea, Jerusalem, and the seacoast of Tyre and Sidon.
18 ULB ወደዚያ የመጡት እርሱን ሊያዳምጡትና ከበሽታዎቻቸው ሊፈወሱ ነበር፡፡ በርኩሳን መናፍስት ሲጨነቁ የነበሩም ሰዎች ተፈወሱ፡፡ BSB BSB: They had come to hear Him and to be healed of their diseases, and those troubled by unclean spirits were healed.
19 ULB የሚፈውስ ኃይል ከእርሱ ይወጣ ስለነበረ፣ በሕዝቡ መካከል ያለ እያንዳንዱ ሰው እርሱን ለመንካት ጥረት ያደርግ ነበር፤ እርሱም ሁሉንም ፈወሳቸ. BSB BSB: The entire crowd was trying to touch Him, because power was coming from Him and healing them all.
20 ULB ከዚያ በኋላም ወደ ደቀመዛሙርቱ ተመለከተና፣ እንደዚህ አላቸው፣ “የእግዚአብሔር መንግሥት ለእናንተ ናትና፣ እናንተ ድሆች የተባረካችሁ ናችሁ፡፡ BSB BSB: Looking up at His disciples, Jesus said: “Blessed are you who are poor, for yours is the kingdom of God.
21 ULB አሁን የምትራቡ የተባረካችሁ ናችሁ፣ ትጠግባላችሁና፡፡ አሁን የምታለቅሱ የተባረካችሁ ናችሁ፣ ትስቃላችሁና፡፡ BSB BSB: Blessed are you who hunger now, for you will be filled. Blessed are you who weep now, for you will laugh.
22 ULB ሰዎች በሚጠሏችሁና በሚያገሏችሁ ጊዜ እንደዚሁም በሰው ልጅ ምክንያት ስማችሁን በክፉ ሲያነሱ የተባረካችሁ ናችሁ፡፡ BSB BSB: Blessed are you when people hate you, and when they exclude you and insult you and reject your name as evil because of the Son of Man.
23 ULB አባቶቻቸው ነቢያትን እንደዚሁ አድርገውባቸው ነበርና፣ በዚያን ቀን ሐሴት አድርጉ፣ በደስታም ዝለሉ፣ ምክንያቱም በሰማይ በእርግጥ ታላቅ ብድራት ይኖራችኋል፡፡ BSB BSB: Rejoice in that day and leap for joy, because great is your reward in heaven. For their fathers treated the prophets in the same way.
24 ULB እናንተ አሁኑኑ መጽናናትን ተቀብላችኋልና፣ ነገር ግን እናንተ ባለጠጎች ወዮላችሁ! BSB BSB: But woe to you who are rich, for you have already received your comfort.
25 ULB በኋላ ትራባላችሁና፣ እናንተ አሁን የጠገባችሁ ወዮላችሁ! በኋላ ስለምታለቅሱና ዋይ፣ ዋይ ስለምትሉ፣ እናንተ አሁን የምትስቁ ወዮላችሁ! BSB BSB: Woe to you who are well fed now, for you will hunger. Woe to you who laugh now, for you will mourn and weep.
26 ULB ሰዎች ሁሉ ስለ እናንተ መልካም በሚናገሩላችሁ ጊዜ ወዮላችሁ! ምክንያቱም አባቶቻቸው ለሐሰተኛ ነቢያት እንደዚያ ያደርጉላቸው ነበርና፡፡ BSB BSB: Woe to you when all men speak well of you, for their fathers treated the false prophets in the same way.
27 ULB ለእናንተ ለምታደምጡ ግን እላችኋለሁ፣ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፣ ለሚጠሏችሁም መልካም አድርጉላቸው፡፡ BSB BSB: But to those of you who will listen, I say: Love your enemies, do good to those who hate you,
28 ULB የሚረግሟችሁን መርቁ፣ ለሚያንገላቷችሁም ጸልዩላቸው። BSB BSB: bless those who curse you, pray for those who mistreat you.
29 ULB አንድ ጉንጭህን ለሚመታህ ሌላውንም ጉንጭህን አዙርለት፡፡ አንድ ሰው ነጠላህን የሚወስድብህ ከሆነ፣ እጀ ጠባብህን አትከልክለው፡፡ BSB BSB: If someone strikes you on one cheek, turn to him the other also. And if someone takes your cloak, do not withhold your tunic as well.
30 ULB ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፣ አንድ ሰው የአንተ የሆነውን የሚወስድብህ ከሆነ፣ እንዲመልስልህ አትጠይቀው፡፡ BSB BSB: Give to everyone who asks you, and if anyone takes what is yours, do not demand it back.
31 ULB ሰዎች እንዲያደርጉልህ የምትፈልገውን ሁሉ አንተም ለእነርሱ ልታደርግላቸው ይገባሃል፡፡ BSB BSB: Do to others as you would have them do to you.
32 ULB ኃጢአተኞችም እንኳን የሚወዷቸውን ይወዳሉና የሚወዷችሁን የምትወዱ ከሆነ፣ ምን ምስጋና ትቀበላላችሁ? BSB BSB: If you love those who love you, what credit is that to you? Even sinners love those who love them.
33 ULB ኃጢአተኞችም እንደዚያው ያደርጋሉና መልካም ለሚያደርጉላችሁ ብቻ መልካም የምታደርጉ ከሆናችሁ፣ ምን ምስጋና ትቀበላላችሁ? BSB BSB: If you do good to those who do good to you, what credit is that to you? Even sinners do the same.
34 ULB እንደሚመልሱላችሁ ለምትጠብቋቸው ብቻ የምታበድሩ ከሆናችሁ፣ ምን ምስጋና አላችሁ? የሰጡትን ያንኑ ያህል ለመቀበል ተስፋ አድርገው፣ ኃጢአተኞችም እንኳን ለኃጢአተኞች ያበድራሉ፡፡ BSB BSB: And if you lend to those from whom you expect repayment, what credit is that to you? Even sinners lend to sinners, expecting to be repaid in full.
35 ULB ነገር ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፣ መልካምም አድርጉላቸው፤ ምንም ነገር ስለመቀበል ሳትጨነቁ አበድሯቸው፣ ዋጋችሁም ታላቅ ይሆናል፡፡ እርሱ ራሱ ለማያመሰግኑና ለክፉ ሰዎች ቸር ነውና፣ እናንተም የልዑል ልጆች ትባላላችሁ፡፡ BSB BSB: But love your enemies, do good to them, and lend to them, expecting nothing in return. Then your reward will be great, and you will be sons of the Most High; for He is kind to the ungrateful and wicked.
36 ULB አባታችሁ መሐሪ እንደሆነ ሁሉ እናንተም መሐሪዎች ሁኑ፡፡ BSB BSB: Be merciful, just as your Father is merciful.
37 ULB አትፍረዱ አይፈርድባችሁም፤ አትኮንኑ አትኮነኑምም፤ ሌሎችን ይቅር በሉ፣ እናንተም ይቅር ትባላላችሁ፡፡ BSB BSB: Do not judge, and you will not be judged. Do not condemn, and you will not be condemned. Forgive, and you will be forgiven.
38 ULB ለሌሎች ስጡ፣ ለእናንተም የተጠቀጠቀ፣ የተነቀነቀ፣ በእቅፎቻችሁም ተርፎ የሚፈስ መልካም መስፈሪያ ተሰፍሮ ይሰጣችኋል፡፡ ለሌሎች ለመስፈር በምትጠቀሙበት በዚያው መስፈሪያ ለእናንተም ይሰፈርላችኋል፡፡" BSB BSB: Give, and it will be given to you. A good measure, pressed down, shaken together, and running over will be poured into your lap. For with the measure you use, it will be measured back to you.”
39 ULB ከዚያም ይህን ምሳሌ ነገራቸው፣ በኋላም፣ “አንድ ዕውር ሌላውን ዕውር ሊመራው ይችላልን? እንደዚያ ቢያደርግ፣ ሁለቱም ጉድጓድ ውስጥ ይገቡ የለምን? BSB BSB: Jesus also told them a parable: “Can a blind man lead a blind man? Will they not both fall into a pit?
40 ULB ደቀመዝሙር ከመምህሩ አይበልጥም፤ ነገር ግን አንድ ሰው ፈጽሞ ከተማረ እንደ መምህሩ ይሆናል፡፡ BSB BSB: A disciple is not above his teacher, but everyone who is fully trained will be like his teacher.
41 ULB በወንድምህ ዓይን ያለውን ትንሽ ጉድፍ ለምን ትመለከታለህ? ለምንስ በራስህ ዓይን ያለውን ግንድ አትመለከትም? በራስህ ዓይን ውስጥ ያለውን ግንድ ሳትመለከት፣ BSB BSB: Why do you look at the speck in your brother’s eye but fail to notice the beam in your own eye?
42 ULB ለወንድምህ፣ ‘ወንድሜ ሆይ፣ ዓይንህ ውስጥ ያለውን ጉድፍ ላውጣልህ’ እንዴት ትለዋለህ? አንተ ግብዝ! በመጀመሪያ በዓይንህ ውስጥ ያለውን ግንድ አውጣ፣ ከዘያም በወንድምህ ዓይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ለማውጣት አጥርተህ ታያለህ፡፡ BSB BSB: How can you say, ‘Brother, let me take the speck out of your eye,’ while you yourself fail to see the beam in your own eye? You hypocrite! First take the beam out of your own eye, and then you will see clearly to remove the speck from your brother’s eye.
43 ULB የተበላሸ ፍሬ የሚያፈራ መልካም ዛፍ የለምና፣ መልካም ፍሬም የሚያፈራ የተበላሸ ዛፍ የለም፡፡ BSB BSB: No good tree bears bad fruit, nor does a bad tree bear good fruit.
44 ULB እያንዳንዱ ዛፍ የሚታወቀው በሚያፈራው ፍሬ ነውና፤ ከእሾህ የበለስ ፍሬ አይለቀምም፣ ከቀጋ ቁጥቋጦም የወይን ፍሬ አይቆረጥም፡፡ BSB BSB: For each tree is known by its own fruit. Indeed, figs are not gathered from thornbushes, nor grapes from brambles.
45 ULB መልካሙ ሰው በልቡ ካከማቸው መልካም ሀብት መልካም የሆነውን ነገር ያወጣል፤ ክፉም ሰው በልቡ ካከማቸው ክፉ ክምችት ክፉ የሆነውን ያወጣል፡፡ በልቡ ሞልቶ ከተረፈው በአፉ ይናገራልና፡፡ BSB BSB: The good man brings good things out of the good treasure of his heart, and the evil man brings evil things out of the evil treasure of his heart. For out of the overflow of the heart the mouth speaks.
46 ULB ለምንስ ‘ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ’ ትሉኛላችሁ? ለምናገራቸውስ ነገሮች ለምን አትታዘዙም? BSB BSB: Why do you call Me ‘Lord, Lord,’ but do not do what I say?
47 ULB ወደ እኔ የሚመጣና ለቃሌ የሚታዘዝ ምን እንደሚመስል እነግራችኋለሁ እነግራችኋለሁ፣ BSB BSB: I will show you what he is like who comes to Me and hears My words and acts on them:
48 ULB መሬቱን በጥልቁ ከቆፈረ በኋላ መሠረቱን በዓለት ላይ በማድረግ ቤቱን እንደሚገነባ ሰው ነው፡፡ ጎርፍ በመጣ ጊዜ የውሃው ሙላት ያን ቤት ገፋው፣ ሆኖም በሚገባ ተገንብቶ ነበርና አልነቀነቀውም፡፡ BSB BSB: He is like a man building a house, who dug down deep and laid his foundation on the rock. When the flood came, the torrent crashed against that house but could not shake it, because it was well built.
49 ULB ነገር ግን ቃሌን ሰምቶ የማይታዘዘው ሰው ቤቱን ያለ መሠረት በመሬቱ አፈር ላይ እንደ ሠራው ሰው ነው፤ ጎርፉ በመጣ ጊዜ ቤቱን መታው፣ ወዲያውኑም ፈረሰ፣ ውድም ብሎም ጠፋ፡፡” BSB BSB: But the one who hears My words and does not act on them is like a man who built his house on ground without a foundation. The torrent crashed against that house, and immediately it fell—and great was its destruction!”